Get Mystery Box with random crypto!

Master Mind Group

የቴሌግራም ቻናል አርማ mastermindgroup — Master Mind Group M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mastermindgroup — Master Mind Group
የሰርጥ አድራሻ: @mastermindgroup
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.71K
የሰርጥ መግለጫ

✍በህይወትዎ ምን ማሳከት ይፈልጋሉ? ቀንዎን በስኬት እና በውጤት ለማሳለፍ።
ውጤታማ የቢዝነስ እና የሽያጭ ሰው ለመሆን።
. የሰራ ፈጠራ ስልጠና
. ለግል ህይወት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና
. የራሰን አቅም በሚገባ ለማወቅ
. ስለ ህልምዎ ፤ ስለ ራዕይዎ ፤ ስለ የህይወት ግብዎ ለማወቅ።
. አነቃቂ እና አስተማሪ የስኬታማ ሰዎች ታሪክ
. በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ እና ውጤታማ ለመሆን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-25 10:01:09 በህይወት ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ እንዲመጣ ፡ ከፈለግህ ፡ ቀላሉን ፡ መንገድ ፡ አትምረጥ። ቀላሉ ፡ መንገድ ፡ የተለመደ ፡ ቦታ ፡ የሚያደርስ ፡ ነው። የተለመደ ፡ ውጤት ፡ የሚያስገኝ ፡ ነው። ቀላሉ ፡ መንገድ ፡ እርካታ ፡ የሌለበት ፤ ሌሎች ፡ ስለሆኑት ፡ የምትሆነውና ፡ ስለኖሩት ፡ የምትኖረው ፡ ነው።
የኔ ፡ ምትለውን ፡ ውጤት ፡ አይሰጥህም።
ከባዱ ፡ መንገድ ፡ ግን ፡ አሰልቺ ፣ የሚያቆስል ፣ የሚያደክምና ፡ የሚያሰቃይ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል ፡ ነገር ፡ ግን ፡ ጣፋጭ ፡ እርካታንና ፡ ስኬትን ፡ ያጎናጽፍሃል።
ተስፋ ፡ ሳትቆርጥ ፡ ሂደቱን ፡ ከተቀበልህ ፡ ውጤታማ ፡ ትሆናለህ።

ብሩክ የሺጥላ

መልካም ቀን!
509 views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 07:56:34
ዓላማ-መር ሁኑ!

በሕይወታችሁ ልትክዷቸው የማትችሏቸው ሁሉት ኃይሎች አሉ፡፡ አንደኛው ኃይል “የመገፋት ኃይል” ሲሆን፣ ሁለተኛው ኃይል ደግም “የመመራት ኃይል” ነው፡፡ የምትወስኗቸውን ውሳኔዎቻችሁን፣ የምትመርጧቸውን ምርጫዎቻችሁንና የምታደርጓቸውን ተግባሮቻችሁን በሙሉ ከእነዚህ ከሁለት ኃይሎች በአንዱ ተጽእኖ እንደምታደርጉ አትዘንጉ፡፡

ምርጫዎቻችሁና ውሳኔዎቻችን የምታደርጉት በየእለቱ በሚመጡ ችግሮች እየተገፋችሁ ከሆነ መጨረሻችሁ የት እንደሆነ የማይታወቅ ሰዎች ወደመሆን ትወርዳላችሁ፡፡

ከዚህ በተቃራኒ በምንም ሁኔታና ችግር ውስጥ ብታልፉም በሁኔታዎቹ እየተገፋችሁ ከአንዱ ውሳኔ ወደሌላኛው ውሳኔ ከመወዛገብ ተረጋግታችሁ ከሕልማችሁ፣ ከዓላማችሁና ከራእያችሁ አንጻር ምርጫና ውሳኔን ስታደርጉ እናንተ በሁኔታዎች የምትገፉ ሳትሆኑ በዓላማችሁ የምትመሩ አይነት ሰዎች ናችሁ፡፡

በእነዚህ በሁለቱ የሕይወት ሂደቶች መካከል ሰፊ የሆነ ልዩነት አለ፡፡ ከችግር አንጻር መወሰን ይገፋናል፣ ከዓላማ አንጻር መወሰን ግን ይመራናል! ከችግር አንጻር መገፋት በፍርሃት ያደናብረናል፡፡ ከዓላማ አንጻር መመራት ግን ያረጋጋናል፡፡ የአንዱ ኃይል አሉታዊ ኃይል ነው፤ የሌላኛው ኃይል ግን አዎንታዊ ነው፡፡

በችግርና በፍርሃት አትገፉ! በዓላማና በሕልማችሁ ተመሩ!

ከዶ/ር እዮብ ማሞ

መልካም ቀን!
628 viewsedited  04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:45:41 ያጣነው አቅም ሳይሆነ ፍላጎት ነው!

ባላሰብነውና ባልጠበቅነው መንገድ ሰዎች ሲያታልሉን ሁኔታው የሚያሳየው ምንም ያህል ንቁና ጎበዝ ብንሆንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ የማናስተውላቸው ሁኔታዎች እንዳሉ እንጂ ነገር የማይገባንና ኋላ ቀር መሆናችንን አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ ሁሉም ሰው የሚያልፍበት “ሰው” ከመሆን መገለጫዎች አንዱ ነው፡፡

ነገር የማይገባንና ኋላ ቀር ነን የሚያሰኘን አንድ ሰው ትክክለኛ ማንነት እንደሌለው፣ አታላይ እንደሆነ፣ ሁለት መልክ ያለው ሕይወት እንደሚኖር፣ ለእኛ የሚነግረንና በእርጥም የሚኖረው ሕይወት የተለያዩ እደሆኑና ከዚያ ሰው ጋር ያለን ግንኘነት እንደማያዛልቀን ውስጣችን እያወቀው ይህንን ያወቅነውን እውነት ተመርኩዘን ትክክለኛን ውሳኔ ለመወሰን አለመፈለጋችን ነው፡፡

በሌላ አገላለጽ የብዙዎቻችን ችግር የመታለል ችግር አይደለም፡፡ የብዙዎቻችን ችግር የሰው ማንነቱ እየገባን ሳለ የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት ከዚያ ሰው መለየት አለመፈለጋችን ነው፡፡ እዚህ ጋር አስተውሉልኝ፡፡ መለየት “አለመቻላችን” አላልኩም፤ “አለመፈለጋችን” ነው ያልኩት፡፡ እዚህ ሁለት ሁኔታዎች ስለሚለያዩ ማለት ነው፡፡

ከአንድ ሰው ጋር ለመለየት ወይም ግንኙነታችንን ስነ-ስርአት ለማስያዝ ፈቃድና ፍላጎት ካለን ያንን ለማድረግ አቅሙ አለን፡፡ ሌሎች ሰዎች አድረገውታል፣ አሁንም በማድረግ ላይ ይኛሉ፤ ስለዚህ እኛም እንችላለን፡፡ ሆኖም ፈቃዳችንን የያዘው ነገር ካለ ግን “ምን ሆኛሁ?” እስከምንል ድረስ ከዚያ ሰው ስር ስር ተወትፈን እንኖራን፡፡

ለሕይወታችሁ ከማይበጃችሁና መርዛማ ግንኙነትን ከሚፈጥሩ ሰዎች የመለየትን ፈቃደኝነት፣ ፍላጎትና ቁርጠኝነት ያዳበራችሁ ቀን የሕይወታሁችን 90 በመቶ ችግር እንዳቃለላችሁ ላስታውሳችሁ፡፡

መልካም ቀን!
619 views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:44:13
ያጣነው አቅም ሳይሆነ ፍላጎት ነው!
539 views04:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 12:15:19
#ሶስቱ_ቀመሮች
#1_ትዕግስት
በማንኛውም ጊዜ ሊኖራችሁ የሚገባ ነገር ትዕግስት ነው ፡፡ የምንኖረው በውድድር ዓለም በመሆኑ የሌሎችን ሰዎች እርዳታም ሆነ እሺታ ለማግኘት ትዕግስተኛ መሆን ያስፈልጋል ፡፡

ትዕግስት ከሌላችሁ ሁሌም የምታገኙት ምላሽ እምቢታ ይሆናል ፡፡ ከሰዎች ጋር በሚኖራችሁ ግንኙነት እጅግ የበዛ ትዕግስት ያስፈልጋችኋል ፡፡ ሁሌም ራሳችሁን መቆጣጠር መቻል አለባችሁ ፡፡ ብዙዎቹ ሰዎች ትዕግስት እንደሌላቸው የምታውቁት በሁለት ሰኮንድ ውስጥ ልታናድዷቸው የምትችሉ በመሆናቸው ነው ፡፡

#2_ትህትና
የልብ ትህትናን የሚወዳደር አስደናቂ ነገር መኖሩን እጠራጠራለሁ ፡፡ ማንም ሰው ተሳስቶ ሰርቶ ለመተቸት ስነሳሳ ለልቤ የምነግረው እኔ ከእሱ የበላለጡ ብዙ ስህተቶችን መስራቴን ነው ፡፡ እናም አስተያየት ከሰጠሁም የምሰጠው በትህትና ነው ፡፡

በፍቅር ፣ በመተሳሰብና በትህትና የተነሳ ባይሆን ኖሮ ሕይወቴን መልካም የሚያደርጉልኝን እርዳታዎች ያደረጉልኝ ሰዎች ሁሉ ላይገኙ ይችሉ ነበር ፡፡

#3_አክብሮት
ሰዎችን በማክበሬ መልካም ስሜት ይሰማኛል ፡፡ በምላሹም ሰዎች የመናቅ ስሜት አያሳዩኝም ፡፡ ምክንያቱም የምንቀበለው ለላክነው ነገር መልስ የሚሆነውን ነው ፡፡

እኛ የሰው ማግኔቶች ነን ፡፡ የምንስበው በልባችንና በነፍሳችን የላክነውን ድምር ነው ፡፡

እነዚህ ሶስት ቀመሮች ካሏችሁ… እናንተ ወደ ሀብት ጉዞ ላይ ናችሁ
695 views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 10:58:22
646 views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 10:58:16 “አንድ ሰው በትርፍ ጊዜው ብዙ ሙታን ወደተቀበሩበት የመቃብር ስፍራ ሄዶ በሰዎች መቃብር ላይ የተጻፉትን ጽሑፎች በማንበብ ላይ ሳለ፣ በአንድ ሰው መቃብር ላይ አንድ ግር የሚል ጽሑፍ አነበበ።

ጽሑፉ በ”30 ዓመቱ ሞተ፣ በ60 ዓመቱ ተቀበረ” ይላል።

ግር ብሎት ቆሞ ማሰላሰል ጀመረ፡፡ “አንድ ሰው በ30 ዓመቱ ሞቶ እንዴት ለ30 ዓመታት ሳይቀበር ሊቆይ ቻለ?” ይህንን እያሰበ የጽሑፉን ትርጉም የሚያውቅ አንድ ሰው ደረሰ፡፡

“ምን እንደምታስብ ገብቶኛል” አለው ሃሳቡን አንብቦ፡፡

ጥያቄውን በግምት ደርሶበት ኖሮ በቀጥታ መልሱን ነገረው፡፡

“ይህ ሰው እጅግ በጣም የሚያስገርም ራእይና ዓላማ የነበረው ሰው ነበር፡፡ ብዙ ነገሮችን የመስራት እቅድ የነበረውና በዚህም ትጋቱ በሕብረተሰቡ ዘንድ እጅግ የታወቀና ለትልቅ ነገር የሚጠበቅ ሰው ነበር፡፡ ልክ 30 ዓመት ሲሞላው በተለያዩ ውጣ ውረዶች በማለፉ ምክንያት ተስፋ በመቁረጥ ዓላማውን ሁሉ ትቶ ከርታታ ሰው ለመሆን በቃ፡፡

የሚቀጥሉትን 30 ዓመታት እንዲሁ በየቦታው ሲንቀዋለል ነው ያሳለፈው፤ ካለምንም ዓላማ፡፡ የጽሑፉ ትርጉም ይህ ነው፡፡

ሰውዬው ሞተ ብለው የሚያምኑት ራእዩን በጣለበትና ጊዜውን በተራ ነገር ማሳለፍ በጀመረበት በ30 ዓመቱ ነው - በአካል ቢኖርም ሞቷል ነው አባባላቸው፡፡ ልክ በ60 ዓመቱ ታምሞ አካላዊ ሞትን ሲሞት ያን ጊዜ ተቀበረ ማለታቸው ነው”

በአካል መኖር ብቻውን ኖሯል አያስብልም ነው ነገሩ፡፡ ህያው የሚያደርገን ራእይና የመኖር ዓላማ እንጂ ቆሞ መሄድ አይደለም፡፡

ቆሞ ለመሄድ በአራት እግር ሆነ እንጂ አህያም ይሄዳል፡፡ አህያ ግን የሰውን ስራ ከማቅለሉ ውጪ የራሱ ራዕይ የለውም፡፡ ስለሌለውም የሌሎች ባሪያ ሆኖ ይኖራል፡፡

በሰው ራእይና ዓላማ የለሽ ህይወት ህይወት ሳይሆን ሞት ነው፡፡ ዓላማ አልባው ሰውም ለመቀበር ነፍሱ ከስጋው እስክትነጠል ይጠበቃል እንጂ ሙትማ ሙት ነው፡፡

ሰውን ህያው የሚያደርገው ህልሙ ነው የሚሉ ይመስላሉ ፀሐፊው፡፡ ልክ ነው! ዓላማ ያለው ሰው መሆንና በዓላማው የሚፀና ሰው መሆን ሁለት የስኬት ቁልፎች ናቸው፡፡

ስኬታማ ሰዎች ባለራዕይ ናቸው፡፡ ለራዕያቸውም ታማኝና ፅኑ ናቸው፡፡ ለፈተናም ሆነ ለየትኛውም ነገር በቀላሉ እጅ አይሰጡም፡፡ እጅ አለመስጠታቸው የህያውነታቸው ምልክት፣ የስኬታቸው ጠቋሚ ነው፡፡

ከዓላማ ውጪ የሚኖር ህይወት ከህይወት አይቆጠርም፡፡ ዓላማ ቢስ ወይም ከባለራዕይነት ወደ ዓላማ የለሽነት የመጣ ሰው ኖሯል ለማለት ከባድ ነው።

ምንጭ፦ “25 የስኬት ቁልፎች” የተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ

መልካም ቀን!
655 viewsedited  07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 10:08:27 ጠቃሚ ምክሮች

1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡

3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

ምንጭ ማህበራዊ ሚዲያ

መልካም ቀን!
698 views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 10:16:53
ነገሮች የማይቻሉ እንደሆኑ ፣ ማሰብ ስንጀምር ፣ አእምሮአችን የተለያዩ ገደቦች እንዳሉብን ፣ በማስረጃ ሊያቀርብልን ይሞክራል ።

በራስ አለመተማመን ፣ ውስጣዊ አቅማችንን አውጥተን እንዳንጠቀም ፣ በፍርሐት እና በጥርጣሬ ታስረን አንድ ቦታ እንድንወሰን ያደርገናል ።

ከአሰብንበት እንድንደርስ ፣ ፍርሐትን እናስፈራራው ፣ አቅም እንደሌለው እንንገረው ። በቃ !!!

መልካም ቀን
718 views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 09:03:00 ሰዎች ከገንዘብ ችግር ጋር የሚታገሉበት ዋነኛው ምክንያት ብዙ አመታትን በት/ቤት ሲያሳልፉ ስለ ገንዘብ እና ኢንቨስትመንት ምንም ባለማወቃቸው ነው። ...ሰዎች ገንዘብ ለማግኘት መስራትን ይማራሉ… ነገር ግን ገንዘብ ለእነሱ እንዴት ሊሰራላቸው እንደሚችል በጭራሽ አይማሩም።’’
.....ሮበርት ኪዮሳኪ

‘Rich Dad Poor Dad’- ሀብታም አባት፤ ደሃ አባት’ እስካሁን ከተፃፉ በጣም እውቅና ካላቸውና ምርጥ የራስ አገዝ (Self-help) መጻሕፍት አንዱ ነው። የተጻፈው ታዋቂ ባለሀብት በሆነው ሮበርት ኪዮሳኪ ሲሆን ሰዎች ስለ ገንዘብ እውቀትን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ እና ለገንዘብ ሳይጨነቁ ህይወትን እንዴት እንደሚመሩ ለማሳወቅ ነው። የገንዘብ ነፃነትን ማግኘት ለሚፈሹ ሁሉ የተፃፈ ነው።

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ደራሲው በወጣትነቱ ያለፈበትን ታሪክ ይተርካል። ሁለት አባቶች እንዳሉት ይጠቅሳል፤ አባቱ እና የጓደኛው አባት። አባቱ ፒኤች.ዲ. (PhD) ያለው አስተማሪ ነገር ግን የገንዘብ ችግር ጋር እየታገለ የነበረ ሲሆን የጓደኛው አባት ደግሞ ከመደበኛ ትምህርት ጋር በተያያዘ ጥሩ ውጤት ያልነበረው እና ትምህርቱን አቋርጦ የነበረ ቢሆንም ሀብታምና የገንዘብ ነፃነት ያለው ነበር። እናም ደራሲው በመፅሃፉ አባቱን "ድሃ አባት" እና የጓደኛውን አባት "ሀብታም አባት" ሲል ይጠራቸዋል።

ይህ ታሪክ የሚያጠነጥነውም "ሀብታም አባቱ" በቀን 8 ሰዓት በሳምንት 5 ቀናት ማሳለፍ የሚጠበቅበትን መደበኛ ሥራ ከመስራት ይልቅ ቀጣይነት ያለው ገቢን ሊያስገኝለት የሚችል የግል ቢዝነስ በመገንባት የገንዘብ ነፃነትን እንዴት ማግኘት እንደሚችል ስለ ገንዘብ እንዴት እንዳስተማረው ነው።

ይህ መጽሐፍ ስለ ገንዘብ እና ገንዘብ እንዴት ማግኘት እንደምትችሉ ያላችሁን አመለካከት ሊለውጥላችሁ የሚችል፤ ስለ ገንዘብ ያላችሁን እምነት እና ግንዛቤ የሚፈትን እና ለምን አንዳንድ ሰዎች ሀብታም፣ አንዳንዶች ደግሞ ህይወታቸውን ሙሉ ድሆች እንደሚሆኑ የሚያስረዳ ምርጥ መጽሐፍ ነው።

አለፍ ሲልም ደራሲው በዚህ መፅሃፉ የትምህርት ስርዓቱ ተማሪዎች በተለመደ እና ባረጀ መንገድ የሚማሩበት፤ ከግል ስራ ፈጠራና ከቢዝነስ አስተሳሰብ ይልቅ የተቀጣሪነት አስተሳሰብን እንዲያዳብሩ የሚገደዱበት እንደሆነ ደራሲው ይሞግታል።

ባጭሩ የራሱን የግል ቢዝነስ ስርዓት ዘርግቶ ሀብታም ለመሆን የሚፈልግ እና እንደ ሀብታም ማሰብ የሚፈልግ፤ ስለ ገንዘብ፣ ትምህርት እና ዓለም ያለውን አመለካከት ወይም አተያይ መቀየር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህን መጽሐፍ ማንበብ አለበት።

መልካም ቀን!
807 views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ