Get Mystery Box with random crypto!

​​ታላቁ አባ ሲኖዳ የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:- - በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የ | VAMOS FIXED MATCH 🇪🇹

​​ታላቁ አባ ሲኖዳ

የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:-
- በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
- በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
- የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
- ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
- በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
- የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
- በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
- የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::

ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሠለስቱ ደቂቅ አስኬማ: የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ ዮሐንስ ቅናትን (መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
- ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
- የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
- በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
- ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ ጋር የተነጋገረ
- ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
- ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ አባት ነው::

በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ አርሲመትሪዳ" (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: ) ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር::

በዚህች ዕለት በ120 ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው አቡነ ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ (ታላቅ ዛፍ) ወደቀ" ብለው አልቅሰዋል:: ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::