Get Mystery Box with random crypto!

Master Mind Group

የቴሌግራም ቻናል አርማ mastermindgroup — Master Mind Group M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mastermindgroup — Master Mind Group
የሰርጥ አድራሻ: @mastermindgroup
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.71K
የሰርጥ መግለጫ

✍በህይወትዎ ምን ማሳከት ይፈልጋሉ? ቀንዎን በስኬት እና በውጤት ለማሳለፍ።
ውጤታማ የቢዝነስ እና የሽያጭ ሰው ለመሆን።
. የሰራ ፈጠራ ስልጠና
. ለግል ህይወት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና
. የራሰን አቅም በሚገባ ለማወቅ
. ስለ ህልምዎ ፤ ስለ ራዕይዎ ፤ ስለ የህይወት ግብዎ ለማወቅ።
. አነቃቂ እና አስተማሪ የስኬታማ ሰዎች ታሪክ
. በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ እና ውጤታማ ለመሆን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-18 09:02:30
646 views06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 10:05:58 የስኬት ሚስጢር!

በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ሶቅራጥስን የስኬት ምስጢር ምን እንደሆነ ይጠይቀዋል። ሶቅራጥስ ከወጣቱ ጋር በነጋታው ጠዋት ከወንዝ ዳርቻ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዘ።

በነጋታው ሁለቱም እየተራመዱ ወደ ወንዙ ገቡ። ውሀው አንገታቸው ላይ ሲደርስ በድንገት ሶቅራጠስ ልጁን ጎትቶ ውሀው ውስጥ ደፈቀው። ልጁ ለመውጣት ቢታገልም ጉልበቱ ከሶቅራጥስ ጋር ሊመጣጠን ስላልቻለ ጥረቱ አልተሳካለትም።

በመጨረሻ ወጣቱ ፊቱ ወደ ሰማያዊነት መቀየር ሲጀምር ለቀቀው። ልጁ አየር ስቦ ከተረጋጋ በኋላ ሶቅራጥስ ጥያቄውን አቀረበለት "ለመሆኑ ውሀ ውስጥ እያለህ ከምንም ነገር በላይ አስፈልጎህ የነበረው ነገር ምንድነው?" ልጁ ምንም ሳያመነታ "አየር" ብሎ መለሰ።

"የስኬትም ሚስጢር ይሄ ነው፤ ልክ አየር የፈለከውን ያህል ስኬትንም ፈልገውና ታገኘዋለህ፤ ሌላ ሚስጥር የለውም" ብሎ መለሰለት።

አንተም ይህን ግሩፕ የተቀላቀልከውም ስለ ስኬት ለማወቅ/ለመማር ፍላጎት ስላለህ ነው!

ያወከውን ነገር ታስባለህ፤ ያሰብከውን ትተገብራለህ!

ስኬት ማለት ደግሞ ያሰብከውን ወደ ተግባር መቀየር እና በውጤቱ ደስተኛ መሆን ማለት ነው።

"ያለህበት አለም የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን የሌሎችን የስኬት ጉዞ ካነበብክ ለስኬት የሚያበቃህን እምነት መፍጠር ትችላለህ!"

--- አንቶኒ ሮቢንስ

መልካም ቀን!
763 views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 07:44:36 #ስኬታማ_መሆን_ከፈለግክ_መተው_ያሉብህ_5_ነገሮች

#ሁልጊዜ_ፍጹምነት_ላይ_ለመድረስ_የምታደርገውን_መውተርተር_አቁም - ፍጹምነት ይሉት ነገር በየትኛውም የሕይወትህ ክፍል ውስጥ ስለሌለ በከንቱ አትድከም፤ ፍጹምነት የመጨረሻው ደረጃ ነው፡፡ አዲስ ሥራ ለመጀመርም ይሁን የምትጠላውን ሥራህን ለመልቀቅ ወይም የእድሜ ልክ ምኞትህ የሆነውን ጉዞህን ለማድረግ የምትጠብቀው ፍጹም የሚባል ጊዜ የለም፡፡ ፍጹምነትን ትተህ አሁኑኑ ማድረግ መጀመር አለብህ፡፡ ውድቀትን ፍራቻ ስኬት ላይ ከመድረስ ወደ ኋላ እንዲያስቀርህ አትፍቀድለት፡፡

#ይሆናል_የሚል_ተስፋን_ተው - በየትኛውም የሕይወት ክፍልህ ላይ ስኬትን መቀዳጀት ከፈለግክ ዕቅድ ልታወጣለት ይገባል፡፡ በራሱ ይሆናል በሚል ዝም ብለህ ተቀምጠህ ተስፋ በማድረግ የሚጨበጥ ነገር አታመጣም፡፡ የራስህ ሕይወት ፈጣሪው ራስህ ነህ፡፡ ይህ ማለት የየእለቱ ፣ የየሳምንቱ እና የየወሩ እቅድ ፈጣሪው አንተ ነህ፡፡

#በትንሹ_መጫወት_አቁም - በትንሹ መጫወት ትተህ በትልቁ ማሰብ ጀምር፡፡ ትልልቅ ግቦች እና ሕልሞች ለብዙ ሰዎች እብደት ይመስላቸዋል፤ በእርግጥ ሰዎች ሕልሞችህን ሊያጣጥሉብህ እና ሊጠራጠሩህ ይችላሉ፤ ታዲያ አንተ ምን አግብቶህ! በራስህ ላይ የተሰላ ኪሳራን ለመውሰድ ካልደፈርክ ሕልምህ አብሮህ ይሞታል፡፡ ከሀሳብህ አልፈው በፍጹም ወደ ገሃድ አይመጡም፡፡ ዓለምም ካንተ ልትጠቀም የምትችለውን ያህል አትጠቀምም፡፡ ሌሎችን ለመማረክ የምታደርገውን ሙከራ ትተህ ትልቅ ስኬትን ለመቀዳጀት ወስን!

#ሰበቦችህን_ተው - ስኬትን መቀዳጀት ከፈለግክ ሰበቦችን መተው አለብህ፡፡ በሕይወትህ ላይ ለሚገጥሙህ መልካምም ሆነ መጥፎም አጋጣሚዎች ሁሉ ራስህን ተጠያቂ ማድረግ ጀምር፡፡

#ስኬት_በአንድ_ለሊት_ይመጣል_የሚል_እምነትህን_ተው - በአንድ ለሊት የሚመጣ ስኬት አልተፈጠረም፤ አባባል ነው፡፡ የአንድ ለሊት ስኬት የሚመጣው ከዓመታት ያለመታከትና ሕልምን ከመከተል ጥረት በኋላ ነው፡፡ ሎተሪ ለማሸነፍ ሳይሆን ግብህ ላይ ለመድረስ በየቀኑ የምታደርገውን መሻሻል ፈጽሞ አታቋርጥ፡፡

#አስታውስ ስኬት ማለት ሁልጊዜ በሕይወትህ ላይ አንድ ነገር እየጨመሩ መሄድ ማለት ብቻ ሳይሆን፣ አንዳንድ ነገሮችን መተውም ጭምር እንዳለብህ ራስን ማስገንዘብ እና ስርዓት ማስያዝ መሆኑን ማወቅም ነው፡፡ ስኬታማ ልማዶችን ገንባ እና ዙሪያህን በአሸናፊዎች ክበብ!!!

መልካም ቀን!
799 views04:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 08:27:20
የገንዘብ ወሳኝነት!

ይህንን ጽሑፍ ከማንበባችሁ በፊት እስቲ ለአፍታ አይናችሁን ጨፈን አድርጉና በአሁኑ ጊዜ በግል ሕይወታችሁና በቤተሰባችሁ ዙሪያ ያሉትን ቢያንስ አምስት መቅረፍ የምትፈልጓቸውን ችግሮች አስቧቸው፡፡ አብዛኛዎቹ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከገንዘብ ገር ይገናኛሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ እንደዚያ ከሆነ የሚከተሉትን ተያያዥ ሃሳቦች አንብቧቸው፡፡

• የራሳችንንና የቤተሰባችንን የኑሮ ችግር ለመፍታት ገንዘብ እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ አብዛኛው የኑሯችን ችግር ከገንዘብ እጦት ጋር ስለሚያያዝ ማለት ነው፡፡

• ገንዘብን ለማግኘት ደግሞ የሌሎችን ሰዎች ችግር መፍታት የግድ ነው፡፡ ሰዎች ገንዘብን የሚከፍሉን ለምንፈታላቸው ችግር ስለሆነ ማለት ነው፡፡

• የሰዎችን ችግር ለመፍታት በቅድሚ ሰዎቹ ችግራቸው ምን እንደሆነ እንዲያውቁ ማድረግ የግድ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ትግል እንዳለባቸው እንጂ ችግራቸው ምን እንደሆነ በቅጡ ስለማያውቁት ማለት ነው፡፡

• የሰዎችን ችግር በመፍታት ተሽሎ ለመገኘት ራሳችንን ካለማቋረጥ ማሻሻል ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ራሳቸውን በየቀኑ በማሻሻል የተሻለ የመፍትሄ መንገድ ይዘው የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎቻችን ብዙ ሰለሆኑ ማለት ነው፡፡

ለሰዎች የምንፈታው ችግር በበዛ ቁጥር የምናስገባው የገንዘብ መጠን ይጨምራል፡፡ የምናስገባው የገንዘብ መጠን በጨመረ ቁጥር የግላችንና የቤተባችንን የኑሮ ችግር ለሚፈቱልን ሰዎች ከፍለን የሚተርፍን ከበቂ በላይ ገንዘብ ማግኘት እንጀምራለን፡፡

እዚህ ላይ ነው ገንዘብን በጤናማ መንገድ የማግኘትና በትክክለኛው መንገድ የመጠቀም አስፈላጊነት ያለው፡፡

መልካም ቀን!
830 views05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 10:03:32 1. በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ አዲስ ሰርተኸው የማታውቀው ስራ ለመስራት መፍቀድ ይኖርብሀል ፡፡
---ቶማስ ጄፈርሰን

2. ትክክለኛ ሕይወት የሚጀምረው የምቾት ቀጠና ሲያልቅ ነው ፡፡
---ዶናልድ

3. አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው ፡፡
---ኢማም አሊ

4. በምድር ላይ ትልቁ አስደሳች ነገር ሰዎች አትችልም ያሉህን ሰርተህ ማሳየትህ ነው ፡፡
---ዋልተር_ባግሆት

5. ህልምህን ለመፈፀም ብዙ ጊዜ በመውሰዱ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጊዜ ስለሚበር አርቀህ ያየኸው ህልም በፍጥነት መፈፀሙ አይቀርም ፡፡
--አርል ኒተንጋል

6. ሰዎች በምታቅደው እቅድ ካልሳቁ ወይም ካልተገረሙ እቅድህ ትንሽ ነው ማለት ነው ፡፡
---አዚም ፕሪሚጂ

7. ደስተኛ የሆነ ሕይወት ለመኖር ከፈለክ ከሁኔታና ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከአላማና እቅድህ ጋር ተጣበቅ ፡፡
---አልበርት አንስታይን

8. አንተ የምርጫህ ውጤት እንጂ በአንተ ላይ የሚደርሱት ነገሮች ውጤት አይደለህም ፡፡
---ካርል ጉስታቭ

9. እስካልቆምክ ድረስ በምንም ዝግታ ብትጓዝ መድረስህ አይቀርም ፡፡
---ኮንፊሺየስ

10. ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሰራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሰራተኛ ይበለጣል ፡፡
---ቲም ኖትኪ

11. ከውድቀት ይልቅ ጥርጣሬ የነገ ህልምን ይገላል ፡፡
---ሱዚ ካስም

12. እውቀት ብቻ አይበቃም ተግባራዊ ካልተደረገ በስተቀር ፣ ፍቃደኛነት ብቻ አይበቃም ካልተሰራ በስተቀር ፡፡
---ብሩስ ሊ

13. የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ምናለ ምናለ ከአመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡
---ካረን ላንብ

14. .ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው ፡፡
---ሮቢን ሻርማ

15. መተንፈስ እንደምትፈልግ ያህል ለስኬታማ ሕይወት ጥልቅ ፍላጎት ካለህ ይሳካልሀል ፡፡
---ኤሪክ ቶማስ

16. 99% የሚሆኑ ሰዎች ሀሳብህን ከተጠራጠሩህ ፣ እጅጉን ስተሀል አልያም ታሪክ ልትሰራ ነው ፡፡
---ስኮት ቤልስካይ
900 views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 10:03:28
736 views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ