Get Mystery Box with random crypto!

በህይወት ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ እንዲመጣ ፡ ከፈለግህ ፡ ቀላሉን ፡ መንገድ ፡ አትምረጥ። ቀላሉ ፡ | Master Mind Group

በህይወት ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ እንዲመጣ ፡ ከፈለግህ ፡ ቀላሉን ፡ መንገድ ፡ አትምረጥ። ቀላሉ ፡ መንገድ ፡ የተለመደ ፡ ቦታ ፡ የሚያደርስ ፡ ነው። የተለመደ ፡ ውጤት ፡ የሚያስገኝ ፡ ነው። ቀላሉ ፡ መንገድ ፡ እርካታ ፡ የሌለበት ፤ ሌሎች ፡ ስለሆኑት ፡ የምትሆነውና ፡ ስለኖሩት ፡ የምትኖረው ፡ ነው።
የኔ ፡ ምትለውን ፡ ውጤት ፡ አይሰጥህም።
ከባዱ ፡ መንገድ ፡ ግን ፡ አሰልቺ ፣ የሚያቆስል ፣ የሚያደክምና ፡ የሚያሰቃይ ፡ ሊሆን ፡ ይችላል ፡ ነገር ፡ ግን ፡ ጣፋጭ ፡ እርካታንና ፡ ስኬትን ፡ ያጎናጽፍሃል።
ተስፋ ፡ ሳትቆርጥ ፡ ሂደቱን ፡ ከተቀበልህ ፡ ውጤታማ ፡ ትሆናለህ።

ብሩክ የሺጥላ

መልካም ቀን!