Get Mystery Box with random crypto!

የአብ ፈቃድ ምንድን ነው ? ይህን ጥያቄ መጠየቅ ለምን አስፈለገ ብባል የአብ ፈቃድ የማይፈጽም | ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)

የአብ ፈቃድ ምንድን ነው ?


ይህን ጥያቄ መጠየቅ ለምን አስፈለገ ብባል የአብ ፈቃድ የማይፈጽም ማነኛውም ሰው የዘላለም ሕይወት ልያገኝ አይችልም ።ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል 7፥21 ላይ “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።” ይላል ። ስለዚህ እኛ ሁላችንም የአብ ፈቃድ ምን እንደሆነ መረዳትና መፈጸም አለብን ። ለመሆኑ የአብ ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅና ለመፈጸም ፈቃደኛ ነህ/ሽ ?


እንግዲህ የአብ ፈቃድ በልጁ ማመን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ “ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።” ዮሐ 6፥40 በማለት ይመሰክራል።ስሙን ከመጥራትና ብዙም ከመናገር የአብ ፈቃድ መፈጸም እንደሚበልጥ ለማንም ግልጽ የሆነ እውነት ነው ።ይህ ብቻ ሳይሆን የአብ ሥራ ራሱ በልጁ ማመን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ 6፥28-29 ላይ “ እንግዲህ፦ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት። ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።” በማለት ከየትኛውም መልካም ሥራ በላይ መልካም የሆነ ሥራ የአብን ፈቃድ መፈጸም እንደሆነ ይመሰክራል ። ስለዚህ ይህንኑ እውነት ለመቀበልና የአብን ፈቃድ ለመፈጸም ፈቃደኛ ነህ/ሽ ?

ፈቃደኛ ከሆንሽ የሚከተሉትን ነገሮች እወቅ

1.እግዚአብሔር ይወድሃል ።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”ዮሐ 3፥16

2.ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ ነው ።

“ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤”ሮሜ 3፥23 በዚህ ያላመነ ሁሉ ምክንያት አሁን ተፈርዶበታል ። ዮሐ 3፥18 ላይ “በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።” ይላል ። የተፈደበት ምክንያትም ሌላ ሳይሆን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ ብቻ ነው ።
ታድያ “ወደ ውጭም አውጥቶ፦ ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል ኣላቸው።”ሐዋ16፥30 ይህ ጥያቄ ያንተ/ያችንም አይሆንም ብለህ ታስባለህ ? ከሆነ መልሱ የሚከተለው ነው ።

3.ከዚህ ፍርድ የሚያድነውም በእግዚአብሔር ልግ በኢየሱስ ማመን ብቻ ነው። 1ኛ ዮሐንስ 5፥12 ላይ “ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።”ይላል ።ስለዚህ መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”ሐዋ 4፥12

4.የመዳን ቀን አሁን ነው ።“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።”2ኛ ቆሮ 6፥2


ፈቃደኛ ከሆንክ/ሽ የሚከተለውን አጭር ፀሎት አብረን እንፀልይ !!

ጌታ ኢየሱስ ሆይ ፣ አንተን በግሌ ለማወቅ እፈልጋለሁ ።ስለ ኃጢአቴ በመስቀል እንደሞትክልኝና እንደሞትክና እንደተነሳህ አምናለሁ ።አሁን ልቤን ከፍቼ አዳኜኛ ጌታዬ አድርጌ እቀበላለሁ ።ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ስላልከኝና የዘላለም ሕይወት ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ ።በሕይወቴ ዙፋን ላይ ሆነህ ግዛኝ።አንተ የሚትፈልገውን አይነት ሰው አድርገኝ ። አሜን !!

አንባቢ ሆይ ከታች ያለውን ጥቅስ በማስተዋል እንታነበው እጋብዛለሁ !!

መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል 3፥18“በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።” ይላል ። እንደዚሁ ደግሞ ዮሐ 3፥36 ላይ “በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።” ይላል።ስለዚህ ይህንን እውነት ተቀብለህ በልጁ አምነህ እንደሆነ ከእግዚአብሔር ቁጣ አምልጠህ የዘላለም ሕይወት አግኝተኃልና በጌታ ደስ ይበልህ “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።” ፊልጵ 4፥4



ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማግኘት

0916569878
0926761358

ማሳሰቢያ ፦ ተጨማሪ ትምህርት ለመማር የሚያስፈልገው መሥፈርት ማመን ብቻ ነው እንጂ ሃይማኖትን መቀየር እንዳይደለ እወቁ ። ማመንና መቀየር የተለያዩ ነገሮች ናቸው ።
በተጨማሪ ጥያቄ ካለ በየትኛውም ጊዜ መጠየቅ ይቻላል !!

ዲ/ን ስንታየሁ ንጋቱ ነኝ

T.me/aikose
t.me/sintayehud