Get Mystery Box with random crypto!

የአርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ የአርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የቀብር ስነ-ስርዓት | Mereja Tv

የአርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

የአርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የቀብር ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት በቡልቡላ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ተፈፀመ።ሁለገቧ አርቲስት ዘነቡ ገሰሰ ባደረባት የጡት ካንሰር ህመም ምክንያት በህክምናና በፀበል ስትረዳ ቆይታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

የአርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የቀብር ሰነ ስርዓት ላይ ወዳጅ ፣ ዘመዶቿ እና አርቲስቶች እንዲሁም አድናቂዎቿ በተገኙበት ተፈፅሟል።አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ በተዋናይትነት፣ በርካታ አጫጭር ተከታታይ ድራማዎችን፣ የመድረክ ትያትሮች ላይም በተዋናይነት እንዲሁም በርካታ ፊልሞችን እና የቴሌቭዥን ድራማዎችን ከመስራት ባለፈ በውዝዋዜ ሙያ ሀገሯን ስታገለግል ቆይታለች ።
አርቲስቷ ካላት የኪነ ጥበብ ችሎታ ባለፈ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ በማድረግም ትታዉቃለች ።

ለ 35 አመታት በኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ውስጥ የራሷን አሻራ ያኖረችው አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ በትላንትናው ዕለት ነበር ቡልቡላ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከዚህ አለም በሞት የተለየችው።

አርቲስት ዘነቡ ገሠሠ የሁለት ሴቶች እና የሁለት ወንዶች እናት ነበረች። ሁለት የልጅ ልጆችን አይታለች።

ቶፕ መረጃ ለአርቲስቷ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎች እና ወዳጆች ሁሉ መጽናናትን ይመኛል።

@Meraja_tv
@Meraja_tv