Get Mystery Box with random crypto!

ተግተን እንጸልይ              የዓይነጥላ መንፈስ የዓይነጥላ መንፈስ ከስሙ እ | "ቃለ እግዚአብሔር "

ተግተን እንጸልይ


             የዓይነጥላ መንፈስ

የዓይነጥላ መንፈስ ከስሙ እንደምንገነዘበው በሚኖረን ኑሮ ዕድል በረከትና ጸጋ ላይ ጥላ የሚሆን ማለት ነው፡፡ የሚጋርድ የሚከልል ማለት ነው፡፡ በምናየው በምንገነዘበውና በሚኖረን መንገዳችን ላይ #አሸምቆና_ተደብቆ ጉዳት የሚያደርስብን አጥፊ የዲያቢሎስ ምሪት ነው፡፡
የዓይነጥላ መንፈስ ራሱን ማሸመቅና ባህሪን ተመሳስሎ መኖር መቻሉ ትልቁ መገለጫው ሲሆን የወደፊት እድላችንን አስቀድሞ ተረድቶ መዝጋት የሚችልና አርቆ በማየት የጥፋት እቅዶችን ቀርፆና ነድፎ የሚያጠፋ አደገኛ ጠላት ነው፡፡
ከፊት በመቅደም የሰው ልጆችን እድል የሚዘጋና ተስፋን የሚያስሟጥጥ፤ ተምረን ተምረን ሰርተን ደክመን ያቆየነውን ሁሉ ከንቱ የሚያደርግ በጣም ክፉ መንፈስ ነው፡፡ በተለይ ተመሳስሎ የመኖር አቅሙና ስልቱ ለጉዳት ጉዞው በጣም የሚያመቸው ሲሆን ከውስጥ ስለማድፈጡ ምንም መረጃ ሳይሰጥ በኑሮአችን፣ በሥራችንና በእውቀታችን ወዘተ... ላይ ሁሉ ዕንቅፋት በመሆን የሚያሰናክልና የሚያጨናግፍ ርኩስ መንፈስ ነው፡፡ ዓይነ ጥላ የምናስበውና የምናቅደው ከውስጥ ወደ ውጪ የምንመዘግበውን፤ በትምህርታችንና በስራችን የምናገኘውን ፍሬዎችና ውጤቶች ላይ በሙሉ አትኩሮቱ በማረፍ በየዕለቱ ወደፊቶቻችንን የሚከታተል መንፈስ ነው፡፡

የዓይነጥላ መንፈስ ከውጫዊ የአካላችን ጤንነት ጋር እምብዛም ጉዳይ የለውም፡፡ እጅ እግር ወገብ አይዝም፡፡ ይልቁን የእርሱ ጉዳይ አዕምሮ እና ልብ ላይ ገብቶ ማስጨነቅና የውስጥ ስቃይ መፍጠሩ ላይ ነው፡፡ የስኬት አቅጣጫና መንገዶቻችንን በአስቀድሞ መረዳት ችሎታው ስለሚያውቀው እድሎቻችንንና በረከቶቻችን ላይ በመቆም መሠረታዊ የሆነ ጥፋትና ውድመትን ያስከትላል፡፡ ከዛ ዋነኛ ጉዳት በኋላ እንዳለ ተያያዥ የሕይወት መስመሮቻችንና አካሄዳችን ስለሚዛነፉና ስለሚበላሹ እቅዱና ፖሮግራሙን ማሳካቱን ያረጋግጣል ማለት ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ እንደዛርና መተት ያሉ ሌሎች መናፍስታንንን በመጎተትና ከውስጣችን ስፍራና ቦታ በማደላደል ካስቀመጣቸው በኋላ የጥፋት መሠረቱን የሚያመቻችና በነጠረ ስልት ከፍተኛ ጉዳት በሰው ልጆች ትውልዶች ላይ አደጋ ይጥላል፡፡

የዓይነጥላ መንፈስ በጣም ብልጣብልጥና ጠንቃቃ መንፈስ ነው፡፡ ያረፈበትን ሰው ጠባይና የውስጥ አመል በጥንቃቄ ይቃኛል፥ ይመረምራል፡፡ በመቀጠል ሰውዬው የደከመበትን ጎን በማጤን ቀስ እያለ ይቆራኘዋል፡፡ በመቀጠል ጠባዩና አመሉን በመዋረስ አንድ እስከሚሆን ድረስ ይመሳሰላል፡፡ በመቀጠል ከሰውየው ጋር ረጅም ዓመታትን በመኖር አከባቢውን እየቃኘ የወደፊት እድሎቹን በማጥናት በመተንበይ ቀድሞ ሄዶ አደጋ ያዘጋጃል ማለት ነው፡፡
ሌላው መንፈሱ የሚይዛቸው ሰዎች ሌሎች ብዙ ሰዎችን ማሰናከልና ማጥፋት የሚችሉ ከሆነ ምንም አይነካቸውም፡፡ እንደውም በሥልጣንና በማዕረግ ያነሣቸዋል፡፡ በሥጋዊ እውቀቶችና የርዕዮተ ዓለም ንድፈ አሳቦች ሰውዬውን በማበልፀግ ሌሎች ሰዎችን እንዲያስቱና ክፉ እንዲያደርጉባቸው አሳብ በሚማርክ ገፅታና አቋም ፖሊሲ ይቀርፃል፡፡ እየተከታተለ ያስፈፅማል፡፡ እነዚህም ሰዎች ለጊዜው ሌሎችን ስለሚጎዱለትና የክፋት ምሪታቸውን እንደ ግብሩ በመቁጠር ከፍ ከፍ ያረጋቸዋል፡፡ የሚገርመው ግን የኃላ የኃላ ራሱ በሰጣቸው ታላቅነትና ክብር ቀንቶ ያጠፋቸዋል፡፡

ሌላው የዓይነጥላ መንፈስ የሚኖረው ጠባይና አካሄድ ካደረበት ሰው ተነስቶ ወደ ሌላ ሰው ገብቶ ያለንንና የሚኖረን ገፅታና መልካም ስም ማርከስና ማጥፋት መቻሉ ነው፡፡ ለምሳሌ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ እናት ላይ ያረፈ አይነጥላ ከልጆቿ ጋር ከባለቤቷ ጋር እያላተመ ሰላማቸውን በማናጋት የምሬት ኑሮ እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡
❖ ስለዚህም ነው ጸሎትን እንደ ቤተሰብ በጋራ መጸለይን መለማመድ ያለብን፡፡

በአጠቃላይ አንክሮ ልንሰጠው የሚገባው ትልቁ ነጥብ
  ዓይነጥላ አእምሮንና ልቦና ውስጥ እንደሚቀመጥ
  ከሕሊናችና ከጠባያችን ጋር ተመሳስሎ እንደሚኖር
  የወደፊት እድሎቻችንንና መንገዶቻችንን ቀድሞ ተረድቶ አደጋ አዘጋጅቶ የሚጠብቅ መሆኑን
ማስተዋልና ማጤን ያስፈልገናል
የዓይነጥላ መንፈስ በዋነኛነት ሁለት አይነት የውጊያ ስምሪቶች አሉት፡፡
➊ ዕንቅፋት መፍጠር ፡
ዓይነጥላ የሰው ልጆችን አኗኗር በመለማመድ የወደፊት እድሎችንና ጉዞዎችን የማጤንና አርቆ የማየት ችሎታ አለው፡፡ በዚህም ችሎታው በኩል አልፎን ይሄድና መንገዳችን ላይ አደጋና ጥፋት አዘጋጅቶ እንቅፋት ሆኖ ይጠብቅሃል፡፡ ለምሳሌ ልክ መኪና እያሽከረኸራችሁ ቢሆን በመንገዳችሁ ላይ አደናቃፊ ድንጋይ ወይ ሌላ እከል እንደማስቀመጥ ማለት ነው
➋ ጥሩ ውጤትን ማበላሸት ፡
እንደምንም ብለህ እንኳ ቀድሞ ያስቀመጠልህን እንቅፋቶች ተቋቁመህ አልፈህ ጥሩ ውጤት ብታመጣ፤ ባስገኘኸው መልካም ፍሬ ላይ ሄዶ በማረፍ የድካምህን ውጤት ከንቱ ያደርገዋል

         የዓይነጥላ መንፈስ የሚገልጣቸው ጠባያት

ትምህርትና ስራህ ሁሉ እያደር ሲያሽቆለቁል ወይም ለፍተህ ለፍተህ በረከቶችህ ሲርቁህና ሲጠፉ
ስኬትን የምታገኝባቸው ዕድሎች ያለምንም በቂ ሁናቴ መበላሸትና ለዘመናት የለፋህበት ነገር መና እየሆነ ሲቸግርህ
የትከሻ መክበድና መጫጫን ድንገተኛ መበርገግና በቁም መቃዠት.. አንዳንዴ ምን ነካኝ እስክንል ድረስ በፊት በምንታወቅባቸው ነገሮች ላይ መልፈስፈስ፡፡ ለምሳሌ እንግዲ ጎበዙ ተማሪ ትምህርቱ ሁሉ ሸክምና የማይገፋ ተራራ ሲሆንበት
በኢንተርኔትና ሌሎች የወሲብ ሱሶች መጠመድና ተደጋጋሚ ህልመ ለሊት ማስተናገድ በተለይ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ባቀድንባቸውጊዜያት
የውስጥ ጭንቀትና የአሳብ መዘበራረቅና መበታተን ግራ መጋባትና ከውስጥ የሚገፋ የተስፋ መቁረጥ ስሜት
የገንዘብና ንብረት መባከንና መጥፋት፤ እራሳችንን እስክንታዘብ ድረስ ለአስፈላጊ ነገሮች ጊዜን፣ ጉልበትንና ገንዘንብን መጨረስ
በማትጠብቀው ሁኔታና አቅጣጫ ዙሪያህ ካሉት ሰዎች ጋር መግግባት ሲያቅትህና ወዘተ..
ሌሎች የአሳብና የሕይወት ጦርነቶች ከዚሁ የዓይነጥላ መንፈስ የሚነሱ የክፋቱ መግለጫ ባህሪያቶቹ ናቸው፡፡

           የዓይነጥላ መንፈስ በትዳርና ፍቅር ውስጥ በባለትዳሮች ሕይወት ውስጥ ራእይ ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አምላክ የቤት ውስጥ አምልኮ (የዘወትር ጸሎትና ስግደት) ከሌለ የዓይነ ጥላ መንፈስ በየተናጠል ባለትዳሮቹ ላይ ያርፍባቸዋል፡፡

ሴቷ ላይ ማራኪ ወንድ ሆኖ በገሀዷም በህልሟም እየመጣ አብሯት ይሆናል፡፡ ሩካቤ ይፈፅማል፡፡ በአንፃሩ በወንዱም ላይ የሚፈልገውን አይነት የሴት ገፅታ ተላብሶ ሚስቱ ይሆናል፡፡ ይህን ፆታ ቀይሮ የማረፍ ስልትና አካሄድ  የዛር መንፈስም ይጠቀምበታል፡፡
ከዛ በኃላ በቃ መበጣበጥ ነው፡፡ መረባበሽ ነው፡፡ ትዳርን መናድ ነው፡፡ በተለይ በለሊት እየመጣ የሚገናኛቸው ጉዳይ ባለትዳሮቹን በጣም ስለሚረብሻቸው ከውስጥ በእጅጉ ማስጨነቅና ተፈጥሯዊው የግንኙነት ስሜትን በማሳጣት የፍቅር ሕይወታቸውን ከንቱ ያደርገዋል!