Get Mystery Box with random crypto!

Lovedface የተወደደ መልክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ lovedface — Lovedface የተወደደ መልክ L
የቴሌግራም ቻናል አርማ lovedface — Lovedface የተወደደ መልክ
የሰርጥ አድራሻ: @lovedface
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.08K
የሰርጥ መግለጫ

ጌታን በማወቅና በክርስቶስ ፍቅር የሆነ ጥልቅ የመንፈስ ቅዱስ ህብረት
@Lovedface @emanuellf

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-29 19:06:35 በፌስቡክ በአማርኛ ቋንቋ በዚህ መከታተል ትችላላችሁ።

https://www.facebook.com/christembassyethiopiapage/videos/1196048844574975
73 views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 17:39:44 በአማርኛ ቋንቋ በዚህ መከታተል ትችላላችሁ። ሜኑ ውስጥ ቋንቋ "Amharic" የሚለውን ምረጡ።

https://healingstreams.tv/live.php?sl=amharic
90 views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 17:18:01 በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀጥታ ስርጭቱ ጀምሯል። በዚህ ከፍታችሁ ተከታተሉ። በአማርኛ ቋንቋ ሼር አደርጋለሁ



95 views14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 09:56:44 ዛሬ ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ በህይወታችሁ ታላቅ ነገር የሚሆንበት የመንፈስ ቅዱስ ህብረትና የፀጋ መካፈል የምታገኙበት እንደሆነ አምኛለሁ። ይህ ያስፈልጋችኋል። በመንፈስ መጠባበቅ ተዘጋጁ!


Watch "የፈውስ ፕሮግራም ከፓስተር ክሪስ ጋር ከሐምሌ 22-24, 2014 Healing Streams with Pastor Chris july 29-31, 2022" on YouTube


126 viewsedited  06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 09:45:01 በትንቢት የጦርነት ዘመቻ ማካሄድ

በድምፅ - ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ
RHAPSODY OF REALITIES

Friday July 29th, 2022
(አርብ - ሐምሌ 22 - 2014)
103 views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 09:45:01 በትንቢት የጦርነት ዘመቻ ማካሄድ

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic)

Friday July 29th, 2022
(አርብ - ሐምሌ 22 - 2014)

════════
ጢሞቴዎስ ልጄ ሆይ፥ አስቀድሞ ስለ አንተ እንደ ተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ፤ (1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡18)

ፓስተር ክሪስ
━━━━━━━━━
በሐዋርያት ሥራ 5፤26 ላይ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል “በዚያን ጊዜ አዛዡ ከሎሌዎች ጋር ሄዶ አመጣቸው፥ በኃይል ግን አይደለም፤ ሕዝቡ እንዳይወግሩአቸው ይፈሩ ነበርና።” ከላይ ከተጠቀሰው ጥቅስ ላይ ሻለቃው አለ፤ እንዲሁም መኮንኖች አሉ። “ካፒቴን” የሚለው ቃል በግሪክ “ስትራቴጎስ” ሲሆን አዛዥ መኮንን ማለት ነው።

ሆኖም “መኮንኖች” የሚለው ቃል «ሁፒሬቴስ» (ግሪክኛ) ሲሆን፣ ይህም በእጃቸው የሚሠሩትን ያመለክታል፤ በሌላ አባባል “ስትራቴጎስ” ማለትም አለቃው ወይም አዛዡ የሚሰጣቸውን ኃላፊነት ወይም መመሪያ የሚያከናውኑ ሰዎች ናቸው። ከዚያም 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3ን ስታነቡ እንዲህ ይላል፣ “እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል።” “ወታደር” የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን “ስትራቲዮተስ” ሲሆን ከ”ስትራቴጎስ” እና ከ”ሁፒሬቴስ” የተለየ ነው። ነገር ግን በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ እንዳነበብነው መልካምን ጦርነት “ትዋጋ” ዘንድ ብሎ ሲናገር ለጦርነት “ስትራቲዮማይ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል። ይህ አባባል በወታደራዊ ዘመቻ ላይ ያለ አንድን አዛዥ ማለትም አንድን የጦር ንድፍ አውጭ ያመለክታል። “ሁፒሬቴስ” ወይም “ስትራቴጎስ” ሳይሆን ስትራቴጂስት ወይም የጦር ስልት አዋቂ ነው!

እንደ “ስትራቲዮተስ” ጠንካራ መሆን ይጠበቅባችኃል፤ እንደ ጥሩ ወታደር። ነገር ግን እንደ “ሁፐሬቴስ” “ጦርነት” ውስጥ በቀጥታ የምትሳተፉ መኮንኖች አይደላችሁም፤ ይልቅ ትንቢትን ተጠቀሙ። ሃሌ ሉያ! የመንፈስ ስልት የሆነውን ትንቢትን ለጦርነት ተጠቀሙ። በትንቢት በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት በኃይል የተሞሉ ቃላትን እያወጃችሁ ነው።

የሕይወታችሁን አቅጣጫ ቅርጽ ለማስያዝና ዕቅድ ለማውጣት ቃሉን ተጠቀሙበት። ቃል መንፈሳዊ ንጥረ ነገር ነው። ለዚህም ነው በመንፈስ ብዙ መፀለያችሁ አስፈላጊ የሆነው። ይህን ስታደርጉ፥ አጋንንትን እና የሕይወትን ተግዳሮቶች የምታሸንፉበትን በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት በአእምሮአችሁ ያለውን ቃላትን ትናገራኛላችሁ።

የእምነት አዋጅ
━━━━━━━━
ከልዕለ ተፈጥሮ በሆነ አቅርቦት፣ በብርታት፣ በችሎታ፣ በጥበብና በእውቀት እየሰራሁ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እግዚአብሔር ለህይወቴ ያለውን አላማ እየፈጸምኩ ነው። በዚህ ዓለም ውስጥ ከክፋት ሁሉ ለዘላለም ተጠብቄአለሁ። የክብር፥ የግዛትና የዘላለም ደስታ ስፍራ በሆነው ሁሉን በሚችል አምላክ ደህንነትና ሰላማዊ መኖሪያ ውስጥ እኖራለሁ፤ በሁኔታዎች ላይ ከክርስቶስ ጋር በመግዛት እኖራለሁ፣ በኢየሱስ ስም። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት:
ትንቢተ ሆሴዕ 14:2;
ዕብራውያን 13:5-6;
መጽሀፈ መክብብ 8:4
━━━━━//━━━━
100 views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 09:00:29
ነገ ከ11:00 ጀምሮ የቀጥታ ስርጭት የፈውስ ፕሮግራም ከፓስተር ክሪስ ጋር። አማኑኤል ሆይ የክንፍህ መዘርጋት የኢትዮጵያንና የምድሪቱን ስፍት ይሞላል! ኦ ሃሌሉያ! "ስሜን ለምትፈሩጨለእናንተ የፅድቅ ፀሀይ ትወጣለች ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል" (ሚል 4:2) ተብሎ የተፃፈው ቃል ይፈፀማል። ለእናንተ የሙሉነት ቀን እንደሚሆን አውቃለሁ። በአማርኛ ቋንቋ የሚተላለፍ ሲሆን ሊንኩን ፕሮግራሙ እንደጀመረ እዚህ አስቀምጣለሁ።

እወዳችኋለሁ. አማኑኤል
147 views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 09:00:24 የአስገዳጅ ፍላጎት ኃይል

RHAPSODY OF REALITIES
በድምፅ - ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ

Thursday July 28th, 2022
(ሐሙስ - ሐምሌ 21 - 2014)
140 views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 09:00:24 የአስገዳጅ ፍላጎት ኃይል

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic)

Thursday July 28th, 2022
(ሐሙስ - ሐምሌ 21 - 2014)

════════
. . .የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። (ያዕቆብ 5፥16)

ፓስተር ክሪስ
━━━━━━━━━
በአሁኑ ጊዜ ያላችሁበት ቦታ ምንም ይሁን ምን ለእናንተ የተዘጋጀ ከፍ ያለ የሕይወት ግዛት አለ።ይሁን እንጂ ይህን የመፈለግ አስገዳጅ ፍላጎት እስካልያዛችሁ ድረስ ወደዚያ አዲስና ከፍ ወዳለ የህይወት ግዛት አትሄዱም ።

በሁኔታቸው ላይ ለውጥ ለማድረግ ባላቸው አስገዳጅ ፍላጎት የተነሳ ሕይወታቸው የተለወጠ ሰዎችን የሚያሳዩ ሁለት ምሳሌዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንመልከት፡፡በእስራኤል ቅድመ ታሪክ መጀመሪያ ዘመን አንዳንዶች በግብጻውያን የአኗኗር ዘይቤ ተመችቷቸው ምናልባትም እግዚአብሔር ለአያት ቅድመ አያቶቻቸው (ለአብርሃም፣ ይስሐቅና ያዕቆብ) ቃል የገባላቸውን ምድር ዘንግተው ሊሆን ይችላል።

ይሁን እንጂ ለባርነት ተገዝተው የግብፃውያን ጅራፍ ቆዳቸውን እስኪያቆስላቸው ድረስ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል አላስታወሱም። እስራኤላውያን በድንገት ለውጥ ለማድረግ ያላቸው ፍላጎት እያደገ ሄደ፤እግዚአብሔርም ጩኸታቸውን ሰምቶ ከባርነት አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲመራቸው ሙሴን ላከ።

በ1ኛ ሳሙኤል 1፡1-21 መጽሐፍ ውስጥ ሐና ስለምትባል አንዲት ሴት ሌላ የሚያነሳሳ ታሪክ አለ።መካን ስለነበረችና ለበርካታ ዓመታት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስለቆየች ልጅ አልወለደችም። ባለቤቷ በጣም ይወዳት ስለነበር ሁኔታዋን መቋቋም የቻለች ይመስል ነበር።ይሁን እንጂ ጣውንትዋ በሁኔታዋ ባበሳጨቻት ጊዜ ነገሮች ወደ እሷ ዞሩ፡፡

በድንገት በጣም አዘነች ታላቅ ሀዘንም ሆነባት።በዚህ ጊዜ ባሏ ሐዘኗን ለመቅረፍ ያደረገው ጥረት ትርጉም የለሽ ነበር፤ ልጅ የመውለድ ፍላጎቷ ከአቅሟ በላይ ሆኖባት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፣“እርስዋም በልብዋ ትመረር ነበር፣በእግዚአብሔር ፊት ጸለየች፣ጽኑ ልቅሶም አለቀሰች፡፡” (1ኛ ሳሙኤል 1፡10)፡፡

በእነዚህ ሁለት ሁኔታዎች ውስጥ ለውጥ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት ከማሳየት የተነሳ የእግዚአብሔር ምላሽ መጣ።ታዲያ ዛሬ ያላችሁበት ሁኔታ እንዲለወጥ ትፈልጋላችሁ?የእግዚአብሔር መንግሥት ኃይል ውጤት እንዲያስገኝላችሁ ትፈልጋላችሁ?ልባችሁ አብዝቶ መፈለግ፤ እናንተም በብርቱ ምኞት መቀጣጠል አለባችሁ።

ይህ በሕይወታችሁ ውስጥ ዘላቂ ለውጥ ለማድረግ ልትወስዷቸው የሚገቡ ቀዳሚ እርምጃዎች ናቸው።በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ እውቀት ለማግኘት "እግዚአብሔር በሚጎበኛችሁ ጊዜ" የተባለውን መጽሐፍ ማንበብ ትችላላችሁ።

ጸሎት
━━━━━━━━
ውድ አባት ሆይ፣ በህይወቴ፣ በአገልግሎቴ፣ በገንዘቤ፣ በንግድና በስራዬ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ጠንካራ መሻትና ልምምድ እንዲኖረኝ ከውስጥ ስለሆነው ብርታት አመሰግናለሁ።ከምንም ነገር በላይ ጽድቅህ አገራትን እንዲሞላ እንዲሁም በእኔ በኩል ዛሬ ብዙዎች ወደከበረው መንግሥትህ እንዲመጡ እሻለሁ፣በኢየሱስ ስም፡፡አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት:
ምሳሌ 23፡18;
መዝሙረ ዳዊት37፡4
━━━━━//━━━━
125 views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 10:40:04 የመዳን ተሸካሚዎች

RHAPSODY OF REALITIES
በድምፅ - ራፕሶዲ ኦፍ ሪያሊቲስ

Wednesday July 27th, 2022
(ረቡዕ - ሐምሌ 20 - 2014)
146 views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ