Get Mystery Box with random crypto!

በትንቢት የጦርነት ዘመቻ ማካሄድ RHAPSODY OF REALITIES (Amharic) Friday | Lovedface የተወደደ መልክ

በትንቢት የጦርነት ዘመቻ ማካሄድ

RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic)

Friday July 29th, 2022
(አርብ - ሐምሌ 22 - 2014)

════════
ጢሞቴዎስ ልጄ ሆይ፥ አስቀድሞ ስለ አንተ እንደ ተነገረው ትንቢት፥ በእርሱ መልካም ጦርነት ትዋጋ ዘንድ ይህችን ትእዛዝ አደራ እሰጥሃለሁ፤ (1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡18)

ፓስተር ክሪስ
━━━━━━━━━
በሐዋርያት ሥራ 5፤26 ላይ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል “በዚያን ጊዜ አዛዡ ከሎሌዎች ጋር ሄዶ አመጣቸው፥ በኃይል ግን አይደለም፤ ሕዝቡ እንዳይወግሩአቸው ይፈሩ ነበርና።” ከላይ ከተጠቀሰው ጥቅስ ላይ ሻለቃው አለ፤ እንዲሁም መኮንኖች አሉ። “ካፒቴን” የሚለው ቃል በግሪክ “ስትራቴጎስ” ሲሆን አዛዥ መኮንን ማለት ነው።

ሆኖም “መኮንኖች” የሚለው ቃል «ሁፒሬቴስ» (ግሪክኛ) ሲሆን፣ ይህም በእጃቸው የሚሠሩትን ያመለክታል፤ በሌላ አባባል “ስትራቴጎስ” ማለትም አለቃው ወይም አዛዡ የሚሰጣቸውን ኃላፊነት ወይም መመሪያ የሚያከናውኑ ሰዎች ናቸው። ከዚያም 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3ን ስታነቡ እንዲህ ይላል፣ “እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል።” “ወታደር” የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን “ስትራቲዮተስ” ሲሆን ከ”ስትራቴጎስ” እና ከ”ሁፒሬቴስ” የተለየ ነው። ነገር ግን በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ እንዳነበብነው መልካምን ጦርነት “ትዋጋ” ዘንድ ብሎ ሲናገር ለጦርነት “ስትራቲዮማይ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል። ይህ አባባል በወታደራዊ ዘመቻ ላይ ያለ አንድን አዛዥ ማለትም አንድን የጦር ንድፍ አውጭ ያመለክታል። “ሁፒሬቴስ” ወይም “ስትራቴጎስ” ሳይሆን ስትራቴጂስት ወይም የጦር ስልት አዋቂ ነው!

እንደ “ስትራቲዮተስ” ጠንካራ መሆን ይጠበቅባችኃል፤ እንደ ጥሩ ወታደር። ነገር ግን እንደ “ሁፐሬቴስ” “ጦርነት” ውስጥ በቀጥታ የምትሳተፉ መኮንኖች አይደላችሁም፤ ይልቅ ትንቢትን ተጠቀሙ። ሃሌ ሉያ! የመንፈስ ስልት የሆነውን ትንቢትን ለጦርነት ተጠቀሙ። በትንቢት በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት በኃይል የተሞሉ ቃላትን እያወጃችሁ ነው።

የሕይወታችሁን አቅጣጫ ቅርጽ ለማስያዝና ዕቅድ ለማውጣት ቃሉን ተጠቀሙበት። ቃል መንፈሳዊ ንጥረ ነገር ነው። ለዚህም ነው በመንፈስ ብዙ መፀለያችሁ አስፈላጊ የሆነው። ይህን ስታደርጉ፥ አጋንንትን እና የሕይወትን ተግዳሮቶች የምታሸንፉበትን በእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሽነት በአእምሮአችሁ ያለውን ቃላትን ትናገራኛላችሁ።

የእምነት አዋጅ
━━━━━━━━
ከልዕለ ተፈጥሮ በሆነ አቅርቦት፣ በብርታት፣ በችሎታ፣ በጥበብና በእውቀት እየሰራሁ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እግዚአብሔር ለህይወቴ ያለውን አላማ እየፈጸምኩ ነው። በዚህ ዓለም ውስጥ ከክፋት ሁሉ ለዘላለም ተጠብቄአለሁ። የክብር፥ የግዛትና የዘላለም ደስታ ስፍራ በሆነው ሁሉን በሚችል አምላክ ደህንነትና ሰላማዊ መኖሪያ ውስጥ እኖራለሁ፤ በሁኔታዎች ላይ ከክርስቶስ ጋር በመግዛት እኖራለሁ፣ በኢየሱስ ስም። አሜን።

ለተጨማሪ ጥናት:
ትንቢተ ሆሴዕ 14:2;
ዕብራውያን 13:5-6;
መጽሀፈ መክብብ 8:4
━━━━━//━━━━