Get Mystery Box with random crypto!

✞ገድለ ቅዱሳን✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ kegdlat — ✞ገድለ ቅዱሳን✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ kegdlat — ✞ገድለ ቅዱሳን✞
የሰርጥ አድራሻ: @kegdlat
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.13K
የሰርጥ መግለጫ

✝✞ከኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ላይ የተገኙ የየዕለቱ የቅዱሳን አባቶቻችን እና የቅዱሳት እናቶቻችን ገድል ይነገርበታል✝

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 18

2023-01-20 07:57:40 ✞✞ ኃያል ቴዎድሮስ በናድሌዎስ ✞✞+በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ (በአንጾኪያ) ያበራ:
*ድንግልናውን በንጹሕ የጠበቀ:
*ቅዱሳን መላእክት የሚያነጋግሩት:
*የአንጾኪያ ሠራዊት ሁሉ አለቃ የነበረ:
*በጦርነት ተሸንፎ የማያውቅ:
*አሕዛብ ስሙን ሲሰሙ የሚንቀጠቀጡለት:
*ከአማልክት ወን ነው እያሉ የሚፈሩት
*እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የሚያመልክ የወቅቱ
ወጣት ክርስቲያን ነው::

ዲዮቅልጢያኖስ በካደ ጊዜም ጌታ ከባልንጀሮቹ
ለውንድዮስና ኒቆሮስ ጋር መላእክት ወደ ሰማይ
አሳርገውታል:: በዚያም
መድኃኒታችን ክርስቶስን ፊት ለፊት አይቶ: በእሳት ባሕርም
ተጠምቁዋል:: በዚህች ቀንም ከቅዱሳን ለውንድዮስና
ኒቆሮስ:
እንዲሁ ከ2.5 ሚሊየን ሰራዊቱ ጋር ለመከራ ተሰጥቷል::
እርሱንም በ153 ችንካር ወግተው ገድለውታል::

✞አምላከ ቅዱሳን ወይነ ቃና ፍቅሩን ያሳድርብን::
ከድንግል እናቱ ምልጃና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::

✞ጥር 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቃና ዘገሊላ
2.ቅዱስ ያዕቆብ እሥራኤል
3.ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ
4.ቅዱሳን ለውንድዮስ እና ኒቆሮስ
5."2.5 ሚሊየን" ሰማዕታት (የቅዱስ ቴዎድሮስ ማሕበር)

በ 12 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ
5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

"+" አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ
አደነቀ:: ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም:: ውሃውን የቀዱት
አገልጋዮች
ግን ያውቁ ነበር:: አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ:- 'ሰው
ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል::
ከሰከሩም
በኋላ መናኛውን:: አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ
አሁን አቆይተሃል' አለው:: (ዮሐ. 2:9)

✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞
256 views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 07:57:39 Daniel:
:
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞ እንኳን አደረሰን ✞

=>ጥር 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+ቃና ዘገሊላ+

=>'ቃና' የሚለው ቃል በሃገራችን ልሳን (በአማርኛ)
የምግብን: የመጠጥን ጥፍጥና ወይም በጐ መዓዛን
የሚያመለክት ነው::
ምንአልባትም ከዚህ በዓል ምሥጢር የተወሰደ ሳይሆን
አይቀርም::

+በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን ቃና ከገሊላ አውራጃዎች
አንዷ ናት:: ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የክብር
ባለቤት
መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚህች ሥፍራ ተገኝቶ በድንግል
እናቱ ምልጃ ታላቅ ተአምርን በዚህች ዕለት ሠርቷል::

+ተአምር የሚለውን ቃል በቁሙ 'ምልክት' ብሎ
መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ
በልሳናቸው Miracle
የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ):
ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር
ይባላል::
ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ
ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ
ተአምራት
ናቸው::

ስለዚህም ነው 'ኤልሻዳይ / ከሐሌ ኩሉ / ሁሉን
ቻይ' እያልን የምንጠራው::
እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና
ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን
እነ ሙሴ
ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ (ኦሪትን
ተመልከት) እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን
ሲያዘንሙ:
ሙታንን ሲያስነሱ (1ነገሥትን ተመልከት) እንደ ነበር
ይታወቃል::

እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ
ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም
መድኃኒታችን ብዙ
ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን
ሰጥቷቸዋል:: (ማቴ. 10:8, 17:20, ማር. 16:17, ሉቃ.
10:17, ዮሐ. 14:12)
+እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን
ሠርተዋል:: (ሐዋ. 3:6, 5:1, 5:12, 8:6, 9:33-43,
14:8, 19:11)

+ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ በወንጌሉ ምዕራፍ 2 ላይ
እንዳስቀመጠው የቃና ዘገሊላው ተአምር የመጀመሪያው
ነው:: "ወዝንቱ
ቀዳሜ ተአምር ዘገብረ . . ." እንዲል:: (ዮሐ. 2:11) ያ
ማለት ግን ጌታ ከዚያ በፊት ተአምራትን አልሠራም ማለት
አይደለም::

ይልቁኑ ራሱን ከገለጠና ከተጠመቀ በኋላ የሠራው
የመጀመሪያው ተአምር ነው ሲል ነው እንጂ:: ምክንያቱም
መድኃኒታችን
እንደ ተጠመቀ ዕለቱኑ ገዳመ ቆረንቶስ ገብቷልና:: (ማቴ.
4:1) አንድም በቃና ሌሎች ተአምራትን የሚሠራ ነውና
ይህ
ተአምር በቃና የመጀመሪያው ሆነ::

+ትክክለኛው የቃና ዘገሊላ ቀን የካቲት 23 ነው:: ጥር
11 ተጠምቆ: የካቲት 21 ቀን ከጾም ተመልሷል::
ከዚያም
የካቲት 23 ቀን ደቀ መዛሙርቱን ሰብስቦ ሒዷል:: ነገር
ግን አበው መንፈስ ቅዱስ እንደ መራቸው የውሃ በዓል
ከውሃ
በዓል ጋር ይስማማል ብለው ጥር 12 ቀን አድርገውታል::

+በቃና ዘገሊላ ሙሽራው ዶኪማስ ሲሆን ባለ ሠርጉ
ደግሞ አባቱ ዮአኪን ነው:: ይህም ለሐዋርያው ቅዱስ
ናትናኤል አጐቱ
ነው:: የልጁ ጋብቻ የተቀደሰ ይሆን ዘንድም ጌታ
ክርስቶስን: ድንግል እናቱንና ባለሟሎቹ ሐዋርያትን ወደ
ሠርጉ ጠራ::

ምንም እንኳ መድኃኒታችንና እመቤታችን ከድግሱ
የማይበሉ ቢሆኑም (በትሕርምት ኗሪዎች ነበሩና)
ጠሪውን ደስ ለማሰኘት
ሠርጉን (ብቻውን) ለመቀደስና የጋብቻን ክቡርነት
ለማሳየት አብረው ታደሙ::

የሠርጉ ሥነ ሥርዓት ሲጀመር በድንኳኑ ውስጥ ጌታ
ከመካከል ተቀመጠ:: ድንግል በቀኙ: ዮሐንስ በግራው
ሲቀመጡ: ሌሎች
ሐዋርያት ግራና ቀኝ ከበው ተቀመጡ:: ሲበላና ሲጠጣ
ድንገት የተደገሰው ምግብና መጠጥ አለቀ::
ደጋሾቹ በጭንቅ ላይ ሳሉም አይጠና ሆዷ ድንግል እመ
ብርሃን የሆነውን አወቀች:: እንዴት አወቀች ቢሉ:- በጸጋ:
አንድም
'ከልጅሽ አማልጂን' ብለው ቢለምኗት ነው ይሏል::
እመቤታችን በዚያ ጊዜ ወደ ልጇ ቀርባ ቸር ልጇን
"ወይንኬ
አልቦሙ-ወይኑኮ አልቆባቸዋል" አለችው::

+ለጊዜው ወይኑም: ምግቡም ስላለቀባቸው እንዲህ
አለች:: በምሥጢሩ ግን ወይን ያለችው ፍቅርን: ቅዱስ
ቃሉንና ክቡር
ደሙን ነው:: ጌታም ይመልሳል:- "ምንት ብየ ምስሌኪ ኦ
ብእሲቶ: ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ-አንቺ ሆይ! (እናቴ ሆይ!)
ያልሺኚን አላደርግ ዘንድ ካንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ? ነገር
ግን ጊዜው ገና አልደረሰም ብየ ነው እንጂ" አላት::
ምክንያቱም ጌታ:-

*የወይን ጋኖቹ እስኪያልቁ ይጠብቅ ነበር:: (አበረከተ
ይሉታልና)
*አንድም ይሁዳ ወጥቶ ነበርና እርሱ እስኪመለስ ነው::
(እኔ ስወጣ ጠብቆ ተአምር ሠራ ብሎ ለክፋቱ ምክንያት
እንዳያቀርብ)
አንድም "ወይን (ቅዱስ ደሜን) የምሰጠው በቀራንዮ አንባ
ነው" ሲል "ጊዜየ ገና ነው" ብሏታል:: አንዳንድ ልቡናቸው
የጠፋ ወገኖቻችን ጌታ እመቤታችንን እንዳቃለላት (ሎቱ
ስብሐት! ወላቲ ስብሐት!) አስመስለው ይናገራሉ::
ይህንን ስእንኅን ጌታ ባለጌዎቹ እነሱም አያደርጉት::
"አባትህንና እናትህን አክብር" (ዘጸ. 20) ያለ ጌታ እንዴት
ለእናቱ ክብርን ይነፍጋል?ልቡና ይስጠን!

ወደ ጉዳያችን ስንመለስ መድኃኒታችን እንዲህ ሲል
መለስላት:: ተግባብተዋልና እመ ብርሃን አሳላፊዎቹን
"ኩሎ ዘይቤለክሙ
ግበሩ-የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" አለቻቸው:: (ዮሐ. 2:5)
ጌታም በ6ቱ ጋኖች ውሃ አስሞልቶ በተአምራት ወይን
አደረጋቸው::

+እንጀራውን ወጡን በየሥፍራው ሞላው:: ታላቅ ደስታም
ሆነ:: የአሳላፊዎቹ አለቃም (ለአባታችን አብርሃም ምሳሌ
ነው)
ከወይኑ ጥፍጥና የተነሳ አደነቀ:: በዚህም የድንግል
ማርያም አማላጅነት: የመድኃኒታችን ከሃሊነት ታወቀ:
ተገለጠ::

✞✞ ቅዱስ ያዕቆብ ርዕሰ አበው ✞✞

+የአባቶች አለቃ የተሰኘ ቅዱስ ያዕቆብ ለ2ቱ ታላላቅ
አባቶቹ እርሱ 3ተኛቸው ነው:: እነርሱን መስሎ: እነርሱንም
አህሎ በጐዳናቸው ተጉዟል:: በፈቃደ እግዚአብሔር
ብኩርናን ከኤሳው ተቀብሎ ወደ ሶርያ ሲሸሽ ቤቴል (ፍኖተ
ሎዛ) ላይ
ድንጋይ ተንተርሶ በተኛበት ግሩም ራዕይን አይቷል::

*ይህችውም የወርቅ መሰላል የድንግል ማርያም ምሳሌ
ናት::
"አንቲ ውዕቱ ሰዋስው ዘርእየ ያዕቆብ" እንዳለ ቅዱስ
ኤፍሬም (ውዳሴ ማርያም ዘሠሉስ)
*ተነስቶም "ዛቲ ይእቲ ኈኅታ ለሰማይ: ዝየ ይትሐነጽ ቤተ
እግዚአብሔር - ይህች የሰማይ ደጅ ናት: ቤተ
እግዚአብሔርም
ይታነጽባታል" ብሎ ትንቢት ተናግሯል::

+ይህ ቅዱስ አባት ለድንግል ማርያም ቅድመ አያት
ከመሆኑ ባሻገር ነቢያትን: ካህናትን: ነገሥታትንና
መሣፍንትን
ወልዷል:: ከ2ቱ ሚስቶቹ (ልያና ራሔል) : ከ2ቱ
ደንገጥሮች 12 ልጆችን ወልዷል::
*ከአጐቱ ከላባ ዘንድ ለ21 ዓመታት አገልግሎ: ሃብት
ንብረቱን ጠቅልሎ ወደ ርስቱ ከነዓን ሲመለስ ለብቻው
ራቅ ብሎ
ይጸልይ ገባ:: በዚያም እግዚአብሔር ሲታገለው አደረ::

(ይኸውም የፍቅርና የምሥጢር ነው) ለጊዜው ጌታ
ያዕቆብን
"ልቀቀኝ" ቢለው "ካልባረከኝ አለቅህም" አለው:: ጌታም
ስሙን "እሥራኤል" ብሎ ባርኮታል::
*ቅዱስ ያዕቆብ በስተእርጅና ብዙ መከራ አግኝቶታል::
ልጁን ዮሴፍን ወንድሞቹ ሽጠው "አውሬ በላው"
ብለውታልና በለቅሶ
ዐይኑ ጠፋ::

በረሃብ ምክንያትም በ130 ዓመቱ ከ75
ያህል ቤተሰቦቹ ጋር ወደ ግብጽ ወረደ:: በዚያም ለ7
ዓመታት ኑሮ
በ137 ዓመቱ ዐርፏል:: ልጆቹም ቀብረውታል::
268 views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 23:10:02 + +  +እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን እና ላለንበት ሀገር ሰላምን ይስጥልን አሜን++

መጽሐፈ ስንክሳር፣
ከዲ/ን ዮርዳኖስ ማስታወሻ

+++መልካም ዕለተ ሐሙስ መልካም በዓል።
+++
179 views20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 23:09:13
193 views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 23:08:29 ስንክሳር ዘወርሃ ጥር አሥራ አንድ(፲፩)
https://t.me/SinkisarZekidusan2
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሰን /አደረሳችሁ
176 views20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 23:07:48 =>"አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ /የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች"
1.ነቢይ
2.ሐዋርያ
3.ሰማዕት
4.ጻድቅ
5.ካሕን
6.ባሕታዊ / ገዳማዊ
7.መጥምቀ መለኮት
8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)
9.ድንግል
10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ)
11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ)
12.መምሕር ወመገሥጽ
13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ)

=>አምላከ ቅዱሳን በጥምቀቱ ይቀድሰን:: ከበረከተ ጥምቀቱም ያድለን::

=>ጥር 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት
1.በዓለ ኤጲፋንያ
2.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
3.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
4.አባ ወቅሪስ ገዳማዊ
5.አባ ዮሐንስ ሊቀ ጳጳሳት
6.ቅዱስ እንጣልዮስ ሰማዕት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.ቅድስት ሐና ቡርክት

=>"ጌታ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ:: እነሆም ሰማያት ተከፈቱ:: የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ: በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ:: እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ:- 'በእርሱ ደስ የሚለኝ: የምወደው ልጄ ይህ ነው' አለ::"
(ማቴ. ፫፥፲፮)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
130 views20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 23:07:47 Daniel:
✞ እንኳን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የጥምቀት በዓል (ኤጲፋንያ) በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✞

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

በዓለ ኤጲፋንያ

††† "ኤጲፋንያ" የሚለው ቃል ከግሪክ (ጽርዕ) ልሳን የተወሰደ ሲሆን በቁሙ "አስተርእዮ: መገለጥ" ተብሎ ይተረጐማል:: በነገረ ድኅነት ምሥጢር ግን ኤጲፋንያ ማለት "የማይታይ መለኮት የታየበት: እሳተ መለኮት በተዋሐደው ሥጋ የተገለጠበት" እንደ ማለት ነው::
"ዘኢያስተርኢ ኅቡዕ እስመ አስተርአየ ለነ::
እሳት በላዒ አምላክነ::" እንዲል:: (አርኬ)

አንድም: ምሥጢር ሆኖ የቆየ አንድነቱ: ሦስትነቱ የተገለጠበት ቀን ነውና ዕለተ ጥምቀቱ ኤጲፋንያ ይሰኛል:: መድኃኒታችን ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ያድን ዘንድ ከሰማያት ዙፋኑ ወርዶ: እንደ ሰውነቱ በሥጋ ማርያም ለ33 ዓመታት ተመላልሷል::

ጊዜው ሲደርስም በፈለገ ዮርዳኖስ: ከዮሐንስ ዘንድ ሊጠመቅ ሔደ:: መድኃኒታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የወረደው ጥር 10 ቀን አመሻሽ ላይ ሲሆን በፍጹም ትሕትና ተራ ሲጠብቅ አድሮ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ደረሰውና ሊጠመቅ ቀረበ::

አሥር ሰዓት መሆኑም ርግብ (መንፈስ ቅዱስ) ሲወርድ ሰዎች ሥጋዊት ርግብ ናት ብለው እንዳይጠራጠሩ ነው:: ርግብ በሌሊት መንቀሳቀስ አትችልምና::

መድኃኒታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ሲጠጋ አምላክነቱን ተረድቶ "እንዴት ፈጣሪየ ወደ እኔ ትመጣለህ? እንዴትስ በእኔ እጅ ትጠመቃለህ?" አለው:: ትህትና ለእናትና ልጅ ልማዳቸው ነውና:: ጌታ ግን "ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባል" ሲል እንዲያጠምቀው ፈቀደለት::

ቅዱስ ዮሐንስም "ስመ አብ በአንተ ሕልው ነው:: ስመ ወልድ ያንተ ነው:: ስመ መንፈስ ቅዱስም በአንተ ዘንድ ሕልው ነው:: በማን ስም አጠምቅሃለሁ?" ሲል ጠየቀው::

ጌታ "ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሐለነ:: አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሲመቱ ለመልከ ጼዴቅ" እያልክ አጥምቀኝ አለው:: ትርጉሙም "የቡሩክ አብ የባሕርይ ልጁ : ብርሃንን የምትገልጥ ሆይ ይቅር በለን! አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዓለም ካህኑ ነህና" እንደ ማለት ነው::

ከዚያም ጌታ ወደ ዮርዳኖስ ሲገባ ባሕር አይታ ደነገጠች : ሸሸችም:: (መዝ. 76:16, 113:3) ዮርዳኖስ ጨንቆት ግራ ቀኝ ተመላለሰ:: እሳተ መለኮት ቆሞበታልና ውኃው ፈላ:: በጌታ ትዕዛዝ ግን ጸና::

ጌታ ተጠምቆ: ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶ: ዮርዳኖስን ብርህት ማሕጸን አድርጐ: የእዳ ደብዳቤአችንንም ቀዶ ከወጣ በኋላ ሰማያት ተከፈቱ:: ማለትም አዲስ ምሥጢር ተገለጠ::

አብ በደመና ሆኖ "የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኜ ልመለክበት የመረጥኩት የባሕርይ ልጄ ይህ ነው!" ሲል በአካላዊ ቃሉ ፍጹም ተዋሕዶን መሰከረ:: መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ:: ራሱንም ቆንጠጥ አድርጐ ያዘው:: በዚህም የሥላሴ አንድነቱ: ሦስትነቱ ታወቀ: ተገለጠ::

ቅዱስ ዮሐንስ "መጥምቀ መለኮት" የሚባልበትን ታላቁን ክብር ሲያገኝ ዮርዳኖስ የልጅነት መገኛ ቅዱስ ባሕር ሆነ::

<<< ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ >>>

ቅዱስ ወንጌል ላይ ቅዱስ ሉቃስ "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ ደግሞ 100 ደርሶ ነበር::

ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕፃናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕፃን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕፃን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕፃኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

ሕፃኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

ከዚህ በኋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጄን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሐ ሰበከ: ለንስሐም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ "አጥምቀኝ" ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::

ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6)
165 views20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 21:57:09 ✞ ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ ✞

✞ እንኩዋን "ለጾመ ገሃድ" እና "አባ ታውብንስጦስ" ዓመታዊ የእረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞

+*" ጾመ ገሃድ "*+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት:: "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው:: የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ መባልዕት መከልከልን ይመለከታል::

+"7ቱ" አጽዋማት:-
1.ዓቢይ ጾም
2.ጾመ ፍልሠታ
3.ጾመ ሐዋርያት
4.ጾመ ነቢያት
5.ጾመ ድኅነት
6.ጾመ ነነዌ እና
7.ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ::

+በእነዚህ አጽዋማት ከዓቢይ ጾም በቀር እስከ 9 ሰዓት ድረስ መጾም ይገባል:: ዓቢይ ጾም ግን የተለየ ሥርዓት አለውና ይቆየን:: ስለ ጾም ሲነሳ አስቀድሞ የሚመጣው ጥያቄ አስፈላጊነቱ ነው:: "ጾም ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ ከመጠየቅ "ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ መጠየቁ ይቀላል::

+ምክንያቱም ከሃይማኖታዊ ትዕዛዛት ትልቁ በመሆኑ እርሱን መቃወም ሃይማኖትንና አዛዡን እግዚአብሔርን መቃወም ነውና:: እኛ ሃገር ላይ የተለመደች ክፉ ልማድ አለች:: የከበደችንን ነገር "አያስፈልግም" በሚል እንከራከራለን::

+ደግሞ ጾምን ለመሻር ጥቅስ የሚጠቅሱ ወገኖች በጣም ይገርሙኛል:: ኃጢአትን ለመሥራት: ጾምንም ለመሻር ጥቅስን መጥቀስ አያስፈልግም:: እኛ ግን ከፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 4:2) አበው ቅዱሳን ጾመው (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ሐዋ. 13:3, ቆሮ. 4:11) አሳይተውናልና እንደ አቅማችን እንጾማለን::

=>"ገሃድ" የሚለው ቃል በቁሙ "መገለጥን : መታየትን : ይፋ መሆንን" የሚያመለክት ሲሆን በምሥጢሩ ግን "የማይታይ አምላክ መታየቱን : የማይዳሰሰው መዳሰሱን" ያመለክታል::

+ወይም በሌላ ልሳን ወልደ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም በተዋሕዶ ሰው ከሆነ በሁዋላ ለ30 ዓመታት ራሱን ሳይገልጥ ቆይቶ ነበርና በ30 ዓመቱ ራሱን ለእሥራኤል በዚህ ሰሞን መግለጡን ልብ የምንልበት በዓል ነው::

+መድኃኒታችን ሁሉን ነገር የሚሠራው በጊዜው ነውና ከሥጋዌው በሁዋላ ለ30 ዓመታት: ከስደት መልስ ደግሞ ለ25 ዓመታት የሰውነቱን ምሥጢር በይፋ ሳይገልጥ ቆይቷል:: ያም ሆኖ የሰውነቱን ምሥጢር እርሱ: የባሕርይ አባቱና ቅዱስ መንፈሱ ለድንግል ማርያም ገልጠውላት ታውቀው ነበር:: እርሷ ግን መዝገበ ምሥጢር ናትና ሁሉን ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር:: (ሉቃ. 2:52)

+መድኃኒታችን ከሥጋዌው (ሰው ከሆነባት) ደቂቃ ጀምሮ መግቦቱን አላቁዋረጠም:: ምንም በግዕዘ ሕጻናት ቢኖርም እርሱ በዘባነ ኪሩብ የሚሠለስ ቸር ጌታ ነውና መግቦናል::

+እንደ እሥራኤል ባህል 30 ዓመት በሞላው ጊዜ ግን ሥግው አምላክ መሆኑን ገለጠ:: የተገለጠውም በጥምቀቱ ሲሆን በዕለቱ ከአብ: ከመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ ልጅነቱን አስመስክሯል:: በባሪያው በዮሐንስ እጅም ተጠምቆ ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶልናል::

+የእዳ ደብዳቤአችን ቀዶ ልጅነታችንን መልሶልናል:: ይህ ሁሉ የተደረገ ለእኛ ነውና በዓለ ኤዺፋንያን (እለተ አስተርእዮቱን) በድምቀት እናከብራለን::

+ነገር ግን ልክ በቅርብ ጊዜ እያየነው እንደሚገኘው በዘፈንና ከአምልኮ ባፈነገጠ መንገድ እንዳይሆን ቤተ ክርስቲያን አበክራ ታሳስባለች:: የመድኃኒታችንን የማዳን ሥራ ከማዘከርና ለእርሱ ከመገዛት ይልቅ ራስን ዘፈን በሚመስል መዝሙር መቃኘቱና ለልብስ ፋሽን መጨነቁ የሚጠቅም አይደለም::

+በዓላት በሚዲያ ታዩ: ተመዘገቡ ብለን ከመዝናናት ትውፊታችንን እያጠፉ ያሉ ድርጊቶቻችን ብንታዘባቸውና ብናርማቸው ይመረጣል:: ስኬታችን ሁሉም ክርስቲያን ለእግዚአብሔር መንግስት መብቃቱ እንጂ በዓል አከባበራችን ዝነኛ መሆኑ አይደለም::

+ጉዳዩ መለኮታዊ እንጂ ፓለቲካዊ አይደለምና ጥንቃቄን ይሻል:: ዛሬ ለታቦተ እግዚአብሔር ክብርን የማይሰጥና ተጋፊ ትውልድን እየፈጠርን ነው:: ካህናትን አለመስማትና ታቦታትን አግቶ አላስገባም ማለት በክርስትና ትርጉሙ ከሰይጣን መወዳጀት ነው:: ስለዚህም በዓል አከከባበራችንን እንታዘብ:: ደግሞም እናርመው::

+*" ጾመ ገሃድ "*+

=>ቤተ ክርስቲያን ጾመ ገሃድን የደነገገች ለ3 ምክንያት ነው:-

1.የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጥሙና እያሰብን በጾም እንድናመልከው::
2.በዓል አከባበራችን እንደ አሕዛብ በተድላ ሥጋ: በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳይሆንና ሰውነታችንን በጾም እንድንገራው::
3.ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዐርብ ሲውሉ እህል በነግህ (በጧት) መቀመስ ስላለበት የእርሱ ቅያሪ (ተውላጥ) እንዲሆን ነው::

+ጾመ ገሃድን የሠሩት አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ ያጸኑት ደግሞ ቅዱሳን ሊቃውንት ናቸው:: አጿጿሙም ጥምቀት ከማክሰኞ እስከ ቅዳሜ ከዋለ በዋዜማው "እስከ ይሠርቅ ኮከብ" እንዲሉ አበው እስከ ምሽት 1 ሰዓት ድረስ ይጾማል::

+በዓለ ጥምቀት እሑድ ሲሆን ዐርብን አዘክሮ: በዕለተ ቅዳሜ ደግሞ ከጥሉላት ተከልክሎ መዋል ይገባል:: በመሳሳይ ሰኞ ቢውል ዐርብን አዘክሮ: ቅዳሜና እሑድን ከጥሉላት (ከሚያገድፉ ምግቦች) ሁሉ ተከልክሎ መዋል ይገባል::

+ከ7ቱ አጽዋማት አንዱ ነውና የተለየ ግለሰባዊ ችግር እስከሌለ ድረስ ሊጾም ግድ ይላል:: ችግር ካለ ደግሞ ከንስሃ አባት ጋር ሊመክሩ ይገባል::

+*" አባ ታውብንስጦስ ዘሲሐት "*+

=>በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም የተነሳ
+ከልጅነቱ መጻሕፍትን የተማረ:
+በክህነት አገልግሎቱ ለብዙዎች አባት የሆነ:
+በምናኔ ወደ ግብጽ የወረደ:

+በእስክንድርያ አካባቢ አበ ምኔት ሆኖ ብዙ መነኮሳትን የመራ::
+በዘመነ ሰማዕታት የተሰደደ:
+ብዙ አሕጉራትን ዞሮ ያስተማረ:

+በትምሕርተ ክርስቶስ ያላመኑትን አሳምኖ : ያመኑትን ያጸና:
+ሽፍቶችን እየገሠጸ ለንስሃ ያበቃ የነበረ ታላቅ አባት ነው::

+በዘመነ ሰማዕታት ስደትን ታግሦ: በሁዋላም በደብረ ሲሐት ተወስኖ ኑሯል:: በዚህች ቀንም በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::
=>አምላከ ቅዱሳን ፍቅሩን: ምሥጢሩን ይግለጥልን:: ከጾመ ገሃድ በረከትም አይለየን::

=>ጥር 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ጾመ ገሃድ
2.አባ ታውብንስጦስ ዘሲሐት
3.ቅዱስ ኪናርያ
4.ቅድስት ጠምያኒ

=>ወርሐዊ በዓላት

1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
7.ቅዱስ እፀ መስቀል

=>+"+ እነርሱ እሥራኤላውያን ናቸውና:: ልጅነትና ክብር: ኪዳንም: የሕግም መሰጠት: የመቅደስም ሥርዓት: የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና:: አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና:: ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ:: እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው:: አሜን:: +"+ (ሮሜ. 9:4)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
1.4K views18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 07:24:40 + +  +እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን እና ላለንበት ሀገር ሰላምን ይስጥልን አሜን++

መጽሐፈ ስንክሳር፣
ከዲ/ን ዮርዳኖስ ማስታወሻ

+++መልካም ዕለተ ማክሰኞ መልካም ቀን።
+++
383 views04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 07:24:31
384 views04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ