Get Mystery Box with random crypto!

ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)

የቴሌግራም ቻናል አርማ iwnrsatt — ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)
የቴሌግራም ቻናል አርማ iwnrsatt — ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)
የሰርጥ አድራሻ: @iwnrsatt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 218
የሰርጥ መግለጫ

ስለ እውነት ዝም ማለት በሕግ መንግሥት ወንጀል ፣ በወንጌል ኃጢአት ፣ ለሕልና ጸጸት እና ለሕይወት መጥፊያ ስለሆነ ስለ እውነት ዝም ማለት አልችልም።
👉 0926761358
https://youtube.com/channel/sintu24
https://facebook.com/groups/321567813074921/
https://www.fb.com/dsintayehunigatu.anitene

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-21 21:02:18 በድጋሚ

መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመዳን አስተምህሮ


 ·        ሁሉም ሰው ኃጢአተኛ ነው።
o   ሁሉም በክርስቶስ ከማመኑበፊትኃጢአተኛ ነው
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርምክብርጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ ፫፣ ፳፫
- ከዚህ ኃጢአት /እና ሞት/ መዳን አለብን፤መድኃኒቱምኢየሱስ ነው፤
እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸውያድናቸዋልናስሙንኢየሱስ ትለዋለህ።  ማቴ ፩፣ ፳፩

o   በክርስቶስ ካመንን በኋላምእንኳኃጢአት ይኖርብናል - ባልዳነሥጋባልዳነች ዓለም ስለምንኖር
ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥​እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
፩ ዮሐ ፩፣ ፰
- ከዚህ ኃጢአት መንጻት አለብን፤ /ከዳንንበኋላበየጊዜው ስለምንቆሽሽ/
የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአትሁሉያነጻናል።  ፩ ዮሐ ፩፣ ፯

        ሁሉም የሚድነው በክርስቶስ በማመንብቻ ነው።
በልጁየሚያምን የዘላለም ሕይወትአለው፤  ዮሐ ፫፣፴፮
        ሌላ መድኃኒት የለም
መዳንምበሌላበማንምየለም፤እንድንበት ዘንድየሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስምከሰማይ በታች ሌላየለምና።  የሐዋ ፬፣ ፲፪
        አምነን መዳናችንን የምረጋግጠውአሁን ነው።
እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁንኵነኔየለባቸውም። ሮሜ ፰፣ ፩
        ካላመንንም ፍርዱ አሁን ነው።
በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምንግንበአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን​ተፈርዶበታል።። ሮሜ ፰፣ ፩


        ማመን ማለት ስለክርስቶስ መረጃ እናእውቀትመያዝ ሳይሆን የክርስቶን አዳኝነትከውስጥ መቀበልነው። ይህም እምነት ከልብየሆነ እና የተፈተነ  ሊሆንይገባል፡፡
- በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ራሳችሁንፈትኑ፤ ፪ ቆሮ ፲፫፣ ፭
/በሃይማኖት - ማለት በእምነት እንጂበተቋምአይደለም፤  ያን ጊዜ ተቋም አልነበረም።/
- ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋውወርቅይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነእምነታችሁ፥ ኢየሱስክርስቶስ ሲገለጥ፥ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝዘንድ አሁንለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩፈተናአዝናችኋል።  ፩ ጴጥ ፩፣ ፮ - ፯
        በክርስቶስ አምነን ከዳንን በኋላመልካም ሥራእንሠራለን።
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድእግዚአብሔር​አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙንሥራለማድረግበክርስቶስኢየሱስ ተፈጠርን።  ኤፌ ፪፣ ፲
/ተፈጠርን፡ ሲል- አዲስ ማንነትን ያሳያል፣ እንጂአዲስየሚፈጠር ነገር የለም።/
መልካም ሥራ የሕይወት መገለጫ ፍሬ ነው፡፡የሕይወትሕግ እንደሚያሳየው ሕይወት ሳይኖርፍሬ አይመጣም፡ - ያልጸደቀ አያፈራም፡ /ዛፍምቢሆን/፡ ጽድቅ ደግሞበክርስቶስ ነው፡፡
          በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነትበኩልእንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።    ገላ ፫፤፳፬
 በኛ ሕይወት የሚገለጠው መንፈሳዊ ፍሬየመንፈሳዊሕይወት /የመንፈስ ቅዱስ ውጤትነው፡፡ /ገላ ፭ ፣፳፪
        በሥራችን መጠን ክብር፣ ሽልማት፣አክሊል፣ ዋጋ፣ደመወዝ.. እናገኛለን።
እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደሥራውመጠንእከፍልዘንድዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። ራእ ፳፪፣ ፲፪
        የምንድነው በእምነት እንጂ በሥራአይደለም።
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህምየእግዚአብሔርስጦታ ነው እንጂ ከእናንተአይደለም፤ ማንምእንዳይመካ ከሥራአይደለም።  ኤፌ ፪፣ ፰ - ፱
/እዚህ ሥራ የተባለው ከኛ የሆነውን ሁሉያካትታል፣መልካም ሥራ፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት..
የምንድነው በኛ ሥራ ሳይሆን ክርስቶስበመስቀል ላይበሠራው ታላቅ የማዳን ሥራበማመን ነው፡፡
መዳን በኛ ሥራ ነው ካልን ቢያንስ ሁለትጥያቄዎችንመመለስ አለብን፡፡
1.     በሥራችን የምንድን ከሆነ የክርስቶስ ሞትጥቅሙምንድን ነው?

የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስበሕግ በኩልከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱሞተ።

ኤፌ ፪፤ ፳፩

2.     ስንት መልካም ሥራ ስንሠራ ነውለመዳንየምንበቃው?
እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደትበሚሆነውመታጠብና በመንፈስ ቅዱስበመታደስ አዳነን እንጂ፥እኛ ስላደረግነውበጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤  ቲቶ ፫፤ ፭
በክርስቶስ አምነን ከዳንን በኋላም ኃጢአትእንሠራለን፡ነገር ግን ወደነው፣ ሆን ብለን፣በተደጋጋሚ ሳይሆን - ሥጋችን ስላልዳነበእርሱ ግፊት ሲሆን ይህም ድልልናደርገውየሚገባ የሥጋ ትግል ነው፡፡ የጾምናጸሎትሚና እዚህ ላይ ወሳኝ ነው፡፡
በእኔ ማለት በሥጋዬበጎነገርእንዳይኖር አውቃለሁና፤ፈቃድ አለኝና፥መልካሙን ግን ማድረግ የለኝም።​የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ሮሜ ፯፣፲፰
        በክርስቶስ አምነን ከዳንን በኋላምኃጢአት ስንሠራየምንነጻው በንስሃ- በክርስቶስ ደም ነው። ይህም ንስሐመግባትበየጊዜው ልናደርገው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅርሊለንከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅነው። ፩ ዮሐ፩፣ ፱
የልጁም የኢየሱስክርስቶስደምከኃጢአት ሁሉያነጻናል። ፩ ዮሐ ፩፣ ፯
ለኃጢአት የተከፈለ ውድ የሕይወት ዋጋየክርስቶስስለሆነ ሌላ የሚያነጻ ነገር የለም፡ሊኖርም አይችልም፡፡
/ልብ እንበል፡- ሊያነጻን፣ ያነጻናል - ስለመንጻት/ስንቆሽሽ/ እንጂ ስለመዳን አይደለም።/

ቢገባንም ባይገባንም የእግዚአብሔር ቃልእውነት ነው፤ይሠራል።

ካመንንበት እና ከተቀበልነው በኛም ሕይወትይሠራል፤​ይለውጠናል፡፡


እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌንየሚሰማየላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወትአለው፥ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደፍርድአይመጣም። ዮሐ ፭፣ ፳፬

---------------------------//-----------------



https://t.me/IWNRSATT
101 viewsSintayehu Nigatu, 18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 17:25:32
የሚታደርጉትን ሁሉ በጥንቃቄ አድርጉ

በዚህ ርዕስ በቅርብ ጊዜ አንድ መልእክት መጻፈ ይታወሳል ።ዛሬም ብሆን ይህንኑ ርዕስ በመጠቀም ሌላውን ጉዳይ ማንሳት ግድ ሆነብኝ ።ምክንያቱም የዛሬው ሾልኮ ገቢ ሐሰተኛ ነው ።

ብዙ ጊዜ የሚንከተላቸው ሰዎች ማናቸው የሚለውን ጥያቄ ሳንጠይቅ እንከተላቸዋለን ።በኃላ ግን በተሳሳተ አቅጣጫ መሆናችንን ካወቀን እንቆጫለን !!

ዛሬ ለመንገር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የተባለው ግለሰብ ማነው ? የሚል ይሆናል ።

ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ከስድሳ (60) በላይ መጽሐፎች የጻፈና united denominations originating from the lightouse group church መስራችና ባለራዕይ በመሆን ይታወቃል ። የሆነው ሆኖ ዛሬ በእርሱ ዙሪያ መጻፍ ያስፈለገው ለምንድን ነው ?? ብባል ብዙ አገልጋዮች ፣ወጣቶች እና አንባቢ የሆኑ ክርስቲያኖች መጽሐፎቹን ያነባሉ ።ነገር ግን ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የሐሰት ትምህርት አስተማሪ መሆኑን አለመረዳታቸው ደግሞ እጅግ በጣም የሚገርም ነገር ነው ።

እኔ ዛሬ ይህን ለመጻፍ የተነሳውት መጽሐፎችን አታነቡ ለማለት ሳይሆን ሲታነቡ ግን በጥንቃቄ እንታነቡ እጋብዛለሁ !! እውነት ለመናገር ከመጽፎቹ የተጠቀምኩት ነገር የለም ማለት ባልችልም ግን የስህተት አስተማሪ መሆኑን እንድታውቁ እፈልጋለሁ ። ለጠቅላላ ዕውቀት ብንጠቅምም ከመዳን ጋር በሚገናኙ ነገሮች ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ።

ማነኛውም ሰው ፊጹም ላይሆን ይችላል ።ነገር ግን በራሱ ድካም ለሌላው መሰናክል ሲሆን ዝም ማለት የለበትም ።
ስህተቱን ምንድን ነው ?
ለዚህ ጥያቄ ከእኔ በላይ መጽሐፎቹ በግልጽ ሊያስረዱ ይችላሉ ። ይንም ለአብነት ያህል ድነትን እንዴት ልትሰብክ ትችላለህ ከሚለው መጽሐፍ በላይ በኩል ያለውን ፎቶ አቅርብያለሁ !!
ይቀጥላል .
58 viewsSintayehu Nigatu, 14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 11:08:04

ውድ የስለ እውነት ዝም አልልም telegram channel ተከታዮች እንኳን በሠላም አደረሳችሁ !!


ይህ telegram channel በቀን 2/12/2012 ዓ.ም ከተጀመረ እስከ ዛሬ ድረስ በእግዚአብሔር ቸርነት በተለያየ ርዕሶች የእግዚአብሔርን ቃል ስንማር መቆየታችን ይታወሳል ።



ላመኑት የመጽናት ላላመኑት የእምነት መንገድ በመሆን መቆየቱ አያጠራጥርም ።



ዛሬም ብሆን ዘላቂ እና ለብዙዎች ግንዛቤ መጨበጫ channel እንዲሆን እና ተደራሽነቱ እንዲጨምር የእናንተ ትብብር እጂግ በጣም የጎላ ነው ።ስለዚህ በእያላችሁበት በእያንስ ለ10 ሰው ሼር ሼር በማድረግ መልካም ትብብራችሁን እንዲትገልፁ በጌታ ስም እጠይቃለሁ !!


https://t.me/IWNRSATT
71 viewsSintayehu Nigatu, 08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 12:38:20

81 viewsSintayehu Nigatu, 09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 23:25:22 https://t.me/IWNRSATT
78 viewsSintayehu Nigatu, 20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 12:48:18 "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"

ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

T.me/sintayehud
70 viewsSintayehu Nigatu, 09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 12:48:05 የአብ ፈቃድ ምንድን ነው ?


ይህን ጥያቄ መጠየቅ ለምን አስፈለገ ብባል የአብ ፈቃድ የማይፈጽም ማነኛውም ሰው የዘላለም ሕይወት ልያገኝ አይችልም ።ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል 7፥21 ላይ “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።” ይላል ። ስለዚህ እኛ ሁላችንም የአብ ፈቃድ ምን እንደሆነ መረዳትና መፈጸም አለብን ። ለመሆኑ የአብ ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅና ለመፈጸም ፈቃደኛ ነህ/ሽ ?


እንግዲህ የአብ ፈቃድ በልጁ ማመን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ “ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።” ዮሐ 6፥40 በማለት ይመሰክራል።ስሙን ከመጥራትና ብዙም ከመናገር የአብ ፈቃድ መፈጸም እንደሚበልጥ ለማንም ግልጽ የሆነ እውነት ነው ።ይህ ብቻ ሳይሆን የአብ ሥራ ራሱ በልጁ ማመን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ 6፥28-29 ላይ “ እንግዲህ፦ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት። ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።” በማለት ከየትኛውም መልካም ሥራ በላይ መልካም የሆነ ሥራ የአብን ፈቃድ መፈጸም እንደሆነ ይመሰክራል ። ስለዚህ ይህንኑ እውነት ለመቀበልና የአብን ፈቃድ ለመፈጸም ፈቃደኛ ነህ/ሽ ?

ፈቃደኛ ከሆንሽ የሚከተሉትን ነገሮች እወቅ

1.እግዚአብሔር ይወድሃል ።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”ዮሐ 3፥16

2.ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ ነው ።

“ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤”ሮሜ 3፥23 በዚህ ያላመነ ሁሉ ምክንያት አሁን ተፈርዶበታል ። ዮሐ 3፥18 ላይ “በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።” ይላል ። የተፈደበት ምክንያትም ሌላ ሳይሆን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ ብቻ ነው ።
ታድያ “ወደ ውጭም አውጥቶ፦ ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል ኣላቸው።”ሐዋ16፥30 ይህ ጥያቄ ያንተ/ያችንም አይሆንም ብለህ ታስባለህ ? ከሆነ መልሱ የሚከተለው ነው ።

3.ከዚህ ፍርድ የሚያድነውም በእግዚአብሔር ልግ በኢየሱስ ማመን ብቻ ነው። 1ኛ ዮሐንስ 5፥12 ላይ “ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።”ይላል ።ስለዚህ መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”ሐዋ 4፥12

4.የመዳን ቀን አሁን ነው ።“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”2ኛ ቆሮ 6፥2


ፈቃደኛ ከሆንክ/ሽ የሚከተለውን አጭር ፀሎት አብረን እንፀልይ !!

ጌታ ኢየሱስ ሆይ ፣ አንተን በግሌ ለማወቅ እፈልጋለሁ ።ስለ ኃጢአቴ በመስቀል እንደሞትክልኝና እንደሞትክና እንደተነሳህ አምናለሁ ።አሁን ልቤን ከፍቼ አዳኜኛ ጌታዬ አድርጌ እቀበላለሁ ።ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ስላልከኝና የዘላለም ሕይወት ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ ።በሕይወቴ ዙፋን ላይ ሆነህ ግዛኝ።አንተ የሚትፈልገውን አይነት ሰው አድርገኝ ። አሜን !!

አንባቢ ሆይ ከታች ያለውን ጥቅስ በማስተዋል እንታነበው እጋብዛለሁ !!

መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል 3፥18“በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።” ይላል ። እንደዚሁ ደግሞ ዮሐ 3፥36 ላይ “በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።” ይላል።ስለዚህ ይህንን እውነት ተቀብለህ በልጁ አምነህ እንደሆነ ከእግዚአብሔር ቁጣ አምልጠህ የዘላለም ሕይወት አግኝተኃልና በጌታ ደስ ይበልህ “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።” ፊልጵ 4፥4



ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማግኘት

0916569878
0926761358

ማሳሰቢያ ፦ ተጨማሪ ትምህርት ለመማር የሚያስፈልገው መሥፈርት ማመን ብቻ ነው እንጂ ሃይማኖትን መቀየር እንዳይደለ እወቁ ። ማመንና መቀየር የተለያዩ ነገሮች ናቸው ።
በተጨማሪ ጥያቄ ካለ በየትኛውም ጊዜ መጠየቅ ይቻላል !!

ዲ/ን ስንታየሁ ንጋቱ ነኝ

T.me/aikose
t.me/sintayehud
69 viewsSintayehu Nigatu, 09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ