Get Mystery Box with random crypto!

የአስገዳጅ ፍላጎት ኃይል RHAPSODY OF REALITIES (Amharic) Thursday Jul | Lovedface የተወደደ መልክ

የአስገዳጅ ፍላጎት ኃይል

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic)

Thursday July 28th, 2022
(ሐሙስ - ሐምሌ 21 - 2014)

════════
. . .የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። (ያዕቆብ 5፥16)

ፓስተር ክሪስ
━━━━━━━━━
በአሁኑ ጊዜ ያላችሁበት ቦታ ምንም ይሁን ምን ለእናንተ የተዘጋጀ ከፍ ያለ የሕይወት ግዛት አለ።ይሁን እንጂ ይህን የመፈለግ አስገዳጅ ፍላጎት እስካልያዛችሁ ድረስ ወደዚያ አዲስና ከፍ ወዳለ የህይወት ግዛት አትሄዱም ።

በሁኔታቸው ላይ ለውጥ ለማድረግ ባላቸው አስገዳጅ ፍላጎት የተነሳ ሕይወታቸው የተለወጠ ሰዎችን የሚያሳዩ ሁለት ምሳሌዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንመልከት፡፡በእስራኤል ቅድመ ታሪክ መጀመሪያ ዘመን አንዳንዶች በግብጻውያን የአኗኗር ዘይቤ ተመችቷቸው ምናልባትም እግዚአብሔር ለአያት ቅድመ አያቶቻቸው (ለአብርሃም፣ ይስሐቅና ያዕቆብ) ቃል የገባላቸውን ምድር ዘንግተው ሊሆን ይችላል።

ይሁን እንጂ ለባርነት ተገዝተው የግብፃውያን ጅራፍ ቆዳቸውን እስኪያቆስላቸው ድረስ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል አላስታወሱም። እስራኤላውያን በድንገት ለውጥ ለማድረግ ያላቸው ፍላጎት እያደገ ሄደ፤እግዚአብሔርም ጩኸታቸውን ሰምቶ ከባርነት አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲመራቸው ሙሴን ላከ።

በ1ኛ ሳሙኤል 1፡1-21 መጽሐፍ ውስጥ ሐና ስለምትባል አንዲት ሴት ሌላ የሚያነሳሳ ታሪክ አለ።መካን ስለነበረችና ለበርካታ ዓመታት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ስለቆየች ልጅ አልወለደችም። ባለቤቷ በጣም ይወዳት ስለነበር ሁኔታዋን መቋቋም የቻለች ይመስል ነበር።ይሁን እንጂ ጣውንትዋ በሁኔታዋ ባበሳጨቻት ጊዜ ነገሮች ወደ እሷ ዞሩ፡፡

በድንገት በጣም አዘነች ታላቅ ሀዘንም ሆነባት።በዚህ ጊዜ ባሏ ሐዘኗን ለመቅረፍ ያደረገው ጥረት ትርጉም የለሽ ነበር፤ ልጅ የመውለድ ፍላጎቷ ከአቅሟ በላይ ሆኖባት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፣“እርስዋም በልብዋ ትመረር ነበር፣በእግዚአብሔር ፊት ጸለየች፣ጽኑ ልቅሶም አለቀሰች፡፡” (1ኛ ሳሙኤል 1፡10)፡፡

በእነዚህ ሁለት ሁኔታዎች ውስጥ ለውጥ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት ከማሳየት የተነሳ የእግዚአብሔር ምላሽ መጣ።ታዲያ ዛሬ ያላችሁበት ሁኔታ እንዲለወጥ ትፈልጋላችሁ?የእግዚአብሔር መንግሥት ኃይል ውጤት እንዲያስገኝላችሁ ትፈልጋላችሁ?ልባችሁ አብዝቶ መፈለግ፤ እናንተም በብርቱ ምኞት መቀጣጠል አለባችሁ።

ይህ በሕይወታችሁ ውስጥ ዘላቂ ለውጥ ለማድረግ ልትወስዷቸው የሚገቡ ቀዳሚ እርምጃዎች ናቸው።በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ እውቀት ለማግኘት "እግዚአብሔር በሚጎበኛችሁ ጊዜ" የተባለውን መጽሐፍ ማንበብ ትችላላችሁ።

ጸሎት
━━━━━━━━
ውድ አባት ሆይ፣ በህይወቴ፣ በአገልግሎቴ፣ በገንዘቤ፣ በንግድና በስራዬ ልዕለ ተፈጥሮአዊ ጠንካራ መሻትና ልምምድ እንዲኖረኝ ከውስጥ ስለሆነው ብርታት አመሰግናለሁ።ከምንም ነገር በላይ ጽድቅህ አገራትን እንዲሞላ እንዲሁም በእኔ በኩል ዛሬ ብዙዎች ወደከበረው መንግሥትህ እንዲመጡ እሻለሁ፣በኢየሱስ ስም፡፡አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት:
ምሳሌ 23፡18;
መዝሙረ ዳዊት37፡4
━━━━━//━━━━