Get Mystery Box with random crypto!

VAMOS FIXED MATCH 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidus_god — VAMOS FIXED MATCH 🇪🇹 V
የቴሌግራም ቻናል አርማ kidus_god — VAMOS FIXED MATCH 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @kidus_god
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.21K
የሰርጥ መግለጫ

✞ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው !! ✞
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:13

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 21

2021-09-18 11:00:37
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹ የመስቀል በዐልን ጥራት ባላቸዉ ዉብ ቲሸርቶች ደምቀዉ ያክብሩ
በሚፈልጉት ዲዛይን ጥራት ያላቸው ቲሸርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ
ይደውሉልን
ከልጅ እስከ አዋቂ በሁሉም size የተዘጋጀ።
Price 350
Discount if you order more than 6

Order us @zecrown

0939509821
0939509821
31.7K viewsRooney, 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-18 10:21:30
​​ታላቁ አባ ሲኖዳ

የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:-
- በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
- በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
- የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
- ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
- በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
- የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
- በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
- የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::

ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሠለስቱ ደቂቅ አስኬማ: የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ ዮሐንስ ቅናትን (መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
- ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
- የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
- በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
- ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ ጋር የተነጋገረ
- ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
- ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ አባት ነው::

በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ አርሲመትሪዳ" (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: ) ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር::

በዚህች ዕለት በ120 ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው አቡነ ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ (ታላቅ ዛፍ) ወደቀ" ብለው አልቅሰዋል:: ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::
50.1K viewsAbela, 07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-14 10:22:14
"ሀይሌ ብርታቴ ክብሬ ሞገሴ
የዘላለሙ የአብርሐሙ ሥላሴ"
" እንደ አብርሐም አርገኝ
እንደ ደጉ አባቴ
ቤቴ እንዲሞላ በአንተ በረከት"
በእግዚአብሔር ደስ ይበላቹ! ሰናይ ቀን!
31.0K viewsAbela, 07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-14 08:55:53
አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ

አቤቱ አምላካችን ሆይ ክቡር መንግስት ያንተ ነውና
ከአለም አስቀድሞ ምስጋና
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ይገባል
ዛሬም ዘወትርም ለልጅ ልጅ ለዘላለሙ የማይፈጸም

አሜን
( ኪዳን ዘነግህ ዘመንፈቀ ሌሊት / ክፍል 1 )

ሰዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሳሉት
ሰኔ 7 / 2013 ዓ/ም
ሰዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እና እኔ ዲ/ን ጌታባለው አማረ ልጃቸው በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማን ከቀኖና ስርዓትን ከትውፊት የጠበቁ ቅዱሳት ስዕላትን ሰዓልያን
30.5K viewsAbela, 05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-13 23:00:13 Do u really want to change ur life?
24.5K viewsY Ni, 20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-02 07:34:24 አፅናኝ የተባለው ማነው ?

ሙስሊም ወንድሞቻችን ይህንን ጥቅስ ከመፅሐፍ ቅዱስ በመውሰድ አፅናኝ የተባለው ነብይ (ነብዩ መሀመድ) እንጂ መንፈስቅዱስ አይደለም ይላሉ። በመሰረቱ እነሱ አሉ እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ አላለም ። ጌታም ነብይ እልክላቹዋለው አላለም ። ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን ተቀበልን ሁሉን ነገረን አሉ እንጂ ነቢይ ተላከልን አላሉምታዲያ ጌታችን እልክላቹዋለው ያለው ማንን ነው ? ከተባለ ያለ ምንም ጥርጥር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ነው

ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ በማያሻማ መልኩ በግልጽ አስቀምጦታል የተስፋውም ፍፃሜ እንዲህ ነበር ፦ "በዓለ ሀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉ በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ ተቀምጠውም የነበሩበትን ቤት ሁሉ ሞላው እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጡባቸው በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር "የሐዋ 2:1-4 ታዲያ ከየት መጥቶ ነው መንፈስ ቅዱስ ነቢይ የሚሆነው ? በጭራሽ ነቢይ አይደለም

ያልተባለን ማውራት ላም ካልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደሚሉት አበው ይህንን ትምህርት ሐዋርያትም ፣ ነብያትም፣ ሊቃውንትም አላስተማሩም። መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው መካከል አንዱ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ነበር ። እርሱም ከሐዋርያት ጋር በፆም በፀሎት የተጉ 120ዎቹን ቤተሰብ በመወከል ከተለያየ አገራት በበዓሉ ላይ ለመገኘት ለመጡት ሰዎች ልብን የሚነካ መንፈሳዊ ክፍተትን የሚሞላ ፣ ጥያቄን የሚመልስ ንግግር አደረገላቸው። የንግግሩ ዋና ማዕከል ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የንግግሩ ርዕስ እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ነበር ። ፈሪና ከሀዲ የነበረው ቅዱስ ጴጥሮስ ታላቅ ድፍረትን ተሞልቶ የመጀመሪያውን የምስራች አወጀ ከዚያም በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት 3000 ሰዎች ያለ ምንም የጦር መሳሪያ ኃይል ወዲያው ለወንጌል ተሸነፋ

የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶክ ፍቅሩ ፣ ሞቱ፣ ትንሳኤው ፣ ለሰው ልጆች ያደረገውን ቤዛነት ሲሰሙ በወንጌል አምነው ተጠመቁ የሐዋ 2:41 ይህ ይላካል የተባለው የአጽናኙ የመንፈስ ቅዱስ ጅማሬ ነበር ። ከዚህም የተነሳ የጥበበኞች ጥበበኛ እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ ሐዋርያትም ዳግመኛ ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ መስበክ እንደማይቻላቸው ያውቃልና በሰናኦር ሜዳ የተበተኑትን የዓለም ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ውስጥ ሰብስቦ ያኖር ዘንድ የጽድቅ መንፈስ ጰራቅሊጦስ ተላከ

መንፈስ ቅዱስ በወረደበት ዕለት የበዓሉ ታዳሚዎች በየራሳቸው ቋንቋ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ከሰሙ በዋላ ደቀ መዛኑርቱን ሰክረው ነው እንጂ ይህ ያልተለመደ ምንድነው ? እያሉ በመደነቅ ማጉረምረም ጀመሩ ። ጴጥሮስም "ለእናንተ እንደመሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም ከቀኑ 3:00 ነውና ነገር ግን በነብዩ ኢዩኤል የተባለው ነው " የሐዋ 2:14 በማለት አስረዳቸው ። ከጠዋቱ 3:00 መጠጥ አይጠጣም ነበርና ከሐዋርያው ከቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር የምንረዳው ወይም የምንማረው እንደ መሰለን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ከአተረጓጎም ስርዓት ውጪ አጽናኙ መንፈስ ቅዱስን ነብይ ነው ብሎ መገመትና መተርጎም አግባብ አይደለም ። እንደመሰለን መተርጎም አላዋቂነት ነው 1ጴጥ 4:11
35.7K viewsAbela, 04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-18 09:52:17 ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል
"ሰኔ ፲፪"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ: ብኡላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ: እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ: ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ: ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።

ዚቅ
ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይመክሮ: አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት: ኢየኀልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኀይሉ: ወአልቦ ኁልቊ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ: አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ: ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሪሃ ለሕግ።

ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል: እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

ዚቅ
አመ ይነፍህ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ: ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ፀሃፈ: ሶበ እጼውእ ስመከ ከሢትየ አፈ: ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ: ለረዲኦትየ ነዓ ሠፊሐከ ክንፈ።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዓቢተነ በመድኃኒትከ: ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ: ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ።

ወረብ
ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ/፪/
ዘኢትነውም ትጉሕ "ኖላዊነ ኄር"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ: በእንተ ስጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ: ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ: ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ: በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።

ወረብ
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/
"በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ/፪/

ዚቅ
አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ: ዘኢይረክቦን ጥረስ: ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ: እስመ ረሰይከ ካህነ ምሥዋኡ ክርስቶስ: መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ።

ዚቅ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ: ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ: ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ።

ወረብ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ/፪/
ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ስዕንኩ/፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለእስትንፋስከ ቁሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ: ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ: ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ: ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ አመፃ ደርብዮ: እስመ ኢኃደገ እንከ ዘትካት እከዮ።

ዚቅ
ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ: ወእከስተ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን: ወእፈውስ ሎሙ ለቁሱላነ ልብ: ወእሰምዮ ለባሕራን ኅሩየ: ዝኬ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት: ለ፳ኤል ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም: ወርእየቱ ከመ ተቅጻ ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ።

ወረብ
"ወከሢቶ ረከበ"/፪/ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ/፪/
ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ/፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ: ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ: ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሥዋኡ: አሣዕነ መድኃኒት ለእገርየ አጻብኢከ ይቅጽዑ: ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ።

ዚቅ
ቅዱሳት አጻብኢከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ: ወብጹዓት አዕይንቲከ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ: ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ።

ወረብ
ምስጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ/፪/
ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ "ሚካኤል መልአክ"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ ኲሉ: ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ: ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ: ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኃ ሰማያት ዘላዕሉ: ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።

ዚቅ
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል: ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ: አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ።

ወረብ
መልአከ ሰላምነ/፬/
ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል በእንቲአነ/፪/

ምልጣን
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ: ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ: ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ: ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ።

አመላለስ
ወሪዶ እመስቀሉ/፪/
እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ/፬/

ወረብ
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ/፪/
ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ/፪/

እስመ ለዓለም
እምድኅረ ተንሥአ እሙታን ዓርገ ውስተ ሰማያት በስብሐት አምላከ ምሕረት: ወተቀብልዎ አዕላፋ አዕላፋት: ወሚካኤል ሊቀ መላእክት በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር: ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር።

ዓዲ (ወይም)
እስመ ለዓለም
ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ: አዓርግ ሰማየ አቡየ ወአቡክሙ: ኀበ አምላኪየ ወአምላክክሙ: ዘንተ ይቤሎሙ ዓርገ ውስተ ሰማያት: ካዕበ ይመጽእ በዘዚአሁ ስብሐት: ሠርጎሙ ለሐዋርያት ብርሃኖሙ ለእለ ውስተ ጽልመት: መድኃኔ ነገሥት ክብሮሙ ለመላእክት ኖላዊሆሙ።

አመላለስ
በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር/፪/
ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር/፪/
ኦ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ዕቀብ ሕይወተነ ወሥረይ ኀጢአተነ፤
አድኀነነ ወባልሐነ ከመ ኢይርከብ ኃይለ ላዕሌነ ዝንቱ ደዌ ዘኮነ በመዋዕሊነ፡፡
ክፍለነ እምበረከትከ ቅድስት፡ በጸሎተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለ አሥመሩከ እምፍጥረተ ዓለም፡፡
42.8K viewsAbela, 06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ