Get Mystery Box with random crypto!

ከአበው አንደበት(Sayings of Desert Fathers)

የቴሌግራም ቻናል አርማ theholyfathers — ከአበው አንደበት(Sayings of Desert Fathers)
የቴሌግራም ቻናል አርማ theholyfathers — ከአበው አንደበት(Sayings of Desert Fathers)
የሰርጥ አድራሻ: @theholyfathers
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 999
የሰርጥ መግለጫ

የቅዱሳን አባቶቻችን ትምህርት

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 08:56:11
ሦስታችን አንድ ነን!


በ11ኛው ክፍለ ዘመን ከሦስቱ አባቶች ዘንድ ማነው የሚበልጥ የሚል ጠብ ተነሳ። እኒህ ሦስቱ የተባሉት ፓትርያርኮችና ቅዱሳን ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ናቸው። በቤዛንታይን ማኅበረሰብ ዘንድ በዚህ ጠብ የተነሳ መከፋፈልና መጎሳሰሞች ነገሱ፣ የቅዱሳኑን ትምህርት እየጠቀሱ ይበላሉ ጀመር። ክፍፍላቸውም የተለያዩ መልኮችን እየያዘ ለአራሚ እና ለመካሪ አስቸጋሪ ሆነ። ይኽም ወንድምን ከወንድም፣ ጎረቤትን ከጎረቤት ወዳጆችን ከወዳጆች እየለየ ክርስቲያኖችን የሚከፋፍል ሆነ....ይኽ አይነቱ ነገር ደግሞ የክርስትናን መመሪያ(The Christian Principles) ከሆኑት ሰላምና አንድነት ጋር ይጣረሳል።

በአንድ ወቅት በዘመኑ የነበረው አባ ማውሮፖስ ራእይን አየ...ሦስቱ ቅዱሳንም መጥተው እንዲህ ሲሉት ተመለከተ...

"ሦስታችን አንድ ነን፤ እንደምታዩትም ለፈጣሪ ቅርብ የሆንንና ምንም ሊለየንና ሊያጣላንም አይችልም...በመካከላችን አንደኛም ሁለተኛም የለም...እንግዲህ ተነስና በእኛ ላይ እንዳይከፋፈሉ የሚጣሉትን ንገራቸው። ምክንያቱም በሕይወትም በሞትም ለሰው ሁሉ ሰላምንና አንድነትን ለማምጣት እንጅ ሌላ ፍላጎት አልነበረንም።"

ይኽንንም ከሰሙ በኋላ ብዙዎች መንገዳቸውን ያስተካከሉ አሉ። በዚኽም በዚያ ዘመን የእኒህን ቅዱሳን መታሰቢያ(ዝክር) በአንድ ቀን እንዲውልና ሥዕላቸውም በአንድ እንዲሳል ተደረገ...የከበረች በረከታቸው ትርዳን፣ ትደርብንም!


ዘገየ ዘአስኩ
194 views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 16:38:55 https://t.me/FreeEearnMoneyPay_Bot?start=r0291547823
425 views13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 22:30:12 ግእዝ ቋንቋ በእፀ ሳቤቅ ቲዩብ።።ተከታታይነት ያለው በአጭር ጊዜ ግእዝ መናገር በሚያስችል መልኩ የቀረበ! ።።ክፍል...


1.2K views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 22:23:37 ግእዝ ቋንቋ በእፀ ሳቤቅ ቲዩብ።።ተከታታይነት ያለው በአጭር ጊዜ ግእዝ መናገር በሚያስችል መልኩ የቀረበ! ።።ክፍል...


997 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 22:23:14 https://youtube.com/channel/UCZccU87sFe4V5BnT_GVHxYg



ይኽንን የግዕዝ መማማሪያ የዩቲዩብ ገጽ subscribe በማድረግ ወጣቶችን እናበረታታ
855 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 22:14:38 ከላይ የምታዩትን ግዕዝ መማማርያ የዩቲዩብ ገጽ subscribe በማድረግ ወጣት መንፈሳውያንን እናበረታታ
798 views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-27 21:18:34 Channel name was changed to «ከአበው አንደበት(Sayings of Desert Fathers)»
18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-07 11:50:11 ብሒለ አበው!



1 ‹ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና
አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ
መታገስ ነው።›› /ቅዱስ ስራፕዮን/


2 ‹‹የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው
ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።›› /መጽሐፈ
ምክር/


3 ‹‹አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር
ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት
ያርቀዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/


4 ‹‹ ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን
ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን
እንዳታጣ።›› /ማር ይስሐቅ/


5 ‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር
ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው
ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/


6 ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ
አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ
እንጦንስ/


7 ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን
የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን
ይቻልናል።›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/


8 ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም
ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም
ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች
የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ
ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/


9 ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን
ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ
መቃርስ/


10 ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ
በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ
አርሳንዮስ/


11 ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን
የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ
ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ
እንድርያስ/


12 ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው
ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ
መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።›› /አባ አብርሃም
መፍቀሬ ነዳያን/


13 ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት
የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
ካልዕ/


14 ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ
ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ
የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።›› /ብፁዕ አቡነ
ጎርጎርዮስ ካልዕ/


15 ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ
እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ
አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና
ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።›› /ቅዱስ ይስሐቅ
ሶርያዊ/


16 ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ
እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን
የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።›› /ቅዱስ
እንጦንስ/


በረከተ ቅዱሳን አበው አይለየን።አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
2.0K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ