Get Mystery Box with random crypto!

Master Mind Group

የቴሌግራም ቻናል አርማ mastermindgroup — Master Mind Group M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mastermindgroup — Master Mind Group
የሰርጥ አድራሻ: @mastermindgroup
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.71K
የሰርጥ መግለጫ

✍በህይወትዎ ምን ማሳከት ይፈልጋሉ? ቀንዎን በስኬት እና በውጤት ለማሳለፍ።
ውጤታማ የቢዝነስ እና የሽያጭ ሰው ለመሆን።
. የሰራ ፈጠራ ስልጠና
. ለግል ህይወት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና
. የራሰን አቅም በሚገባ ለማወቅ
. ስለ ህልምዎ ፤ ስለ ራዕይዎ ፤ ስለ የህይወት ግብዎ ለማወቅ።
. አነቃቂ እና አስተማሪ የስኬታማ ሰዎች ታሪክ
. በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ እና ውጤታማ ለመሆን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 10:08:32
ለራስ ዋጋ መስጠጥ!

አስደማሚ ሂወት ለመኖር አንዱ ወሳኝ ነገር ለራሳችን የምንሰጠው ዋጋ ነው። ብዙዎች ግን ሰዎች ናቹህ ብለው በወሰኑናቸው ልኬት ነው የሚኖሩት ሰዎች በወሰኑናቸው የማድረግ፣ የእምነት፣ የተስፋ፣ የአልችልም ባይነት አቅም ነው። ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ሂወት አስደማሚ ሂወት ሳይሆን አስቸጋሪ ሂወት እንድንኖር ነው የሚያደርገን። እንቁላልም እኮ በሌላ ሀይል ከውጭ ሲሰበር ሳይሆን ጊዜውን ጠብቆ ከውስጡ በራሱ ጊዜ ሲሰበር ነው ሂወት ያለው ጫጩት የሚኖረው።

እናም እልሀለው ወዳጄ የራስህን ዋጋ ራስህ ተምነው ስተምነውም ደሞ ዙሪያህ ባለው የውስንነት አቅም ሳይሆን ውስጥህ ባለው እምቅ አቅም ይሁን።

መልካም ቀን!
301 views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:17:23 የሰኬት አንድ አራተኛው!

የስኬት አንድ አራተኛው ዓላማን ማወቅ ነው!

የስኬት ሌላኛው አንድ አራተኛ ዓላማችን ላይ እንደምንደርስ ማመን ነው!

የስኬት ተጨማሪው አንድ አራተኛ እርምጃ መውሰድ ነው!

የስኬት የመጨረሻውና ሙሉ የሚያደርገው አንድ አራተኛ የጀመሩትን እርምጃ በፍጹም አለማቆም ነው!

መልካም ቀን
311 views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:29:09 𝟎𝟕 𝐏𝐨𝐰𝐞𝐫𝐟𝐮𝐥 𝐋𝐞𝐬𝐬𝐨𝐧𝐬 𝐅𝐫𝐨𝐦 𝐓𝐡𝐞 𝐁𝐨𝐨𝐤 "𝐓𝐡𝐞 𝐑𝐢𝐜𝐡𝐞𝐬𝐭 𝐌𝐚𝐧 𝐢𝐧 𝐁𝐚𝐛𝐲𝐥𝐨𝐧"

𝟏. 𝐏𝐚𝐲 𝐲𝐨𝐮𝐫𝐬𝐞𝐥𝐟 𝐟𝐢𝐫𝐬𝐭 𝐰𝐢𝐭𝐡 𝟏𝟎% 𝐨𝐟 𝐲𝐨𝐮𝐫 𝐢𝐧𝐜𝐨𝐦𝐞.
You will adjust your budget to fit your means within the other 90%.

2. Control unnecessary expenses by controlling your desires.

Desires grow when there is a chance of them being fulfilled. Study your habits and eliminate any unnecessary expenses.

3. Make your money work for you by investing your savings.

Invest the profit from your investments to grow your wealth even quicker.

4. Make safe investment decisions to prevent financial ruin. Your money can't work for you if you lose it.

Do your best to never lose money.

5. Own a home if it means you can save on rent.

If you can rent out rooms to lower your living expenses, do it.

6. There will be a day where you can no longer work and earn.

Prepare for retirement from an early age. The earlier, the better.

7. Increase your ability to earn more money by amassing skills.

It is the burden of all men to gain the confidence needed to achieve his desires.

Have a great day!
447 viewsedited  07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:19:42
494 views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:19:37
በመጠበቅ ጊዜያችሁን አታባክኑ!

• ደስተኛ ለመሆን ሰዎች በሚያሳይዋችሁ ሁኔታ ደስተኛ እስከሚያያደርጓችሁ አትጠብቁ፡፡ ከማንም ሰው ውጪ ደስተኛ የመሆን ብቃት አላችሁ፡፡

• ችግራችሁን ለማሸነፍ ችግራችሁን ሰዎች እስኪፈቱላችሁ አትጠብቁ፡፡ በመጀመሪያ ችግራችሁን ለመፍታት በራሳችሁ የመንቀሳቀስ ብቃት አላችሁ፡፡

• ሙሉ ሰው ለመሆን በሰዎች ተቀባይነት እስከምታገኙ አትጠብቁ፡፡ ሰዎች ቢቀበሏችሁም ሆነ ባይቀበሏችሁም ሙሉ ሰው ናችሁ፡፡

• የተሟላ ኑሮ ለመኖር ሁሉም ነገር እስኪሟላ አትጠብቁ፡፡ ነገር ሞላም አልሞላም ከዚያ ጋር ባልተነካካ ሁኔታ ከፈጣሪ ጋር ሙሉ ሰው ናችሁ፡፡

• ውስጣችሁ እንዲያርፍ ያሰባችሁበት ዓላማ ላይ እስከምትደርሱ አትጠብቁ፡፡ ከጅማሬው አርፋችሁና በጉዞው እየተደሰታችሁ ወደ ዓላማችሁ የመገስገስ ብቃት አላችሁ፡፡

ሕይወት ሂደት እንጂ የአንድ ቀን ክስተት አይደለችም!

መልካም ቀን!
483 views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 10:29:26
“ሁለቱ ክህሎቶች”

ሁለት አይነት ክህሎቶች አሉ፡- አንደኛው የሞያ ክህሎት ሲሆነ፣ ሌላኛው ግን ማሕበራዊ ክህሎት ነው፡፡ የመጀመሪያው ስራን በስኬታማነት እንድንሰራ ሲያደርገን፣ ሁለተኛው ግን ማሕበራዊ ግንኙታችን የሰመረ እንዲሆን ያግዘናል፡፡ ማንኛውም የሞያ ክህሎት ከማሕበራዊ ክህሎት ውጪ ብዙ ርቀት አያስኬደንም፡፡

በትምህርት ቤት ወይም በልምድ የተማርነው ሞያ-ነክ ክህሎት የስኬታችነን 10 በመቶ ሲይዝ፣ በማሕበራዊ ግንኙነት ጥበብ የምናገኘው ክህሎቶ ደግሞ የስኬታችንን 90 መቶ ያዋጣል፡፡

መጽሐፉን በመግዛት የዛሬ ንባባችሁ አድርጉ! እደጉ!

(መጽሐፉን ለማግኘት:- 0911 47 51 96

መልካም ቀን!
523 views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:30:57
316 views05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:30:56 "ዛሬ ሕይወቴን በአዎንታዊ ማረጋገጫ እያነጽኩ ነው"

ፈጣሪ አለምን የፈጠረው በቃሉ ነው። ቃል ህይወት ነው።
መጽሐፍ እንደሚል ሰው የአፉን ፍሬ ይበላል። ቃል ዘር ነው። መልካሙን መዝራት አረም መዝራትም ምርጫ ነው።
አዎንታዊ ማረጋገጫ ስለ ራሳችን ፣ ስለ ሰው፣ ስለ አለም ፥ ስለ ህይወት ያለንን እምነት፣ አመለካካት፣ እይታ ለማቅናት ሁነኛ መንገድ ነው። በአዎንታዊ ማረጋገጫ ልምድን እናዳብራል የውስጥ አእምሯችንን እናንጻለን። በዚህም ግባችን እናሳካለን።
አዎንታዊ ማረጋገጫችን ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን
* መቀየር የምንፈልገው የህይወት ክፍል ላይ ይበልጥ እናተኩር
* ሊሳካ ይችላል ብለን የምናምነው ቢያንስ አውንታዊ ግብ ላይ እናተኩር
*አሉታዊ ሃሳቦችን እና ስሜቶችን እና የውስጥ ንግግሮች በአዎንታዊ እንተካ
* አዎንታዊ ማረጋገጫችን በአሁን ጊዜ አረፍተነገር ይጻፍ
*በጥሩ ስሜት እንበለው ( አዎንታዊ ማረጋገጫችንን ስንል ስሜት ካጣንበት ወይም ምቾት ከነሳን ቃላቶቹን በማሻሻል አዎንታዊ ስሜት እንፍጠርለት )
* አዎንታዊ ማረጋገጫን ከበምናብ ማየት እና ግልጽ ግብ ማስቀመጥ ቢጠመር ይበልጥ ውጤታማ ይሆናል።

ቃል ህይወት ነው

እስቲ ይሄን እንበል

ዛሬ ህይወቴን በአዎንታዊ ማረጋገጫ አያነጽኩ ነው

መልካም ቀን!
311 views05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 15:27:16 ስኬታማ ሰዎች ያሏቸው 5 ነገሮች

1. ጠንክረው ይሰራሉ

ዛሬ ላይ ጠንክረው ለመስራት ቁርጠኛ ናቸው የዛሬ ጠንካራ ስራ እና ውሳኔ ለነገ የተሻለ ህይወት መሰረት ነው። ስኬታማ ሰዎች ጠንካራ ሰራተኛች ናቸው።

2. በፍፁም አያቋርጡም

ከባድ ና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢገጥሟቸውም በፍፁም አያቋርጡም ።
ስኬት በመጀመር ብቻ ሳይሆን በመጨረስ ውስጥ ናት!!

3. መስዋዕት ይከፍላሉ

የስኬት ጉዞ ቀላል ላይሆን ይችላል ብዙ ጥልፍልፎሽ ና አስቸጋሪ አቀበቶች፣ ውጣ ውረድ ይኖረዋ። ስኬታማ ለመሆን ከምቾት ቀጠና ወጥቶ መስዋዕት መክፈል ግድ ይላል። ስኬት በቀላሉ አትገኝም።  ስኬታማ ሰዎች የሚከፈለውን ዋጋ ( መስዋዕት) ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።

መስዋዕት ከፍለህ ወጥረህ ካልሰራህ ህይውት ጀርባዋን ታዞርብሃለች። የስኬት ሚዛኗ የሚያጋድለው መስዋዕት ከፍለው ለሚተጉ ነው። ነፃ ቁርስ የለም!!!

4. አዕምሯቸውን ይመግባሉ

ስጋችን ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ አዕምራችንም መመገብ አለበት "እውቀት" ! ማንበብ፣ መማር ... አስፈላጊ ነው። ስኬታማ ሰዎች ሁሌም ያነባሉ፤ መሪዎች ሁሌም አንባቢዎች ናቸው።

5. ኃላፊነት ይወስዳሉ

ስኬታማ ሰዎ በሚሰሩት ስራ ሁሉ ሃላፊነት ይወስዳሉ፣ ከማማረር ይልቅ መፍተሔ ፣ ከመውቀስ ይልቅ ማመስገን መለያቸው ነው። ለችግሮች መፍትሔ ፈላጊ እንጂ ችግር ፈጣሪ አይደሉም።

እርስዎስ ስኬታማ ለመሆን ምን እያደረጉ ነው ?

መልካም ቀን
445 views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 10:06:37
518 views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ