Get Mystery Box with random crypto!

ኺታሙሁ ሚስክ ከነብያችን (ሰዐወ) አገር ጠይባ ዚያራ ካለቀና ከጅዳ ጥቂት ቀናት ቆይታዬ በኋላ፣ | Abdurahman Seid (ሜጢ)

ኺታሙሁ ሚስክ

ከነብያችን (ሰዐወ) አገር ጠይባ ዚያራ ካለቀና ከጅዳ ጥቂት ቀናት ቆይታዬ በኋላ፣ ፕሌን ውስጥ አንድነትን፣ወንድማማችነትንና መከባበርን ሲያስተምሩና ሲኖሩ እኔ በግሌ ከማውቃቸው ስብዕና ጋር ወንበር ተጋራሁ። እርሳቸውም ፈዲለቱ ሸይኽ ዶክተር ጀይላን ኸድር ገመዳ ናቸው።

አብረን ስለተመለስን አልሐምዱሊላህ ብለው ጨበጡኝ። ፕሌኑ ተነስቶ ወደ አየር ሲገባ የሰፈር ዚክር አብረን አልን። እነሆ ከተቀመጡ ጊዜ አንስቶ ምላሳቸው አላህን ያወሳል፣ በመሃል ስለ ኢስላምና ሙስሊሙ ጉዳይ ሐሳብ ያነሳሉ።

በሁለት ረከዓም ቢሆን በተቀመጥንበት ዊትር እንስገድ አሉና የሱረቱል ዒምራንን የመጨረሻ ገፆች አነበቡ። እነሆ የዊትርንም ዱዓ አደረጉ። በስተመጨረሻም ውድና ልዩ ምክሮችን ለገሱኝ።

መሰል ስብዕናዎች በሕይወት አጋጣሚም ይሁን በመኗኗር ውስጥ የሚጥሉብን አሻራ አብሮ ይቆያል። ሁሉንም ከተግባር የተቆራኘ የእውቀት ባለቤቶችን እድሜ ጀሊሉ ያርዝመው።

https://t.me/mettiey