2023-02-10 08:01:11
✞ ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ ✞
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
❖ የካቲት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+" ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ "+
+እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም
የተወለደው ንጽቢን በምትባል የሶርያ ግዛት ውስጥ
በ298 / 306
ዓ/ም ነው:: ወላጆቹ በክርስቶስ የማያምኑ አላውያን
ነበሩ:: (ምንም አንዳንድ ምንጮች ክርስቲያኖች ነበሩ
ቢሉም)
+ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ንጽቢን ዽዽስናን የተሾመ
ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር:: የሰማዕትነት:
የሐዋርያነት: የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት
ነው:: ታዲያ ቅዱስ ኤፍሬም ይሔ አባት ሁሌ ሲያስተምር
ይሰማው
ነበርና በስብከቱ ተማርኮ ደቀ መዝሙሩ ለመሆን በቃ::
+ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱስ ያዕቆብ እጅ ከተጠመቀ በሁዋላ
ሙሉ የጣትነት ጊዜውን ያሳለፈው በትምሕርት ነው::
የሚገርመው
መምሕሩ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን እመቤታችን ድንግል
ማርያምን በፍጹም ልቡ የሚወድና ጠርቷት የማይጠግብ
አባት ነውና ለልጁ
ለቅዱስ ኤፍሬም ይሕንኑ አጥብቆ አስተምሮታል::
+ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን ሲመረምር የእመቤታችን
ፍቅር ይበዛለት ጀመር:: ምክንያቱም እመ ብርሃንን
ሳይወዱ ክርስትና
የለምና:: እንደ እርሱ የሚወዳት የለም እስኪባል ድረስ
ያገለግላት: ይገዛላትም ገባ::
+እንዲህ እንደ ዛሬ የድንግል ማርያም ምስጋና በአንደበት
እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበር:: እርሱ ግን ከወንጌለ
ሉቃስ
በስድስተኛው ወርን (ይዌድስዋን) እና ጸሎተ ማርያምን
(ታዐብዮን) አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ 64 64
ጊዜ
ያመሰግናት ነበር::
+በእንዲህ ያለ ግብር እያለ አርዮስ በመካዱ እርሱን
ለማውገዝና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማጽናት በ317 /
325
ዓ/ም 318ቱ ሊቃውንት በኒቅያ ሲሰበሰቡ አንዱ መምሕረ
ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ
ኤፍሬም
ከሊቃውንቱ ትምሕርትና በረከትን አግኝቷል::
+ከጉባዔ መልስ መንገድ ላይ በራዕይ የብርሃን ምሰሶ
አይቶ "ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ "ይህማ
ታላቁ ቅዱስ
ባስልዮስ ነው" አለው:: እርሱም መምሕሩን ቅዱስ
ያዕቆብን ተሰናብቶ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ (ቂሣርያ) ወረደ::
ተገናኝተውም በአንድ ሌሊት ቁዋንቁዋ ተገልጦላቸው
ሲጨዋወቱ አድረዋል::
+በቦታው ብዙ ተአምራት ተደርጉዋል:: ቅዱስ ኤፍሬም
ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በሁዋላ ሃገረ ስብከት
ተሰጥቶት ያስተምር
ጀመር:: ሁል ጊዜ ታዲያ ጸሎቱ ይሔው ነበር:: "እመቤቴ
ሆይ! ምስጋናሽ እንደ ሰማይ ከዋክብት: እንደ ባሕር አሽዋ
በዝቶልኝ: እንደ እንጀራ ተመግቤው: እንደ ውሃ ጠጥቼው:
እንደ ልብስም ተጐናጽፌው" እያለ ይመኝ ነበር::
+አፍጣኒተ ረድኤት: ፈጻሚተ ፈቃድ እመ ብርሃንም በገሃድ
ተገልጻ የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት:: ዛሬ ጸጋ በረከት
የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት:: ሲደርስላትም
እርሷ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ
ወርዳ:
በፊቱም ተቀምጣ ሲሆን እርሱ ደግሞ ባጭር ታጥቆ:
በፊቷ ቆሞ: በመንፈስ ቅዱስም ተቃኝቶ ነው::
+ውዳሴዋን በ7 ቀናት ከደረሰላት በሁዋላ በብርሃን
መስቀል ባርካው: ሊቀ ሊቃውንትም እንዲሆን ምስጢር
ገልጣለት
ዐረገች:: ከዚህ በኋላ በምስጢር ባሕር ውስጥ ዋኝቶ 14
ሺህ ድርሰቶችንም ደርሷል:: ዛሬ ሶርያ ውስጥ
የምንሰማውን
ዜማም የደረሰው ይህ ቅዱስ ነው::
+እንዲያውም አንድ ቀን የምሥጢር ማዕበል ቢያማታው
"አሃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" ብሎ ጸልዩዋል:: (የጸጋህን
ማዕበል
ያዝልኝ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
በመጨረሻ ሕይወቱ ተክሪት በምትባል ሃገር ኤዺስ ቆዾስ
ሆኖ ተሹሟል::
+በጣፋጭ ስብከቱ ብዙዎችን ካለማመን መልሷል:
የምዕመናንንም ሕይወት አጣፍጧል:: ለመናፍቃንና
ለአርዮሳውያን ግን
የማይጋፉት ግድግዳ ሆኖባቸው ኑሯል:: በዘመኑም ብዙ
ተጋድሎ አፍርቷል: ተአምራትንም ሠርቷል:: በተወለደ
በ67 ዓመቱ
በ365 / 373 ዓ/ም ዐርፎ ተቀብሯል::
+ቅዱሱ ለሶርያ ብቻ ሳይሆን እመቤታችንን ለምንወድ
የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ሞገሳችን ሆኗል:: ስለዚህም
እንዲህ እያልን
እንጠራዋለን:-
1.ቅዱስ ኤፍሬም
2.ማሪ ኤፍሬም
3.አፈ በረከት ኤፍሬም
4.ሊቀ ሊቃውንት
ኤፍሬም
5.ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም
6.አበ ምዕመናን
ኤፍሬም
7.ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን አንተ ነህ::
❖የካቲት ፫ ቀን ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የፍልሠት በዓሉ ነው፡፡
✞ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን
ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን:
አእምሮውን: ለብዎውን
በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::
+" አባ ያዕቆብ ገዳማዊ "+
+ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት "ለስሒት መኑ ይሌብዋ-
ስሕተትን ማን ያስተውላታል" (መዝ) ሲል የተናገረው
ይፈጸም ዘንድ ይህ
ታላቅ ቅዱስ ሰው በኃጢአት ብዙ ተፈተነ:: ወደ በርሃ
ወጥቶ: በምናኔ ጸንቶ: በጾምና በጸሎት ተግቶ ዘመናትን
ስላሳለፈ
ሰይጣንን አሳፈረው::
+ግን ደግሞ ክፉ ጠላት ባልጠረጠረው መንገድ መጥቶ
መከራ ውስጥ ከተተው:: የአገረ ገዢው ልጅ ታማ
"ፈውሳት" አሉት:
ፈወሳት:: ወደ ቤቷ ስትመለስ ግን አመማት:: "ከአንተ ጋር
ትቆይ" ብለው ትተዋት ቢሔዱ ከመለማመድ የተነሳ
በዝሙት
ወደቀ::
+እንዳይገለጥበት ስለ ፈራም ገደላት:: በሆነው ነገር
ተስፋ ቆርጦ ወደ ዓለም ሲመለስ: ቸር ፈጣሪ የሚናዝዝ
አባትን ልኮ
ንስሃ ሰጠው:: ጉድጓድ ምሶ: ድንጋይ ተንተርሶ ለ30
ዓመታት አለቀሰ:: እግዚአብሔርም ምሮት: የቀደመ
ጸጋውን
ቢመልስለት: ዝናምን አዝንሞ ሕዝቡን ከእልቂት ታድጓል::
በዚህች ዕለት ዐርፎም ለርስቱ በቅቷል::
+" ታላቁ አባ ዕብሎይ "+
+ይህ ቅዱስ የአቡነ አቢብ ደቀ መዝሙር ሲሆን በዚህ
ስም ከሚጠሩ ቅዱሳንም ቀዳሚው ነው:: ብዙ መጻሕፍት
'ርዕሰ
ገዳማውያን' ይሉታል:: የቅዱሱ ተጋድሎ እጅግ ሰፊ ነው::
✞የካቲት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት-በዓለ ፍልሠቱ)
2.ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ (ሕይወቱ መላዕክትን
የመሰለ ግብፃዊ አባት)
3.አባ ያዕቆብ መስተጋድል
++"+ ለምኑ ይሰጣችሁማል:: ፈልጉ ታገኙማላችሁ::
መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል:: የሚለምነው ሁሉ
ይቀበላልና::
የሚፈልገውም ያገኛል:: መዝጊያንም ለሚያንኳኳ
ይከፈትለታል:: +"+ (ማቴ. 7:7)
++"+ የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::አንደበቱም
ፍርድን ይናገራል::የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም
አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 37:30)
✞ ✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞ ✞
448 views05:01