Get Mystery Box with random crypto!

✞ገድለ ቅዱሳን✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ kegdlat — ✞ገድለ ቅዱሳን✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ kegdlat — ✞ገድለ ቅዱሳን✞
የሰርጥ አድራሻ: @kegdlat
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.13K
የሰርጥ መግለጫ

✝✞ከኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክ ላይ የተገኙ የየዕለቱ የቅዱሳን አባቶቻችን እና የቅዱሳት እናቶቻችን ገድል ይነገርበታል✝

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2023-02-04 19:53:06 ስንክሳር ዘወርሃ ጥር ሃያ ሰባት(፳፯)
https://t.me/SinkisarZekidusan2
778 views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 19:52:54 † † እንኳን ለጌታችን አማኑኤል ክርስቶስ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † †

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

ተአምረ እግዚእ

††† "ተአምር" የሚለውን ቃል በቁሙ "ምልክት" ብሎ መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ): ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር ይባላል::

ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው:: ስለዚህም ነው "ኤልሻዳይ - ከሐሌ ኩሉ - ሁሉን ቻይ" እያልን የምንጠራው::

እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ (ኦሪትን ተመልከት) እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ (1 ነገሥት) እንደ ነበር ይታወቃል::

እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: (ማቴ. 10:8, 17:20, ማር. 16:17, ሉቃ. 10:17, ዮሐ. 14:12)

እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: (ሐዋ. 3:6, 5:1, 5:12, 8:6, 9:33-43, 14:8, 19:11)

††† ተአምራተ እግዚእ †††

††† ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: እያንዳንዱ ግን ቢጻፍ ዓለም ለራሷ ባልበቃች ነበር:: ከእነዚህ መካከልም አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው በዚህ ዕለት በ7 እንጀራ እና በጥቂት ዓሣ ሴቶችና ሕፃናትን ሳይጨምር 4,000 ሰዎችን በቸርነቱ አበርክቶ አጥግቡዋል:: ደቀ መዛሙርቱም 7 ቅርጫት ማዕድ አንስተዋል::

ጌታችን በከሃሊነቱ የተራቡትን ሲያጠግብ እንዲሁ አይደለም:: በጊዜው የነበሩ አይሁድ ጠማሞች ነበሩና እነሱን ምላሽ በሚያሳጣ መንገድ ነበር እንጂ:: አይሁድ ላለማመን ብዙ ጥረት ነበራቸውና::

በዚህ ዕለትም እንጀራውን አበርክቶ ሲያበላቸው:-
1.ጊዜው አመሻሽ ላይ ነበር:: ምክንያት:- ጧት ላይ ቢሆን ከቤታችን የበላነው ሳይጐድል ብለው ከማመን ይርቁ ነበርና::

2.ከውሃ ዳር አድርጐታል:: መታጠቢያ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን እንዳይሉ::

3.ሳር የበዛበት ቦታ ላይ አድርጐታል:: ምክንያቱም መቀመጫ ብናጣ በደንብ ሳንበላ ቀረን እንዳይሉ::

4.ከከተማ አርቆ ምድረ በዳ ላይ አድርጐታል:: ያማ ባይሆን "ፈጣን: ፈጣን ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው እየገዙ አቀረቡለት" ባሉ ነበርና::

††† ለመድኃኒታችን ክርስቶስ አምልኮና ምስጋና ይሁን!
አማኑኤል አምላካችን ጣዕመ ፍቅሩን ያሳድርብን::

††† ጥር 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሰማዕት (ስለ ሃይማኖት 7 ጊዜ ሙቶ የተነሳ, 7 አክሊል የወረደለት)
2.ቅዱስ አካውህ መነኮስ
3."800" ሰማዕታት
4.ቅዱስ ዮሴፍ አይሁዳዊ (የእመቤታችን ወዳጅ)
5.ቅድስት ሳቤላ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባቶቻችን አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ
2.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ

††† "ጌታ ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ:- ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስከ አሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለ ሌላቸው አዝንላቸዋለሁ:: በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም' አላቸው::
ደቀ መዛሙርቱም:- 'ይህን ያህል ሕዝብ የሚያጠግብ ይህን ያህል እንጀራ በምድረ በዳ ከወዴት እናገኛለን?' አሉት:: ጌታ ኢየሱስም:- 'ስንት እንጀራ አላችሁ?' አላቸው:: እነርሱም:- 'ሰባት: ጥቂትም ትንሽ ዓሣ' አሉት::
ሕዝቡም በምድር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ:: ሰባቱንም እንጀራ: ዓሣውንም ይዞ አመሰገነ:: ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ:: ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ:: ሁሉም በሉና ጠገቡ:: የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰባት ቅርጫት ሙሉ አነሱ:: የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ::" †††
(ማቴ. 15:32)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
1.1K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 14:36:52 Channel photo updated
11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 05:54:22 + +  +እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን እና ላለንበት ሀገር ሰላምን ይስጥልን አሜን++

መጽሐፈ ስንክሳር፣
ከዲ/ን ዮርዳኖስ ማስታወሻ

+++መልካም ዕለተ አርብ መልካም ቀን።
+++
1.3K views02:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 05:52:43
1.3K views02:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 05:52:35 ስንክሳር ዘወርሃ ጥር ሃያ ስድስት(፳፮)
https://t.me/SinkisarZekidusan2
966 views02:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 05:52:29 † † እንኳን ለቅዱሳን አርባ ዘጠኝ አረጋውያን ሰማዕታት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † †

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አረጋውያን ሰማዕታት †††

††† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን
ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

የእነዚህ ሰማዕታት ቁጥራቸው 49 ሲሆን አባ ቢስዱራ የሚባል ጻድቅ ሰው 50ኛ ሁኖ ይመራቸው ነበር:: መኖሪያቸው ገዳመ አስቄጥስ (ግብጽ) ሆኖ ዘመኑ 5ኛው መቶ ክ/ዘ ነበር::

ሃምሳውም ሙሉ ዘመናቸውን በምናኔና በቅድስና ፈጽመው በስተእርጅና ደግሞ ሰማዕትነት መጣላቸው:: በ430ዎቹ አካባቢ
የዚያን ጊዜ በርበር ይባሉ የነበሩት አረማውያኑ (የዛሬዎቹ አሕዛብ አባቶች) "ሃይማኖት ካዱ" እያሉ ሰይፍን መዘዙባቸው::

በጊዜው አባ ቢስዱራ በማረፉ ሃላፊነቱን የወሰዱት አባ ዮሐንስ ከአርባ ስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ተስማምተው በበርበር እጅ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል:: ከንጉስ ቴዎዶስዮስ (ትንሹ) ተልኮ የነበረ አንድ ክርስቲያንም በፍቅረ ክርስቶስ ተስቦ ከወጣት ልጁ ጋር ተሰይፏል:: የብርሃን አክሊልም ለሃምሳ አንዱም ወርዷል::

††† አምላከ ቅዱሳን ከተከፈተ ገነት : ከተነጠፈ ዕረፍት በቸርነቱ ያድርሰን::

††† ጥር 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አርባ ዘጠኝ አረጋውያን ሰማዕታት (ግብጽ ገዳመ አስቄጥስ ውስጥ)
2.ቅድስት አንስጣስያ (በ5ኛው መቶ ክ/ዘ ከቁስጥንጥንያ ወደ ግብጽ ወርዳ ፡ ንግሥናን ንቃ በበርሃ ስትጋደል የኖረች ቅድስት
እናት ናት::)
3.ቅዱስ ዮሴፍ (መፍቀሬ ነዳያን)
4.አባ ጽሕማ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ኢትዮጵያዊ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ
ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን? 'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን' ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" †††
(ሮሜ. ፰፥፴፭-፴፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
1.0K views02:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 07:20:59 + +  +እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን እና ላለንበት ሀገር ሰላምን ይስጥልን አሜን++

መጽሐፈ ስንክሳር፣
ከዲ/ን ዮርዳኖስ ማስታወሻ

+++መልካም ዕለተ ሐሙስ መልካም ቀን።
+++
1.2K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 07:20:13
1.2K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 07:19:49 ገድለ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
https://t.me/SinkisarZekidusan2
1.1K views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ