Get Mystery Box with random crypto!

✞ገድለ ቅዱሳን✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ kegdlat — ✞ገድለ ቅዱሳን✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ kegdlat — ✞ገድለ ቅዱሳን✞
የሰርጥ አድራሻ: @kegdlat
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.13K
የሰርጥ መግለጫ

✝✞ከኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ላይ የተገኙ የየዕለቱ የቅዱሳን አባቶቻችን እና የቅዱሳት እናቶቻችን ገድል ይነገርበታል✝

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 22

2023-01-10 07:00:54 +ቀጥሎም ለታላቅ ሃላፊነት ተመረጠ:: አባ መክሲሞስ ባረፈ ጊዜ የግብጽ 16ኛ ፓትርያርክ ሆነ:: ግን ኃላፊነቱ ሠርግና ምላሽ (የተመቸ) አልነበረም:: ምክንያቱም እርሱ ሊቀ ዻዻሳት ሲሆን ዘመነ ሰማዕታት በመጀመሩ ክርስቲያኖች ተሰደዱ: ተጨፈጨፉ::+አብያተ ክርስቲያናትም ተቃጥለው አለቁ:: በዚሀ ጊዜ ቅዱስ ቴዎናስ እየዞረ ሕዝቡን ያጸና ነበር:: በተለይም የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን አንጾ ለሕዝቡ ያቆርብ: ያስተምር ነበር::

+በዘመነ ሲመቱ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ዼጥሮስን ጨምሮ ብዙ አርድእትን አፍርቷል:: ሥልጣነ እግዚአብሔር ጋርዶት ስለ ነበር አገልግሎቱን ፈጽሞ በዚህ ቀን ዐርፏል::

=>የጻድቅ ሰው አቤል አምላከ የውሃቱን ይስጠን:: የዋሃንን ያብዛልን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

=>ጥር 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
2.ቅዱስ ቴዎናስ ሊቀ ዻዻሳት
3.ቅዱስ አላኒቆስ ሰማዕት
4.ቅድስት ሳቤላ ነቢዪት
5.ቅዳሴ ቤታ ለድንግል (በደብረ አባ ሲኖዳ)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
4.ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ (መጥምቀ መለኮት)
5.ሊቁ አባ ሕርያቆስ
6.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

=>+"+ እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ: የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው . . . አቤል ከቃየን ይልቅ የሚበልጥን መስዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ:: በዚህም እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት:: ሞቶም ሳለ በመስዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል:: +"+ (ዕብ. 11:1)

    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
461 views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 07:00:54 Daniel:
✞ እንኳን ለጻድቅ ሰው "ቅዱስ አቤል" እና "ቅዱስ ቴዎናስ ሊቅ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞

("አቤል" ማለት በስዕሉ ከፊት ያለው ወጣት ነው)

+*" ቅዱስ አቤል ጻድቅ "*+

=>እግዚአብሔር አዳምን በ7 ሃብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው "አትብላ" የተባለውን ዕፀ በለስ በላ:: በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ: በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ: በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ተፈረደበት:: በሁዋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ "ከ5 ቀን ተኩል (5,500 ዘመን) በሁዋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃል ኪዳንን ሰጠው::

+አዳምና ሔዋን ከገነት ከወጡ በሁዋላ ወዲያው ሕገ ሰብሳብን (የወንድና የሴት ሥርዓትን) አልፈጸሙም:: ይልቁኑ ለ14 ኢዮቤልዩ (ለ100 (98) ዓመታት) ንስሃ ገቡ: አለቀሱ እንጂ::

+አለቃቀሳቸውም እንደኛ በቤተ ፈት ልማድ ሳይሆን "እግዚአብሔርን ያህል ጌታ: ገነትን ታህል ቦታ በበደላችን አጣን" እያሉ ነበር:: "አልቦቱ ለአዳም ካልዕ ሕሊና ዘእንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢአቱ" እንዲል:: (መቅድመ ወንጌል)

+እውነትን እንነጋገር ከተባለ እኛ ለወላጆቻችን አዳምና ሔዋን ተገቢውን ክብር እየሰጠናቸው አይደለም:: አንደበቱን የከፈተ "አስተማሪ" ሁሉ ኃጢአታቸውን እንጂ ክብራቸውን ሲናገር ሰምቼ አላውቅም:: ሌላው ይቅርና ማንም ሰው "ቅዱስ አዳምና ቅድስት ሔዋን" ብሎ ሲጠራቸው ገጥሞኝ አያውቅም::

+የሚገርመው ደግሞ እኛ እልፍ አእላፍ ኃጢአትን ተሸክመን እነርሱን ስለ አንዲቷ ኃጢአታቸው ስንወቅሳቸው መዋላችን ነው:: በእነርሱ ምክንያት ገነት ብትዘጋ: ዳግመኛ የተከፈተችው በፍጹም እንባና ንስሃቸው ነው::

+"ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት" (ቅዳሴ ማርያም) እንዲል:: ጌታን ለሰውነት: ለሞት ያበቃው ፍቅረ አዳም መሆኑን ልንዘነጋ አይገባም::

+በዚያውም ላይ አባታችን ቅዱስ አዳም:-
*በኩረ ኩሉ ፍጥረት
*በኩረ ነቢያት አበው
*በኩረ ሐዋርያት ወአርድእት
*በኩረ ጻድቃን ወሰማዕት
*በኩረ ደናግል ወመነኮሳት የሆነ ደግ ፍጥረት ነው:: ስለዚህም ቅዱሳን አዳምና ሔዋንን ልናከብራቸው በእጅጉ ይገባናል::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱሳኑ አዳምና ሔዋን ንስሃቸውን ፈጽመው: ተስፋ ድኅነት ከተሰጣቸው በሁዋላ አብረው አደሩ:: በዚያች ሌሊትም ቃየንና ኤልዩድ (ሉድ) ተጸነሱ: በጊዜውም ተወለዱ::

+አሁንም ድጋሚ አብረው ቢያድሩ ቅዱስ አቤልና መንትያው አቅሌማ ተጸንሰው ተወለዱ:: ዓለምም በጊዜው እነዚ 6 ሰዎች ይኖሩባት ነበር:: ምንም እንኩዋ እናታችን ቅድስት ሔዋን ብዙ መንትያዎችን ብትወልድም "ብዙ ተባዙ: ምድርንም ሙሉአት" ያለው የጌታ ቃል ይፈጸም ዘንድ ልጆቻቸውን ማጋባት ነበረባቸው::

+የመጀመሪያው የልጆች ጋብቻም በአቤልና በኤልዩድ: እንዲሁም በቃየንና በአቅሌማ መካከል እንዲሆን ተወሰነ:: አባታችን ቅዱስ አዳም ደግ ነቢይ ነውና ለማራራቅ ሲል ይህንን አደረገ:: ነገር ግን በውሳኔው እንደማይስማማ ቃየን ተናገረ::

+ምክንያቱ ደግሞ የአቤል መንትያ መልኩዋ የኔ ብጤ በመሆኗና የእርሱ መንትያ ኤልዩድ ግን እናቷን ቅድስት ሔዋንን የምትመስል ቆንዦ ስለ ነበረች "እኔ መንትያየን ነው የማገባ" የሚል ነበር::

+አቤል ግን የቱንም ቢሉት ከወላጆቹና ከፈጣሪው ትዕዛዝ የማይወጣ ደግ ሰው ነበር:: በጊዜውም መላእክት ባስተማሩት መሠረት ቅዱስ ሰው አዳም ለልጆቹ እርሻንና እንስሳት እርባታን አስተምሯቸው ነበርና ቃየን በግብርና: አቤል ደግሞ በበግ እረኝነት (እርባታ) ይኖሩ ነበር::

+ቅዱስ ሰው አቤል በቅንነቱና በታዛዥነቱ መንፈሰ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሆነለት:: ሁሌም ስንጠራው "ጻድቅ" ብለን ነው:: ከጻድቃነ ብሊት (ብሉይ) አንዱ ሲሆን የዚህች ዓለም የመጀመሪያው ሟችና ሰማዕት ለመሆንም በቅቷል::

+በሴት ልጅ መልክ ምክንያት በዚህች ዓለም ጥላቻ "ሀ" ብሎ ጀመረ:: ምንም ሳያደርገው ቃየን ወንድሙ አቤልን ጠላው:: የጥላቻ አባቷ ዲያብሎስ ነውና የእርሱ ዘመድ ሆነ::

+ነገሮች ያላማሩት ቅዱሱ አባታቸው ግን በጐ መፍትሔ ሊሆናቸው: የቀናውንም ሥርዓት ሊያስተምራቸው "ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አቅርቡ:: እግዚአብሔር መስዋዕቱን የተቀበለለት ኤልዩድን ያገባል" አላቸው:: "እሺ" ብለው መካነ ምስዋዕ አዘጋጁ::

+አቤል ከንጹሕ ልቡ እንዲህ አሰበ:: "እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ ነውና ንጹሕ ነገርን ይወዳል" አለ:: በዚህም ቀንዱ ያልከረከረውን: ጥፍሩ ያልዘረዘረውን: ጠጉሩ ያላረረውን: የ1 ዓመት ነውር የሌለበትን ጠቦት አቀረበ::

+ቃየን ደግሞ ከክፉ ልቡ እንዲህ አሰበ:: "እግዚአብሔር አይበላ: አይጠጣ:: ጥሩ ነገር ብሰጠውስ ምን ያደርገዋል" ብሎ ዋግ የመታውን: ነቀዝ የበላውን እሕል (ሥርናይ) አቀረበ:: እዚህ ላይ አንድ ነገርን ልብ እንበል::

+እግዚአብሔር እንደ ሰው አይበላም: አይጠጣም:: ይህ እውነት ነው:: ግን እግዚአብሔር የአቤልን መስዋዕት የተቀበለው በጉን ፈልጐ: ወይ አቤል ቆንጆዋን ሴት እንዲያገባ አይደለም:: ምክንያቱም አቤል እንደሚገደልና በድንግልናው እንደሚሰዋ እርሱ ያውቃልና::

+ይልቁኑ እግዚአብሔርን የሚያስደስተው የስጦታው ምንነት ሳይሆን የሰጭው ማንነት ነውና እኛ ክርዳድ ሆነን ለእግዚአብሔር ስንዴ ልናቀርብለት አንችልም:: ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእኛ ምንም ነገርን አይሻም:: ሰማይና ምድር: ፍጥረታት በሙሉ የእርሱ ናቸውና::

+ንጹሐ ባሕርይ ጌታ ከእኛ አንዲት ነገርን ብቻ ይሻል:: ይህቺም በንጹሕ ልቡና የምትቀርብ ንጹሕ አምልኮ ናት:: በዚህም የምንጠቀመው እኛ እንጂ እርሱ አይደለም::

+2ቱ ወንድማማቾች መስዋዕትን ሲያቀርቡለትም "ወነጸረ እግዚአብሔር ላዕለ አቤል ወላዕለ መስዋዕቱ" እንዲል እግዚአብለሔር ቃየንና መስዋዕቱን ትቶ መጀመሪያ ወደ አቤል: ቀጥሎም ወደ መስዋዕቱ ተመለከተ:: ማለትም አቤልና መስዋዕቱን ወደዳቸው::

+በዚህ ምክንያትም ቃየን ተበሳጨ:: ክፋትን እያሰበ ሲመላለስም ሰይጣን ተገናኝቶ ክፉውን መከረው:: በቁራ ተመስሎ ነፍሰ ገዳይነትን አስተማረው:: በዚህም ወደ ምድረ በዳ ወስዶ በድንጋይ ጭንቅላቱን መትቶ ገድሎት ሔደ::

+በዚህ ምክንያትም አቤል "በኩረ ምውታን - የመጀመሪያው ሟች" ተባለ:: "የዋሕ" የተባለበትም ምሥጢሩ ቂም እንደ ያዘበት: ክፋትን እንዳሰበበት እያወቀ እንደ በግ ተከትሎት መሔዱ ነው::

+ስለዚህም ነገር ለመድኃኒታችን ክርስቶስ ምሳሌው ሆነ:: አባ ሕርያቆስም እመቤታችንን ሲያመሰግናት "የውሃቱ ለአቤል ዘተቀትለ በአመጻ-በአመጻ የተገደለ የአቤል የውሃቱ: የየዋህነቱን ዋጋ የምታሰጭው አንቺ ነሽ" ብሏል::

+ቅዱስ አቤል ከተገደለ ከ28 ዓመታት በሁዋላ ነፍሱ ገነትን ተሳልማለች:: ስለ ቅዱሱ ግፍም እግዚአብሔር የቃየንን ዘሮች በጥፋት ውሃ ደምስሷቸዋል::

+"+ ቅዱስ ቴዎናስ ሊቀ ዻዻሳት +"+

=>ይህ ቅዱስ ሰው ተወልዶ ያደገው በእስክንድርያ (ግብጽ) ሲሆን ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እርሱ ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ተምሮ ጸጋው ቢበዛለት ከምዕመንነት ወደ ዲቁና: ከዲቁና ወደ ቅስና ማዕርግ ተሸጋገረ::
564 views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 06:52:29 + +  +እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን እና ላለንበት ሀገር ሰላምን ይስጥልን አሜን++

መጽሐፈ ስንክሳር፣
ከዲ/ን ዮርዳኖስ ማስታወሻ

+++መልካም ዕለተ ሰንበት መልካም ቀን።
+++
654 views03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 06:51:33
651 views03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 06:50:41 ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሠላሳ(፴)
https://t.me/SinkisarZekidusan2
507 views03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 06:49:46 +ሚስቱ ግን በረከቱን ሽታ ልታየው ብትሞክርም አልተሳካም:: ሕገ ምናኔ አይፈቅድምና:: በዚህ ነገር ፈጽማ ማዘኗን በጸጋ ያወቀው አባ ዮሐንስ ግን በራዕይ ወደ እርሷ መጣ::+"ሚ ሊተ ወለኪ ብእሲቶ - አንቺ ሆይ! ለምን ካላየሁህ እያልሽ ትዘበዝቢኛለሽ? እኔ ነቢይ ወይ ጻድቅ አይደለሁ" ብሏት ባርኯ ተሠወራት:: እርሷም ደስ ብሏት ለባሏ ነገረችው:: ባሏ ወደ ጻድቁ ሲሔድም ገና ሳይነጋገሩአባ ዮሐንስ ሳቅ ብሎ "ሚስትህ ደስ አላት አይደል?" ብሎታል:: ጻድቁ በ90 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል::

=>አምላከ ጻድቃን ቅዱሳን ስለ ወዳጆቹ በጐ ምኞታችንን ይፈጽምልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

=>ታሕሳስ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ዮሐንስ አበ ምኔት
2.አባ ዘካርያስ ገዳማዊ
3.አባ ዮሐንስ ብጹዕ
4."144 ሺ" ሕጻናት (ሔሮድስ የገደላቸው)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
5.አባ ሣሉሲ ክቡር ጻድቅ

=>+"+ ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኑራችሁ: ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ:: እንደሚታዘዙ ልጆች ባለ ማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ:: ዳሩ ግን 'እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ' ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ:: +"+ (1ዼጥ. 1:13)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
420 views03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 06:49:45 Daniel:
✞ እንኩዋን ለቅዱሳን ጻድቃን ወገዳማውያን "አባ ዮሐንስ" : "አባ ዘካርያስ ወአባ ዮሐንስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞

+*" አባ ዮሐንስ ዘአስቄጥስ "*+

=>ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::

+ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::

+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::

+ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::

+ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::

+ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::

+እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::

+አባ እንጦንስ አባ መቃርስን: አባ መቃርስ አባ ዮሐንስን ወልደዋል:: አባ ዮሐንስም የታላቁ ገዳመ አስቄጥስ አበ ምኔት ሆነው በጸጋ አገልግለዋል:: አስቄጥስ በምድረ ግብጽ የሚገኝ: በስፋቱና ብዙ ቅዱሳንን በማፍራቱ ተወዳዳሪ የሌለው የዓለማችን ቁጥር አንድ ገዳም ነው::

+ሕይወተ ምንኩሰናም ወደ መላው ዓለም የተስፋፋ በዚህ ገዳም መናንያን አማካኝነት ነው:: በዚህ ገዳም ላይ የሚሾሙ አበው ደግሞ በብዛት መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸውና አባታቸውን ቅዱስ መቃርስ ታላቁን የመሰሉ ናቸውና ኃላፊነቱ እጅግ ከባድ ነው::

+በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ተወልደው ያደጉት አባ ዮሐንስ ከመነኑባት ዕለት ጀምረው በፍጹም ተጸምዶና ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ስለ ተገዙ የታላቁ ገዳም አበ ምኔት ሊሆኑ ተገባቸው::

+በአበ ምኔትነት ዘመናቸውም መንጋውን ይጠብቁ ዘንድ ብዙ ደከሙ:: በተለይ ቅዱስ ቃሉን ያስተምሩ ዘንድ ተጉ:: ሕይወተ መላእክትንም ያሳዩ ዘንድ በቃል ብቻ ያይደለ በተግባር ሆነው ከመንፈሳዊ አብራካቸው ብዙ ቅዱሳንን ወለዱ::

+ከዋክብቱ አባ ገዐርጊ: አባ አብርሃም: አባ ሚናስ: አባ ዘካርያስ . . . የአባ ዮሐንስ ፍሬዎች ናቸውና:: ጻድቁ በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: ከዕረፍታቸው በሁዋላ እንኩዋ መግነዛቸውና የልብሳቸው እራፊ ብዙ ድውያንን ፈውሷል::

+አንድ ጊዜም ለልጆቻቸው መነኮሳት ቤዛ ሆነው በበርበር (አረማውያን) ተማርከዋል:: በዚያም ክፉዎች ባሪያ ቢያደርጉዋቸው እግዚአብሔር ድንቅን ሠርቶ ወደ ገዳማቸው መልሷቸዋል:: ከብዙ ተጋድሎ በሁዋላም በ90 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈው በበዓታቸው ተቀብረዋል::

+"+ አባ ዘካርያስ ገዳማዊ +"+

=>ይሕም ቅዱስ የተነሳው በዚያው በዘመነ ጻድቃን ነው:: ምንም ክርስቲያን ቢሆንም በቀደመ ሕይወቱ ገንዘብ የሚጥመው ነጋዴ ነበር:: በንግድ ሥራውም ሃብታም መሆን ችሎ እንደ ነበር ዜና ሕይወቱ ይናገራል::

+እግዚአብሔር ሁሉም የሰው ልጆች ወደ መንግስተ ሰማያት ቢገቡ መልካም ፈቃዱ ነው:: ያ ብቻ አይደለም:: ለእያንዳንዱ ሰው የድኅነት ጥሪን በተለያየ መንገድ ያቀርብለታል:: ድምጹን ለሰማ ወደ ወንጌል ወደብ ያደርሰዋል::

+አንዳንዴ "እንቢ" ስንለው እንደ በጐ አባትነቱ በተግሣጹ ሊጠራንም ይችላል:: ተግሣጹም በደዌ: በአደጋና በመሰል መንገዶች ሊሆን ይችላል:: ዋናው ቁም ነገር ግን ጊዜው ሳያልፍብን: ቀኑም ሳይመሽብን ድምጹን መስማት: ለቃሉ መታዘዝ: ጥሪውንና ተግሣጹን አለማቃለል ነው::

+አባ ዘካርያስም የቅድስና ሕይወት ጥሪ የደረሰው ለሥጋ ገበያ ሲታትር ነበር:: አንድ ቀን ንብረቱን ይዞ ለንግድ መንገድ ላይ ሳለ ሽፍቶች ያዙት:: ሊያርዱት አጋድመውት ሳለ ግን የገዳመ ዻኩሚስ አበ ምኔት በሥፍራው ነበርና ጮኸባቸው::

+ቅዱሱ አበ ምኔት አካሉ በገድል ያለቀ ቢሆንም ድምጹ እንደ ነጐድጉዋድ ሲመጣ ገዳዮቹ ደንግጠው በረገጉ:: ዘካርያስም ከሞት ተረፈ:: እንደ ገና ሃብቱን ይዞ ወደ ከተማ ሲገባ በሃገረ ገዢው ተይዞ ሞት ተፈረደበት:: ከገንዘቡ መብዛት የተነሳ ዘራፊ መስሏቸው ነበርና:: በዚህ ጊዜም እግዚአብሔር በመኮንኑ ልብ ርሕራሔን ጨምሮ አዳነው::

+በዚያች ሌሊት ግን ነገሮችን ያስተዋለው ዘካርያስ የተፈጠሩት አጋጣሚወች የፈጣሪው ጥሪ እንደ ሆኑ አስተዋለ:: ወዲያውም ለዓይነ ሥጋ የሚያሳሳውን ያን ሁሉ ንብረቱን መጽውቶ በርሃ ገባ:: በደብረ አባ ዻኩሚስም መንኩሶ በዓት ወሰነ::

+ከዚያች ቀን ጀምሮም በፍጹም አምልኮ: በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን እያገለገለ ከርኩሳን መናፍስት ጋር ታገለ:: በእግሩም ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዞ ቅዱሳት መካናትን ተሳለመ:: አንድ ጊዜም ሰይጣን ሰው መስሎ "አባትህ ሳልሞት ልየው እያለህ ነው" አለው:: ውስጡ ግን ፈቃደ ሥላሴ ነበረበትና "እሺ" ብሎ ሒዶ: አባቱን ቀብሮ ተመልሷል::

+ቅዱስ አባ ዘካርያስ ከብቃቱ የተነሳ የሚኖረው ከግሩማን አራዊት ጋር ነበር:: ሁሉንም አራዊትም ይመግባቸው ነበር:: በተለይ ደግሞ ዘንዶዎች ሰውን እንዳይጐዱ አዝዞ እርሱ ይመግባቸው ነበር:: የተጋድሎ ዘመኖቹን ከፈጸመ በሁዋላም በዚህች ቀን በክብር ዐርፏል::

+"+ አባ ዮሐንስ ብጹዕ +"+

=>ይህም ቅዱስ በተመሳሳይ የዘመነ ጻድቃን ቅዱሳን ፍሬ ነው:: "ኢትርአይ ገጻ : ወኢትስማዕ ድምጻ" በሚለው ሕገ ተባሕትዎ ለ40 ዓመታት ተወስኖ ኑሯል::

+ይህም ማለት አንድ ወንድ ከመነነ በሁዋላ ሴቶችን እንዲያይና ከእነርሱም ጋር እንዲያወራ አይፈቀድለትም:: ሴትም ብትመንን ሕጉ ያው ነው:: (ዛሬ እየተደረገ ያለውን ግን ፈጣሪ ይመርምረው)

+አባ ዮሐንስ ብጹዕም እንዲህ ባለ ፈሊጥ: ማለትም በጾምና በጸሎት: ከዓለም ተለይቶ: ከሴት ርቆ: ንጽሕ ጠብቆ ሲኖር አረጀ:: በጊዜው በከተማ የሚኖር አንድ መስፍን ወዳጅ ነበረው:: ይህ መስፍን ዘወትር ወደ ጻድቁ እየመጣ ይባረካል::
561 views03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 14:20:58 + +  +እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን እና ላለንበት ሀገር ሰላምን ይስጥልን አሜን++

መጽሐፈ ስንክሳር፣
ከዲ/ን ዮርዳኖስ ማስታወሻ

+++መልካም ቀን መልካም በዓል።
+++
486 views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 14:19:50
497 views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 14:19:28 +++"ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት ወድቀውም ሰገዱለት ሳጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት" ተብሎ እንደተጻፈ ማቴ 2:11

እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ በዓለ ልደት አደረስን/ እደረሳችሁ።
ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሃያ ዘጠኝ(፳፱)
https://t.me/SinkisarZekidusan2
426 views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ