Get Mystery Box with random crypto!

Orthodox photos

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox_photos — Orthodox photos O
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox_photos — Orthodox photos
የሰርጥ አድራሻ: @orthodox_photos
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.24K
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም ውድ የተዋህዶ ልጆች ይህ ቻናል የተከፈተው
የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ምስሎችን እንዲተላለፉበት ነው።
✞በዚህ ቻናል ላይ የምንለቃቸው
🔸ቤተክርስቲያናዊ ምስሎች ፤
🔸የንግስ በአላት ጥሪዎች
🔸መዝሙሮች
🔸ስብከቶች....

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-20 13:34:39
@Orthodox_photos
542 viewshaile, edited  10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 21:19:15 1 , ኦርቶዶክስ ነኝ የሚልና ማዕተብ ያሰረ በሙሉ ቢያንስ ለ20 ሰው የግዴታ ሼር ያድርግ በሁሉም social media ለተዋህዶ ልጆች ሁሉ መድረስ አለበት። ሀላፊነታችሁን የማትወጡ የተዋህዶ ፀር እናንተ ናችሁ።
2, ልቦና ማስተዋል ያላቹና እንደ አብዛኛው የተዋህዶ ልጆች ቸልተኛ ያሎናችሁ የተዋህዶ ልጆች ደሞ ጦማሩን በአግባቡ አንብቡና አስተዋይ እና ለሀይማኖቱ የሚቀና ሰው የሚደርገውን አድርጉ።
?ማስጠንቀቂያና ማሳሰብያ በምንም ተአምር የተዋህዶ ልጅ ሆኖ ሼር የማያደርግ እንዳይኖር የእውነት ቸልተኞች ሆይ አደራ የኅልውና ጉዳይ ነው በእግዚአብሔር ስም ተይዛችኋል ይህን ባታደርጉ የቤተክርስቲያን ጠላቶቿ ናችሁ !!!
@Orthodox_photos
1.8K viewshaile, 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 21:02:53
@orthodox_photos
1.1K viewshaile, edited  18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 08:11:04
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አርፈዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

የቅዱስነታቸውን ሽኝት በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ተሰብስቦ በሚያስተላልፈው ውሳኔና በሚያወጣው መርሐ ግብር መሰረት የሚፈጸም መሆኑን የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው በሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበሩ መገለፁ ይታወሳል።

@orthodox_photos
2.2K viewshaile, 05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 20:50:42
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በ ገርጂ ቅ/ጊዮርጊስ
@Orthodox_photos
Share
1.7K viewshaile, edited  17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 19:38:44
Share argu
@orthodox_photos
1.7K viewshaile, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 19:35:58 ዐቢይ ጾም

ዐቢይ ለምን ተባለ ቢሉ ‹‹ዐበየ›› ማለት ከፍ አለ ማለት ሲሆን ከዚህም ግስ አቢይ የሚለው ቅጽል ይገኛል፡፡ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት፡-

ሀ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም
ስለሆነ
ለ. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ
ሐ. ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም
➛ ትዕቢት
➛ ስስት
➛ ፍቅረ ነዋይ ድል የተመቱበት ስለሆነ ነው፡፡

በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፡-

1. ዘወረደ
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡

2. ቅድስት
ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡

3. ምኩራብ
ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ይህች ዕለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ምኩራብ ማለት የቤተ አይሁዳውያን የጸሎት ቤት ነው፡፡

4. መጻጉዕ
ይህ የአራተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ እውራንን ማብራቱ ለምጻምን ማንጻቱ ሽባዎችን መተርተሩ የሚያነሳ መዝሙር የሚዘመርበት እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ድንቅ ገቢራተ ታምራቶች የሚዘከሩበት ዕለት ነው፡፡

5. ደብረ ዘይት
ይህ የአምስተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚወሳበት ሰንበት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ማለት ወይራ የበዛበት ተራራ ማለት ነው፡፡

6. ገብርኄር
ይህ የስድስተኛው ሳምንት ሰንበት ስያሜ ሲሆን ይህም ዕለት ለጌታው ታማኝና በጎ የሆነው ባርያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ተብሎ እንደተመሰገነ የሚነገርበት ዕለት ነው፡፡

7. ኒቆዲሞስ
ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡

8. ሆሳዕና
ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚተሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::

ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን፡፡

ለሌሎች ያካፍሉ!
@orthodox_photos
@Orthodox_photos
1.7K viewshaile, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 20:17:22
@orthodox_photos
2.0K viewshaile, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 20:17:17
@orthodox_photos
1.8K viewshaile, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ