Get Mystery Box with random crypto!

አፅናኝ የተባለው ማነው ? ሙስሊም ወንድሞቻችን ይህንን ጥቅስ ከመፅሐፍ ቅዱስ በመውሰድ አፅናኝ የ | VAMOS FIXED MATCH 🇪🇹

አፅናኝ የተባለው ማነው ?

ሙስሊም ወንድሞቻችን ይህንን ጥቅስ ከመፅሐፍ ቅዱስ በመውሰድ አፅናኝ የተባለው ነብይ (ነብዩ መሀመድ) እንጂ መንፈስቅዱስ አይደለም ይላሉ። በመሰረቱ እነሱ አሉ እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ አላለም ። ጌታም ነብይ እልክላቹዋለው አላለም ። ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን ተቀበልን ሁሉን ነገረን አሉ እንጂ ነቢይ ተላከልን አላሉምታዲያ ጌታችን እልክላቹዋለው ያለው ማንን ነው ? ከተባለ ያለ ምንም ጥርጥር እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ነው

ይህንንም መጽሐፍ ቅዱስ በማያሻማ መልኩ በግልጽ አስቀምጦታል የተስፋውም ፍፃሜ እንዲህ ነበር ፦ "በዓለ ሀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉ በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ ተቀምጠውም የነበሩበትን ቤት ሁሉ ሞላው እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጡባቸው በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር "የሐዋ 2:1-4 ታዲያ ከየት መጥቶ ነው መንፈስ ቅዱስ ነቢይ የሚሆነው ? በጭራሽ ነቢይ አይደለም

ያልተባለን ማውራት ላም ካልዋለበት ኩበት ለቀማ እንደሚሉት አበው ይህንን ትምህርት ሐዋርያትም ፣ ነብያትም፣ ሊቃውንትም አላስተማሩም። መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው መካከል አንዱ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ነበር ። እርሱም ከሐዋርያት ጋር በፆም በፀሎት የተጉ 120ዎቹን ቤተሰብ በመወከል ከተለያየ አገራት በበዓሉ ላይ ለመገኘት ለመጡት ሰዎች ልብን የሚነካ መንፈሳዊ ክፍተትን የሚሞላ ፣ ጥያቄን የሚመልስ ንግግር አደረገላቸው። የንግግሩ ዋና ማዕከል ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የንግግሩ ርዕስ እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ነበር ። ፈሪና ከሀዲ የነበረው ቅዱስ ጴጥሮስ ታላቅ ድፍረትን ተሞልቶ የመጀመሪያውን የምስራች አወጀ ከዚያም በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት 3000 ሰዎች ያለ ምንም የጦር መሳሪያ ኃይል ወዲያው ለወንጌል ተሸነፋ

የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶክ ፍቅሩ ፣ ሞቱ፣ ትንሳኤው ፣ ለሰው ልጆች ያደረገውን ቤዛነት ሲሰሙ በወንጌል አምነው ተጠመቁ የሐዋ 2:41 ይህ ይላካል የተባለው የአጽናኙ የመንፈስ ቅዱስ ጅማሬ ነበር ። ከዚህም የተነሳ የጥበበኞች ጥበበኛ እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ ሐዋርያትም ዳግመኛ ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ መስበክ እንደማይቻላቸው ያውቃልና በሰናኦር ሜዳ የተበተኑትን የዓለም ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ውስጥ ሰብስቦ ያኖር ዘንድ የጽድቅ መንፈስ ጰራቅሊጦስ ተላከ

መንፈስ ቅዱስ በወረደበት ዕለት የበዓሉ ታዳሚዎች በየራሳቸው ቋንቋ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ከሰሙ በዋላ ደቀ መዛኑርቱን ሰክረው ነው እንጂ ይህ ያልተለመደ ምንድነው ? እያሉ በመደነቅ ማጉረምረም ጀመሩ ። ጴጥሮስም "ለእናንተ እንደመሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም ከቀኑ 3:00 ነውና ነገር ግን በነብዩ ኢዩኤል የተባለው ነው " የሐዋ 2:14 በማለት አስረዳቸው ። ከጠዋቱ 3:00 መጠጥ አይጠጣም ነበርና ከሐዋርያው ከቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር የምንረዳው ወይም የምንማረው እንደ መሰለን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ከአተረጓጎም ስርዓት ውጪ አጽናኙ መንፈስ ቅዱስን ነብይ ነው ብሎ መገመትና መተርጎም አግባብ አይደለም ። እንደመሰለን መተርጎም አላዋቂነት ነው 1ጴጥ 4:11