Get Mystery Box with random crypto!

ጎንደር ላይ ሲጠበቅ 4ኪሎ የተገኘው ህወሓት በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ኤሌክትሮ | Mereja Tv

ጎንደር ላይ ሲጠበቅ 4ኪሎ የተገኘው ህወሓት

በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር ዋና መምርያ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ገብረመድኅን ፈቃዱ ( ወዲ ነጮ) ቀብር ትናንት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ሲፈጸም ቀብሩ ላይ የተገኙት የትግራይ ተወላጆች የሕወሓትን መፈክር ሲያሰሙ ( ለመንግሥት ያላቸውን ተቃውሞ ሲያሰሙም ጭምር ) ታይተዋል ።

ይህ ድምጽ በዘመነ ኢሕአዴግ ተሰምቶ ቢሆንስ ? አሁን መቐለ ላይ የተሰማ የተቃውሞ ድምጽ ቢሆንስ ? መንግሥትስ ለምን ይህ እንዲሆን ፈቀደ ? የዚህን ያህል ነው የዜጎችን መብት የሚያከብረው ማለት ነው ? አንድን ጋዜጠኛ አስሮ የት እንዳደረሰው የማይታወቀው መንግሥት ሩቅ ሄዶ ሲፈልጋቸው የነበሩት 4 ኪሎ አፍንጫው ስር መጥተው ሲጮሁበት ምነው የበዛ ታጋሽነትን አሳየ ?

Via Tewodros TeklaAregay

@TopMereja
@TopMereja