Get Mystery Box with random crypto!

Mereja Tv

የቴሌግራም ቻናል አርማ meraja_tv — Mereja Tv M
የቴሌግራም ቻናል አርማ meraja_tv — Mereja Tv
የሰርጥ አድራሻ: @meraja_tv
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.04K
የሰርጥ መግለጫ

ωєℓ¢¢σмє тσ Mereja TV™🇪🇹
✅ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ነው
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
➠ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
መረጃ ቲቪ -Mereja TV Satellite Eutelsat 8 West B Frequency 11637 / 11636 Symbol Rate 27500 5/6
🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
@meraja_tv

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-28 09:53:58
882 views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 09:53:58
ጀግኖቹ አዲስ አበባ ገብተዋል

በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ዛሬ ምሽት በሰላም አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገዋል።

ነገ በተመረጡ የመዲናችን አካባቢዎች ህዝቡ በዓለም መድረክ ሀገራችንን #ኢትዮጵያ ከፍ ላደረገው የአትሌቲክስ ቡድን አድናቆቱን በመግለፅ አቀባበል ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@TopMereja
@TopMereja
923 views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 21:55:11
ለሰርግ ወደ አዲስ አበባ የመጣችው ሀናን

ሃናን ትባላለች የ25 አመት ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነች፣ ከእጮኛዋ ጋር ኒካ ለማሰር ስላሰቡ አዲስ አበባ በመምጣት ለሰርጋቸው የሚያስፈልጋቸው እቃዎች ለመግዛት በአንድ ሆቴል 8ኛ ፎቅ ማረፊያቸውን አደረጉ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ከታዲያስ አዲስ ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል።

በሆቴሉ እንዳሉ በመካከላቸው አለመግባባት ተፈጥሮ ይጨቃጨቃሉ እሱ ክፍሉን ጥሎ ወጣ ከቆይታ በኋላ የሆቴሉን ባልደረባ "እስቲ ሂድና ቼክ አድርጋት ቅድም ተበሳጭታ ነበር" ብሎ ይልከዋል፣ እሱም ሄዶ ሲመለከት ከ8ኛ ፎቅ ራሷን ወደ 3ኛ ፎቅ ወርውራ ህይወቷ እንዳለፈ ታውቋል ሲል ፖሊስ ተናግሯል።

ፖሊስም ምርመራውን መቀጠሉን ገልፇል::


@meraja_tv
@meraja_tv
1.6K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 20:50:55
1.8K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 20:50:55
1.7K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 20:50:54
1.7K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 20:50:54
ጎንደር ላይ ሲጠበቅ 4ኪሎ የተገኘው ህወሓት

በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር ዋና መምርያ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ገብረመድኅን ፈቃዱ ( ወዲ ነጮ) ቀብር ትናንት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሲፈጸም ቀብሩ ላይ የተገኙት የትግራይ ተወላጆች የሕወሓትን መፈክር ሲያሰሙ ( ለመንግሥት ያላቸውን ተቃውሞ ሲያሰሙም ጭምር ) ታይተዋል ።

ይህ ድምጽ በዘመነ ኢሕአዴግ ተሰምቶ ቢሆንስ ? አሁን መቐለ ላይ የተሰማ የተቃውሞ ድምጽ ቢሆንስ ? መንግሥትስ ለምን ይህ እንዲሆን ፈቀደ ? የዚህን ያህል ነው የዜጎችን መብት የሚያከብረው ማለት ነው ? አንድን ጋዜጠኛ አስሮ የት እንዳደረሰው የማይታወቀው መንግሥት ሩቅ ሄዶ ሲፈልጋቸው የነበሩት 4 ኪሎ አፍንጫው ስር መጥተው ሲጮሁበት ምነው የበዛ ታጋሽነትን አሳየ ?

Via Tewodros TeklaAregay

@TopMereja
@TopMereja
1.5K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 20:33:35
የአርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

የአርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የቀብር ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት በቡልቡላ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ተፈፀመ።ሁለገቧ አርቲስት ዘነቡ ገሰሰ ባደረባት የጡት ካንሰር ህመም ምክንያት በህክምናና በፀበል ስትረዳ ቆይታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

የአርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የቀብር ሰነ ስርዓት ላይ ወዳጅ ፣ ዘመዶቿ እና አርቲስቶች እንዲሁም አድናቂዎቿ በተገኙበት ተፈፅሟል።አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ በተዋናይትነት፣ በርካታ አጫጭር ተከታታይ ድራማዎችን፣ የመድረክ ትያትሮች ላይም በተዋናይነት እንዲሁም በርካታ ፊልሞችን እና የቴሌቭዥን ድራማዎችን ከመስራት ባለፈ በውዝዋዜ ሙያ ሀገሯን ስታገለግል ቆይታለች ።
አርቲስቷ ካላት የኪነ ጥበብ ችሎታ ባለፈ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ በማድረግም ትታዉቃለች ።

ለ 35 አመታት በኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ውስጥ የራሷን አሻራ ያኖረችው አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ በትላንትናው ዕለት ነበር ቡልቡላ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከዚህ አለም በሞት የተለየችው።

አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የሁለት ሴቶች እና የሁለት ወንዶች እናት ነበረች። ሁለት የልጅ ልጆችን አይታለች።

ቶፕ መረጃ ለአርቲስቷ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎች እና ወዳጆች ሁሉ መጽናናትን ይመኛል።

@Meraja_tv
@Meraja_tv
1.9K views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 23:32:37
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው
በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
መልካም የትንሣኤ በዓል




@happybirthdaypic
@happybirthdaypic
1.5K views20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ