Get Mystery Box with random crypto!

"ቃለ እግዚአብሔር "

የቴሌግራም ቻናል አርማ kaleegziabeher — "ቃለ እግዚአብሔር "
የቴሌግራም ቻናል አርማ kaleegziabeher — "ቃለ እግዚአብሔር "
የሰርጥ አድራሻ: @kaleegziabeher
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.12K
የሰርጥ መግለጫ

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16
"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-07-03 15:25:01 ከሀሰተኛ አጥማቂዎች እንጠንቀቅ! እባካችሁ ሁሉንም እንመርምር!



2.5K viewsedited  12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 20:57:41 ይኸውላችሁ የፍቅር ግንኙነትና ጉዞ ከእግዚአብሔር አምላክ በኩል ካልጀመረ ዋጋ የለውም፡፡ ይልቁን መጥፍያችን እስከሚሆን ድረስ ልንፈተንበትም እንችላለን፡፡ አባት እናቶቻችን ዘመናትን በአምልኮ በኩል ተጠብቀው የኖሩበትን ፍቅርና የትዳር ሕይወት እኛ ለማጣጣም አልታደልንም፡፡ ለምን? ዓይነጥላ ቀድሟላ፡፡ ፍቅረ ንዋይን ከልብ ውስጥ አስቀድሞ ተሽቀዳድሞ ሄዶ ያስቀምጥና በፍልስፍናና ከአምላክ በራቀ ፖሊሲ የፍቅር ህይወታችን እንዲጓዝ ያደርገዋል፡፡
በትጋት እንዳል ይ
2.5K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 20:57:41 ተግተን እንጸልይ


             የዓይነጥላ መንፈስ

የዓይነጥላ መንፈስ ከስሙ እንደምንገነዘበው በሚኖረን ኑሮ ዕድል በረከትና ጸጋ ላይ ጥላ የሚሆን ማለት ነው፡፡ የሚጋርድ የሚከልል ማለት ነው፡፡ በምናየው በምንገነዘበውና በሚኖረን መንገዳችን ላይ #አሸምቆና_ተደብቆ ጉዳት የሚያደርስብን አጥፊ የዲያቢሎስ ምሪት ነው፡፡
የዓይነጥላ መንፈስ ራሱን ማሸመቅና ባህሪን ተመሳስሎ መኖር መቻሉ ትልቁ መገለጫው ሲሆን የወደፊት እድላችንን አስቀድሞ ተረድቶ መዝጋት የሚችልና አርቆ በማየት የጥፋት እቅዶችን ቀርፆና ነድፎ የሚያጠፋ አደገኛ ጠላት ነው፡፡
ከፊት በመቅደም የሰው ልጆችን እድል የሚዘጋና ተስፋን የሚያስሟጥጥ፤ ተምረን ተምረን ሰርተን ደክመን ያቆየነውን ሁሉ ከንቱ የሚያደርግ በጣም ክፉ መንፈስ ነው፡፡ በተለይ ተመሳስሎ የመኖር አቅሙና ስልቱ ለጉዳት ጉዞው በጣም የሚያመቸው ሲሆን ከውስጥ ስለማድፈጡ ምንም መረጃ ሳይሰጥ በኑሮአችን፣ በሥራችንና በእውቀታችን ወዘተ... ላይ ሁሉ ዕንቅፋት በመሆን የሚያሰናክልና የሚያጨናግፍ ርኩስ መንፈስ ነው፡፡ ዓይነ ጥላ የምናስበውና የምናቅደው ከውስጥ ወደ ውጪ የምንመዘግበውን፤ በትምህርታችንና በስራችን የምናገኘውን ፍሬዎችና ውጤቶች ላይ በሙሉ አትኩሮቱ በማረፍ በየዕለቱ ወደፊቶቻችንን የሚከታተል መንፈስ ነው፡፡

የዓይነጥላ መንፈስ ከውጫዊ የአካላችን ጤንነት ጋር እምብዛም ጉዳይ የለውም፡፡ እጅ እግር ወገብ አይዝም፡፡ ይልቁን የእርሱ ጉዳይ አዕምሮ እና ልብ ላይ ገብቶ ማስጨነቅና የውስጥ ስቃይ መፍጠሩ ላይ ነው፡፡ የስኬት አቅጣጫና መንገዶቻችንን በአስቀድሞ መረዳት ችሎታው ስለሚያውቀው እድሎቻችንንና በረከቶቻችን ላይ በመቆም መሠረታዊ የሆነ ጥፋትና ውድመትን ያስከትላል፡፡ ከዛ ዋነኛ ጉዳት በኋላ እንዳለ ተያያዥ የሕይወት መስመሮቻችንና አካሄዳችን ስለሚዛነፉና ስለሚበላሹ እቅዱና ፖሮግራሙን ማሳካቱን ያረጋግጣል ማለት ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ እንደዛርና መተት ያሉ ሌሎች መናፍስታንንን በመጎተትና ከውስጣችን ስፍራና ቦታ በማደላደል ካስቀመጣቸው በኋላ የጥፋት መሠረቱን የሚያመቻችና በነጠረ ስልት ከፍተኛ ጉዳት በሰው ልጆች ትውልዶች ላይ አደጋ ይጥላል፡፡

የዓይነጥላ መንፈስ በጣም ብልጣብልጥና ጠንቃቃ መንፈስ ነው፡፡ ያረፈበትን ሰው ጠባይና የውስጥ አመል በጥንቃቄ ይቃኛል፥ ይመረምራል፡፡ በመቀጠል ሰውዬው የደከመበትን ጎን በማጤን ቀስ እያለ ይቆራኘዋል፡፡ በመቀጠል ጠባዩና አመሉን በመዋረስ አንድ እስከሚሆን ድረስ ይመሳሰላል፡፡ በመቀጠል ከሰውየው ጋር ረጅም ዓመታትን በመኖር አከባቢውን እየቃኘ የወደፊት እድሎቹን በማጥናት በመተንበይ ቀድሞ ሄዶ አደጋ ያዘጋጃል ማለት ነው፡፡
ሌላው መንፈሱ የሚይዛቸው ሰዎች ሌሎች ብዙ ሰዎችን ማሰናከልና ማጥፋት የሚችሉ ከሆነ ምንም አይነካቸውም፡፡ እንደውም በሥልጣንና በማዕረግ ያነሣቸዋል፡፡ በሥጋዊ እውቀቶችና የርዕዮተ ዓለም ንድፈ አሳቦች ሰውዬውን በማበልፀግ ሌሎች ሰዎችን እንዲያስቱና ክፉ እንዲያደርጉባቸው አሳብ በሚማርክ ገፅታና አቋም ፖሊሲ ይቀርፃል፡፡ እየተከታተለ ያስፈፅማል፡፡ እነዚህም ሰዎች ለጊዜው ሌሎችን ስለሚጎዱለትና የክፋት ምሪታቸውን እንደ ግብሩ በመቁጠር ከፍ ከፍ ያረጋቸዋል፡፡ የሚገርመው ግን የኃላ የኃላ ራሱ በሰጣቸው ታላቅነትና ክብር ቀንቶ ያጠፋቸዋል፡፡

ሌላው የዓይነጥላ መንፈስ የሚኖረው ጠባይና አካሄድ ካደረበት ሰው ተነስቶ ወደ ሌላ ሰው ገብቶ ያለንንና የሚኖረን ገፅታና መልካም ስም ማርከስና ማጥፋት መቻሉ ነው፡፡ ለምሳሌ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ እናት ላይ ያረፈ አይነጥላ ከልጆቿ ጋር ከባለቤቷ ጋር እያላተመ ሰላማቸውን በማናጋት የምሬት ኑሮ እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡
❖ ስለዚህም ነው ጸሎትን እንደ ቤተሰብ በጋራ መጸለይን መለማመድ ያለብን፡፡

በአጠቃላይ አንክሮ ልንሰጠው የሚገባው ትልቁ ነጥብ
  ዓይነጥላ አእምሮንና ልቦና ውስጥ እንደሚቀመጥ
  ከሕሊናችና ከጠባያችን ጋር ተመሳስሎ እንደሚኖር
  የወደፊት እድሎቻችንንና መንገዶቻችንን ቀድሞ ተረድቶ አደጋ አዘጋጅቶ የሚጠብቅ መሆኑን
ማስተዋልና ማጤን ያስፈልገናል
የዓይነጥላ መንፈስ በዋነኛነት ሁለት አይነት የውጊያ ስምሪቶች አሉት፡፡
➊ ዕንቅፋት መፍጠር ፡
ዓይነጥላ የሰው ልጆችን አኗኗር በመለማመድ የወደፊት እድሎችንና ጉዞዎችን የማጤንና አርቆ የማየት ችሎታ አለው፡፡ በዚህም ችሎታው በኩል አልፎን ይሄድና መንገዳችን ላይ አደጋና ጥፋት አዘጋጅቶ እንቅፋት ሆኖ ይጠብቅሃል፡፡ ለምሳሌ ልክ መኪና እያሽከረኸራችሁ ቢሆን በመንገዳችሁ ላይ አደናቃፊ ድንጋይ ወይ ሌላ እከል እንደማስቀመጥ ማለት ነው
➋ ጥሩ ውጤትን ማበላሸት ፡
እንደምንም ብለህ እንኳ ቀድሞ ያስቀመጠልህን እንቅፋቶች ተቋቁመህ አልፈህ ጥሩ ውጤት ብታመጣ፤ ባስገኘኸው መልካም ፍሬ ላይ ሄዶ በማረፍ የድካምህን ውጤት ከንቱ ያደርገዋል

         የዓይነጥላ መንፈስ የሚገልጣቸው ጠባያት

ትምህርትና ስራህ ሁሉ እያደር ሲያሽቆለቁል ወይም ለፍተህ ለፍተህ በረከቶችህ ሲርቁህና ሲጠፉ
ስኬትን የምታገኝባቸው ዕድሎች ያለምንም በቂ ሁናቴ መበላሸትና ለዘመናት የለፋህበት ነገር መና እየሆነ ሲቸግርህ
የትከሻ መክበድና መጫጫን ድንገተኛ መበርገግና በቁም መቃዠት.. አንዳንዴ ምን ነካኝ እስክንል ድረስ በፊት በምንታወቅባቸው ነገሮች ላይ መልፈስፈስ፡፡ ለምሳሌ እንግዲ ጎበዙ ተማሪ ትምህርቱ ሁሉ ሸክምና የማይገፋ ተራራ ሲሆንበት
በኢንተርኔትና ሌሎች የወሲብ ሱሶች መጠመድና ተደጋጋሚ ህልመ ለሊት ማስተናገድ በተለይ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ባቀድንባቸውጊዜያት
የውስጥ ጭንቀትና የአሳብ መዘበራረቅና መበታተን ግራ መጋባትና ከውስጥ የሚገፋ የተስፋ መቁረጥ ስሜት
የገንዘብና ንብረት መባከንና መጥፋት፤ እራሳችንን እስክንታዘብ ድረስ ለአስፈላጊ ነገሮች ጊዜን፣ ጉልበትንና ገንዘንብን መጨረስ
በማትጠብቀው ሁኔታና አቅጣጫ ዙሪያህ ካሉት ሰዎች ጋር መግግባት ሲያቅትህና ወዘተ..
ሌሎች የአሳብና የሕይወት ጦርነቶች ከዚሁ የዓይነጥላ መንፈስ የሚነሱ የክፋቱ መግለጫ ባህሪያቶቹ ናቸው፡፡

           የዓይነጥላ መንፈስ በትዳርና ፍቅር ውስጥ በባለትዳሮች ሕይወት ውስጥ ራእይ ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አምላክ የቤት ውስጥ አምልኮ (የዘወትር ጸሎትና ስግደት) ከሌለ የዓይነ ጥላ መንፈስ በየተናጠል ባለትዳሮቹ ላይ ያርፍባቸዋል፡፡

ሴቷ ላይ ማራኪ ወንድ ሆኖ በገሀዷም በህልሟም እየመጣ አብሯት ይሆናል፡፡ ሩካቤ ይፈፅማል፡፡ በአንፃሩ በወንዱም ላይ የሚፈልገውን አይነት የሴት ገፅታ ተላብሶ ሚስቱ ይሆናል፡፡ ይህን ፆታ ቀይሮ የማረፍ ስልትና አካሄድ  የዛር መንፈስም ይጠቀምበታል፡፡
ከዛ በኃላ በቃ መበጣበጥ ነው፡፡ መረባበሽ ነው፡፡ ትዳርን መናድ ነው፡፡ በተለይ በለሊት እየመጣ የሚገናኛቸው ጉዳይ ባለትዳሮቹን በጣም ስለሚረብሻቸው ከውስጥ በእጅጉ ማስጨነቅና ተፈጥሯዊው የግንኙነት ስሜትን በማሳጣት የፍቅር ሕይወታቸውን ከንቱ ያደርገዋል!
2.4K viewsedited  17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 00:48:10 *ተአምር**
ይህ የእመቤታችንን ድንቅ ተአምር የተነገረው በግቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሲሆን ነገሩም እንዲህ ነው::
“እማየ” ብሎ ጠራኝ እኔም “አቤት” አልኩት “ጆሮወቼ ሰሙልኝ” አለኝ፡፡ እኔም “ልብህ ቢሰማ ነውንጅ የሚሻለው” አልኩት፡
ይህ የእመቤታችንን ድንቅ ተአምር የተነገረው ትናንት ነሃሴ 19/2003 በግቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የማታ ጉባኤ ሲሆን ነገሩም እንዲህ ነው ፦ ተአምሩን የመሰከሩት አንዲት እናት ሲሆኑ “የእመቤቴን ስም እየጠራሁ ያለአባት ያሳደግኩት ልጅ ነበርኝ ፡ እኔም ልጄም እመቤታችንን በጣም እንወድ ነበረ ፡ ያለአባት በእመቤቴ ስም ያሳደኩት ልጄ ተምሮልኝ ጥሩ ስራ ያዘልኝ ፡ በዚህ ደስ ብሎኝ ሳለ ልጄ በስራ ቦታ ካልሆኑ ልጆች ጋር ገጥሞ አዲስ ነገርን ተማረብኝ ፡ አንድ ቀን ማታ ሲመጣ “ እናቴ ሆይ ጌታን ተቀበይ” አለኝ ይህን ሲለኝ ደነገጥኩ “እመቤታችንስ” ስለው “ዙሪያ ጥምጥም መሄዱ ይበቃናል አንቺም እኔም ጌታን መቀበል አለብን” አለኝ ፡ እኔም ጧት ማታ አለቅስ ጀመር ፡ ለልጄም ይህ የነፍስ በሽታ ለስጋውም ተርፎ ሁለቱ ጆሮወቹ አልሰማም አሉት፡፡ በዚህም የተነሳ ጴንጤወች እንፀልይልህ ብለው በአዳራሻቸው ወሰዱት ፡ ጆሮወቼ ይድኑ ይሆን ብሎ ተስፋ ያደረገው ልጄም ይባስ ብሎ ሁለቱም አይኖቹ ጠፉ ፡ ከዚህ በኅላ እቤት ተኛ ፡ እኔም እያለቀስኩ እኖር ነበር፡፡ አስቡት ጆሮውንኳ ባይሰማ አይን ቢኖረው እንግባባ ነበር ፡ ወይንም አይኑ ባይኖርና ጆሮው ቢሰማ በድምፅ እንግባባ ነበር አሁን ግን እጅግ ችግር ሆነብኝ፡፡ ከሁሉ የሚያስጨንቀኝ ግን እመቤቴን መክዳቱ ነበር፡፡
አንድ ቀን ቤተክርስቲያን ምስክርነት ሲሰጥ ሰምቼ እኔም በሃይላንድ ፀበል ይዜ ወደቤት ሄድኩኝ፡፡ በሁለቱ ጆሮወቹ ፀበሉን አፈሰስኩበት፡፡ የእመቤቴ ስእል ፊትም ተንበርክኬ “እመቤቴ ሆይ ጆሮውም አይስማ ፡ አይኑም አይይ ፡ ነገር ግን ልቡን መልሺልኝ” እያልኩ አልቅሼ ፀልየ ወደ መኝታየ ሄድኩኝ ሌሊት 10፡00 ላይ ልጄ “እማየ” ብሎ ጠራኝ እኔም “አቤት” አልኩት “ጆሮወቼ ሰሙልኝ” አለኝ፡፡ እኔም “ልብህ ቢሰማ ነውንጅ የሚሻለው” አልኩት፡፡ አሁንም ትንሽ ቆይቶ 11፡00 ላይ “ እማየ የእመቤታችንን ስእሏን ስጭኝ” አለኝ ፡ እኔም ሰጠሁት እሱም ስእሏን አቅፎ ለአንድ ሰአት ያክል አለቀሰ፡፡ ትንሽ ቆይቶም “እማየ” አለኝ ፡ እኔም “አቤት ልጄ” አልኩት ፡ እርሱም ”ሁለቱም አይኖቼ በሩልኝ” አለኝ፡፡ ደስታየን እንዴት እንደምገልፀው አላውቅም ፡ የኔ እመቤት የልጄን የነፍሱንም የስጋውንም ህመም ፈወሰችልኝ፡፡ አሁንም ልጄ እዚሁ ቤተክርስቲያን ከእመቤቴ ስእል ፊት ተንበርክኮ እየፀለየ ነው፡፡ እኔን የሰማች እናንተንም ትስማልኝ” ይህ ታአምር እንዴት ደስ ይላል፡፡ እመቤታችን ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን ፡ ከፍ ከፍ እናደርግሻለን ፡ በልጅሽ አምነው በአማላጅነሽ ተማምነው ስምሽን የሚጠሩትን እንደማትተያቸው እናውቃለን፡፡ ድንግል ሆይ ስለዚህ ክብር ምስጋና ይገባሻል፡፡ አንቺን ለእናትነትና ለአማላጅነት የሰጠን ጌታችን አምላካችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅሩ ነገር ምን ይረቅ?

@KaleEgziabeher
2.9K views21:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 00:46:01 ድንግል ሆይ! የኃጢአቴን አጽር ቅጽር ታፈርሽልኝ ዘንድ እታመንሻለሁ፡፡ ድንግል ሆይ! የዕዳ በደሌን ደብዳቤ በጅሽ ትቀጅው ዘንድ እታመንሻለሁ፡፡ ድንግል ሆይ በንጽሕና ውሀ ሰውነቴን ታጽቢልኝ ዘንድ እታመንሻለሁ፡፡ ድንግል ሆይ! በመከራዬና በጭንቀቴ ጊዜ እንድትደርሽልኝ ድንግል ሆይ! እታመንሻለሁ፡፡ ለጠላቶቼ አሳልፈሽ እንዳትሰጭኝ በጠላቶቼም እጅ እንዳትጥይኝ ድንግል እታመንሻለሁ፡፡ የሚጥለኝን እንድትጥይው፣ የሚቃረነኝንም እንድትቃረኒው፡፡
ድንግል ሆይ! እታመንሻለሁ፡፡ የሚበረታታብኝን ልምሾ ታደርጊው ዘንድ የሚቃወመኝንም ትቃወሚው ዘንድ ድንግል ሆይ! እታመንሻለሁ፡፡ ስወጣ ስገባም እንድትከተይኝ ስቀመጥና ስነሣም እንድትጠብቂኝ፡፡ ጠንካራዪቱን አምባ መጠጊያ አንቺን የታመንሽቱን ጋሻ እታመንሻለሁ፡፡ አንቺን ተጠጋሁ ነፍሴንም በፊትሽ እጥላለሁ፡፡ አንቺን ተጠጋሁ፡፡ እራሴንም በእጅሽ ሰጠሁ፡፡ ከንፈሮቼንም ለምስጋናሽ መሣሪያ አደረግሁ፡፡ የሚቃረነኝ ጠላቴ እንዳያገኘኝ የሰይጣንም ፈረሶች ሠረገላ እንዳይደርስብኝ አንቺን ተጠጋሁ፡፡ በአንቺም አመንሁ ከመስቴማ ሠራዊት ከመከበብ ከርኩሳንም መናፍስት ወጥመድ እንድድን አንቺን ተጠጋሁ፡፡ የመላእክተ ጽልመት ፍላፃ እንዳይነድፈኝ፣ ከአመፀኞችም ጦር እንድድን፣ ልዩ ከሆነ ሰይፍም እንድድን አንቺን ተጠጋሁ፡፡ የጽድቅንም መንገድ ከሚቃወሙ ሰዎች ወጥመድ እንድድን አንቺን ተጠጋሁ፡፡ አንቺን አመንሁ እኔን አገልጋይሽን አድኝኝ፡፡
1.9K views21:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 09:25:52
2.0K views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 09:25:44 መምህር ዐምደ ወርቅ እስጢፋኖስ ይባላል። ከልጅነቱ ዠምሮ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የማያልቅ መንፈሳዊ ዕውቀትና ጥበብ ከደጋጎቹ ዕንቁ ሊቃውንት አባቶቻችን እግር ሥር ቁጭ ብሎ የተማረ ነው።
አባቶቻችንን በዕውቀት ብቻ ሳይኾን በሕይወታቸው የሚመስላቸው ይኽ ታላቅ ሊቅ ታላቋን ገዳማችንን ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያምን ለረዥም ዘመናት ያገለገለ አኹንም በሚጠበቅበት ኹሉ እያገለገላት ያለ እጅግ ትኁት አባት ነው። በዚኽ ዘመንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን፣ የገዳማችን እና የሰ/ት/ቤታችን ዐይን ነው።
ዕድሜውን በአገልግሎት፣ በጸሎት፣ በትህትና፣ በፍቅር የሚመራ ስለኾነ የሰ/ት/ቤታችንን መምህራን፣ አባላት እና ቤተሰቦች በማስተማር፣ በመምከር፣ በመገሰጽ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አደራ እንዲወጡ እያደረገ ያለ አባት ነው።
ይኽ ታላቅ ሊቅ መምህራችን (ጋሽ ዐምዴ) ከተጠቀሱት ተግባራት በተጨማሪ ለቀጣዩ የቤተ ክርስቲያን ትውልድ የሚቀመጡ ቅዱሳት መጻሕፍትን እያዘጋጀ ያበረክታል። ትልልቅ የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት ደራሲያንና አዘጋጆች መጻሕፍቶቻቸውን በጥልቀት እየመረመረ የአርትዖት ሥራን በየጊዜው ይሠራላቸዋል::
ይኽ ሊቅ በግሉም እስካኹን "ኆኅተ ብርሃን ወእንዚራ ስብሐት - በግዕዝና በአማርኛ" እና "ገድለ ቅድስት አርሴማ ተኣምረ ቅድስት አርሴማ መልክአ ቅድስት አርሴማ - በግዕዝና በአማርኛ" የተሰኙ መጻሕፍትን አዘጋጅቶ ለሕትመት አቅርቦአል:: በቅርቡም "መጻሕፍተ ድርሳናቲሁ ለቅዱስ ቄርሎስ ድርሳነ ቄርሎስ ዘውእቱ እሰትጉቡእ ግጻዌ ድርሳን ዘውእቱ ጰላድዮን ተረፈ ቄርሎስ" የተሰኘ መጽሐፍ በትዕግሥት ተርጎሞ አዘጋጅቶአል።
ይኽነንም ብዙ ምሥጢራትን የያዘ መጽሐፍ እሑድ ዕለት ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 7 ሰዓት ዠምሮ በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ እኛ ልጆቹ ባለንበት ተጋባዥ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶችና ምዕመናን በተገኙበት ይመረቃል።
2.0K views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 08:10:13 በጣም የብዙ ልጆች፣ ወጣቶች፣ ባለትዳሮች ህይወት እየተቀየረበት ያለበት ጉባኤ ነው እና የተቸገራቹበት፣ የተጨነቃቹበት፣ በቃ ከዚህ በኋላ ምንም መፍትሄ የለውም ያላቹበት ጉዳይ ያላችሁ እህትና ወንድሞቼ ሆይ ጉባኤውን ተሳተፉ እና ለውጥ ታገኛላችሁ።
2.4K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ