Get Mystery Box with random crypto!

ሰዎች ከገንዘብ ችግር ጋር የሚታገሉበት ዋነኛው ምክንያት ብዙ አመታትን በት/ቤት ሲያሳልፉ ስለ | Master Mind Group

ሰዎች ከገንዘብ ችግር ጋር የሚታገሉበት ዋነኛው ምክንያት ብዙ አመታትን በት/ቤት ሲያሳልፉ ስለ ገንዘብ እና ኢንቨስትመንት ምንም ባለማወቃቸው ነው። ...ሰዎች ገንዘብ ለማግኘት መስራትን ይማራሉ… ነገር ግን ገንዘብ ለእነሱ እንዴት ሊሰራላቸው እንደሚችል በጭራሽ አይማሩም።’’
.....ሮበርት ኪዮሳኪ

‘Rich Dad Poor Dad’- ሀብታም አባት፤ ደሃ አባት’ እስካሁን ከተፃፉ በጣም እውቅና ካላቸውና ምርጥ የራስ አገዝ (Self-help) መጻሕፍት አንዱ ነው። የተጻፈው ታዋቂ ባለሀብት በሆነው ሮበርት ኪዮሳኪ ሲሆን ሰዎች ስለ ገንዘብ እውቀትን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ እና ለገንዘብ ሳይጨነቁ ህይወትን እንዴት እንደሚመሩ ለማሳወቅ ነው። የገንዘብ ነፃነትን ማግኘት ለሚፈሹ ሁሉ የተፃፈ ነው።

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ደራሲው በወጣትነቱ ያለፈበትን ታሪክ ይተርካል። ሁለት አባቶች እንዳሉት ይጠቅሳል፤ አባቱ እና የጓደኛው አባት። አባቱ ፒኤች.ዲ. (PhD) ያለው አስተማሪ ነገር ግን የገንዘብ ችግር ጋር እየታገለ የነበረ ሲሆን የጓደኛው አባት ደግሞ ከመደበኛ ትምህርት ጋር በተያያዘ ጥሩ ውጤት ያልነበረው እና ትምህርቱን አቋርጦ የነበረ ቢሆንም ሀብታምና የገንዘብ ነፃነት ያለው ነበር። እናም ደራሲው በመፅሃፉ አባቱን "ድሃ አባት" እና የጓደኛውን አባት "ሀብታም አባት" ሲል ይጠራቸዋል።

ይህ ታሪክ የሚያጠነጥነውም "ሀብታም አባቱ" በቀን 8 ሰዓት በሳምንት 5 ቀናት ማሳለፍ የሚጠበቅበትን መደበኛ ሥራ ከመስራት ይልቅ ቀጣይነት ያለው ገቢን ሊያስገኝለት የሚችል የግል ቢዝነስ በመገንባት የገንዘብ ነፃነትን እንዴት ማግኘት እንደሚችል ስለ ገንዘብ እንዴት እንዳስተማረው ነው።

ይህ መጽሐፍ ስለ ገንዘብ እና ገንዘብ እንዴት ማግኘት እንደምትችሉ ያላችሁን አመለካከት ሊለውጥላችሁ የሚችል፤ ስለ ገንዘብ ያላችሁን እምነት እና ግንዛቤ የሚፈትን እና ለምን አንዳንድ ሰዎች ሀብታም፣ አንዳንዶች ደግሞ ህይወታቸውን ሙሉ ድሆች እንደሚሆኑ የሚያስረዳ ምርጥ መጽሐፍ ነው።

አለፍ ሲልም ደራሲው በዚህ መፅሃፉ የትምህርት ስርዓቱ ተማሪዎች በተለመደ እና ባረጀ መንገድ የሚማሩበት፤ ከግል ስራ ፈጠራና ከቢዝነስ አስተሳሰብ ይልቅ የተቀጣሪነት አስተሳሰብን እንዲያዳብሩ የሚገደዱበት እንደሆነ ደራሲው ይሞግታል።

ባጭሩ የራሱን የግል ቢዝነስ ስርዓት ዘርግቶ ሀብታም ለመሆን የሚፈልግ እና እንደ ሀብታም ማሰብ የሚፈልግ፤ ስለ ገንዘብ፣ ትምህርት እና ዓለም ያለውን አመለካከት ወይም አተያይ መቀየር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህን መጽሐፍ ማንበብ አለበት።

መልካም ቀን!