2022-07-27 10:40:04
የመዳን ተሸካሚዎች
RHAPSODY OF REALITIES
(Amharic)
Wednesday July 27th, 2022
(ረቡዕ - ሐምለ 20 - 2014)
════════
የብሩክ እግዚአብሔርንም ክብር እንደሚገልጥ ለእኔ አደራ እንደ ተሰጠኝ ወንጌል (1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡11)
ፓስተር ክሪስ
━━━━━━━━━
እንደ ክርስቲያኖች የማስታረቅ አገልግሎት አለን። የእኛ የወንጌል ስራ አለማችንን መድረስና ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ ነው። ይህን መፈፀም አለብን። በኢየሱስ ክርስቶስ ያመንን እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ወዳለ ህብረት እንድንመጣ ሆኗል (1ኛ ዮሐንስ 1፡3)። ነገር ግን አለም በጠቅላላው ወደዚህ ህብረት ገና አልመጣም። እነርሱን ማምጣት የእኛ ኃላፊነት ነው።
ኢየሱስ በማርቆስ 16፡15 ላይ እንዲህ አለ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።” ይህ ትዕዛዝ የተሰጠው ለእኛ ለደቀ መዝሙሮቹ እንጂ ለመላዕክት አልነበረም። ሰዎችን ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ እንዲያደርጉ እግዚአብሔር መላዕክትን እንዲልክ የሚፀልዩ ሰዎች አሉ። ነገር ግን ያ የመላዕክት ስራ አይደለም። የእነርሱ ስራ እኛ ወንጌልን እንድናገለግላቸው ሰዎችን ከእኛ ጋር እንዲገናኙ ማድረግ ነው።
እኛ የመዳን መልዕክት ተሸካሚዎች ነን። ሰዎችን በክርስቶስ ኢየሱስ ወዳለ ደህንነት የምንመራው እኛ ነን። ምናልባት የሆነ ሰው እንዲህ ሊል ይችላል “ነገር ግን በራዕይ 14፡6-7 የዘላለም ወንጌልን ሊሰብክ ስላለው መልዓክ ተነግሮናል፤ ‘በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤ በታላቅ ድምፅም። የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት አለ።’”
የዚህ መልአክ መልዕክት የመዳን መልዕክት ሳይሆን ቁጥር 7 ላይ ባለው የተሰመረበት ጥቅስ ላይ እንደሚታየው የፍርድ ነበር። የደህንነት ወንጌልን መስበክ በግልፅ ለእኛ የተመደበ ተግባር ነው። በሐዋርያት ስራ 10 ላይ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ መልአክ ስሙ ቆርኔሌዎስ ወደ ተባለ የሮም ወታደር እንዴት እንደተላከ ይነግረናል (ሐዋርያት ስራ 10፡1-3)። ነገር ግን መልዓኩ ወንጌልን ለቆርኔሌዎስ አልሰበከለትም።በዚያ ፈንታ መልአኩ ከስምዖን ጴጥሮስ ጋር እንዲገናኝ አደረገው። እርሱም መጥቶ ለቆርኔሌዎስና ለቤተሰዉ ሰበከ፤ እነርሱም ደህንነትን ተቀበሉ።
እኛ እስከ አለም ጥግ ድረስ የመዳን መልዕክትን ተሸካሚ መሆናችን እንዴት የከበረ ሃላፊነት ነው! እግዚአብሔር ይባረክ! በዚያ ደስተኛ መሆን አለባችሁ። የህይወታችሁ ስራ አድርጉት። በወንጌል ለማገልገል፣ የእርሱን ጽድቅ ለማሳወቅ እና መንግስቱን በምድርና በሰዎች ልብ ውስጥ ለመመስረት እድል ተሰጥቷችኋል።
ጸሎት
━━━━━━━━
ውድ ጌታ ሆይ፤ የመዳን መልዕክትን ተሸካሚ ለመሆን ስለሰጠኸኝ እድል አመሰግንሃለሁ። ሰዎችን ወደ ጽድቅ ለመመለስ ከጨለማ ወደ ብርሃን እና ከሰይጣን ስልጣን ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉ ለማድረግ የሚያስፈልገውን ፀጋ ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። የክርስቶስና የወንጌል አምባሳደር በመሆን አገልግሎቴን ዛሬ እፈፅማለሁ። አሜን።
ለተጨማሪ ጥናት:
የማርቆስ ወንጌል 16:15-16;
ትንቢተ ዳንኤል 12:3;
2ኛ ቆሮንጦስ 5:18-19;
የማቴዎስ ወንጌል 28:19
━━━━━//━━━━
136 views07:40