Get Mystery Box with random crypto!

ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)

የቴሌግራም ቻናል አርማ iwnrsatt — ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)
የቴሌግራም ቻናል አርማ iwnrsatt — ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)
የሰርጥ አድራሻ: @iwnrsatt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 218
የሰርጥ መግለጫ

ስለ እውነት ዝም ማለት በሕግ መንግሥት ወንጀል ፣ በወንጌል ኃጢአት ፣ ለሕልና ጸጸት እና ለሕይወት መጥፊያ ስለሆነ ስለ እውነት ዝም ማለት አልችልም።
👉 0926761358
https://youtube.com/channel/sintu24
https://facebook.com/groups/321567813074921/
https://www.fb.com/dsintayehunigatu.anitene

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-06 13:21:23 የመጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን ንጽጽራዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

ክፍል ሦስት

ቅዱሳት መጻሕፍት

5.እግዚአብሔር ቃሉን በሙሉ ከብረዛ ለመጠበቅ ይሻልን? (ፍላጎት / ኒያ)

መጽሐፍ ቅዱስ አዎን / ቁርአንም አዎን ነው ።

መ/ዳዊት 12፡6-7 በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።
አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን።

ኢሳ 14 ፡24 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፥ እንደ አሰብሁም እንዲሁ ይቆማል።
በምድር ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያሰበው አሳብ ይህ ነው፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋች እጅ ይህች ናት። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን አስቦአል፤ የሚያስጥለውስ ማን ነው? እጁም ተዘርግታለች የሚመልሳትስ ማን ነው?

ማቴ 24፡35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።

-----------------------------------

አል-ሒጅር 15፡9 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡

አልሷፍፋት 37፡3 & 7 ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ።….አመጸኛም ከሆነ ሰይጣን ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት።

6.እግዚአብሔር ቃሉን ከመለወጥና ከብረዛ መጠበቅ ይችላልን?

መጽሐፍ ቅዱስ አዎን / ቁርአንም አዎን ነው ።

ኢሳ 46፡9-10 እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።….በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ።

ማርቆስ 12፡24 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ስለዚህ የምትስቱ አይደለምን?

ሉቃስ 21፡23 በዚያን ወራት ለእርጕዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይሆናልና፤
ዮሐ 10፡35 መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥

-------------------------------------

አል-አንዓም 6፡115 የጌታህም ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትኾን ተፈጸመች፡፡ ለቃላቱ ለዋጭ የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡

ዩኑስ 10፡64 ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡

አል-ጂን 72፡26-28 (እርሱ) ሩቁን ሚስጢር ዐዋቂ ነው፣ በሚስጢሩ ላይ አንድንም አያሳውቅም። ….እነሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበና ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲሆን፣ የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ ዘንድ (ጠባቂ ያደርጋል)።



join


በጌታ የሆናችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይህ መልእክት ለእናንተ ምናልባት ቀላል ልመስላችሁ ይችላል ።ነገር ግን ለአንድ ሙስሊም ወንድም ከባድ መልእክት አለው ። ስለዚህ share በማድረግ እንዲትተባበሩ በጌታ ፍቅር አሳስባችኋለሁ !!

ለእናንተ በአንድ ደቅቃ ለተወሰኑ ሰዎች share ማድረግ ቀላል ነገር ነው ።ብሆንም የሚያመጣው ውጤት ከእኔ ጋር ለመንግሥቱ አግልግሎት መቆም መሆኑን እውቁ ውጤቱ ደግሞ የጽድቅ አክልል ነው ። ስለዚህ አስባችሁ ተባበሩልኝ !!

https://t.me/IWNRSATT

ክፍል አራት

ይቀጥላል .........
31 viewsSintayehu Nigatu, 10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:12:12 የመጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን ንጽጽራዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

ክፍል ሁለት

ቅዱሳት መጻሕፍት

3.እግዚአብሔር ቃሉን በተለይም በአይሁድ አማካይነት ለሰዎች አስተላልፏልን?

መጽሐፍ ቅዱስ አዎን /ቁርአንም አዎን ነው ።

ሮሜ 3፡1-2 እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው። አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጡአቸው። ታዲያ ምንድር ነው?

ሮሜ 9፡4 እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፡፡

------------------------------

አል-ዐንከቡት 29፡27 ለርሱም ኢስሐቅንና ያዕቆብን ሰጠነው፤ በዘሩም ውስጥ ነቢይነትንና መጽሐፍን አደረግን፤ ምንዳውንም በቅርቢቱ ዓለም ሰጠነው፤(2) እሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከደጋጎቹ ነው።

አል-ጃሢያህ 45፡16 ለእስራኤል ልጆችም መጽሐፍንና ሕግን፣ ነቢይነትንም በእርግጥ ሰጠናቸው፤ ከመልካም ሲሳዮችም ለገስንላቸው በአለማት ላይም አበለጥናቸው።

4.እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለሚገኙት ነቢያት ተዓምራትን እንዲያደርጉ ኃይልን በመስጠት ከእርሱ የተላኩ ስለመሆናቸው ማረጋገጫን ሰጥቷልን?

መጽሐፍ ቅዱስ አዎን /ቁርአን አዎን ነው ።

ዘጸአት 10፡2 ይህችንም ተአምራቴን በመካከላቸው አደረግ ዘንድ የእርሱን የባሪያዎቹንም ልብ አደንድኜአለሁና ወደ ፈርዖን ግባ አለው።

ዮሐ 14፡11 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ

ዕብ 2፡4 እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ በምልክትና በድንቅ ነገር በልዩ ልዩ ተአምራትም፥ መንፈስ ቅዱስንም በማደል አብሮ መሰከረለት።

----------------------------

አል-በቀራህ 2፡92 ሙሳም በታምራቶች በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ከዚያም ከበኋላው እናንተ በዳዮች ስትኾኑ ወይፈንን (አምላክ አድርጋችሁ) ያዛችሁ፡
አሊ-ዒምራን 3፡49 ወደ እሥራኤልም ልጆች መልክተኛ የደርገዋል፤ (ይላልም) ፡-እኔ ከጌታዬ ዘንድ በታምር መጣኋችሁ። እኔ ለናንተ ከጭቃ አንደ ወፍ ቅርጽ እፈጥራለሁ፤ በርሱም እተነፍስበታለሁ፤ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይሆናል። በአላህም ፈቃድ ዕዉር ሆኖ የተወለደን፥ ለምጸኛንም፥ አድናለሁ፤ ሙታንንም አስነሳለሁ። የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ የምታምኑ እንደሆናችሁ ለእናንተ በዚህ ዉስጥ በእርግጥ ታምር አለበት።

አሊ-ዒምራን 3፡183 እነዚያ ለማንኛዉም መልክተኛ እሳት የምትበላዉ የሆነን ቁርባን እስከሚያመጣልን ድረስ ላናምን አላህ ወደኛ አዟል ያሉ ናቸዉ፤ መልክተኞች ከኔ በፊት በታምራትና በዚያም ባላችሁት (ቁርባን) በእርግጥ መጥተዉላችኋል፣ እዉነተኞች ከሆናችሁ ታድያ ለምን ገደላችኋቸዉ? በላቸዉ።



join


በጌታ የሆናችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይህ መልእክት ለእናንተ ምናልባት ቀላል ልመስላችሁ ይችላል ።ነገር ግን ለአንድ ሙስሊም ወንድም ከባድ መልእክት አለው ። ስለዚህ share በማድረግ እንዲትተባበሩ በጌታ ፍቅር አሳስባችኋለሁ !!

ለእናንተ በአንድ ደቅቃ ለተወሰኑ ሰዎች share ማድረግ ቀላል ነገር ነው ።ብሆንም የሚያመጣው ውጤት ከእኔ ጋር ለመንግሥቱ አግልግሎት መቆም መሆኑን እውቁ ውጤቱ ደግሞ የጽድቅ አክልል ነው ። ስለዚህ አስባችሁ ተባበሩልኝ !!

https://t.me/IWNRSATT

ክፍል ሦስት

ይቀጥላል .........
45 viewsSintayehu Nigatu, edited  13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:08:06
አሁን አሁንማ መጽሐፍ ቅዱን አንብቡ ማለትን መጀመራቸው እጅግ በጣም ያስገርመኛል ። ከዚህ ቀጥሎ የሚመጣ ነገር እግዚአብሔር ያሳየን !!

https://t.me/IWNRSATT
38 viewsSintayehu Nigatu, edited  13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 16:59:36 ክፍል አንድ


የመጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን ንጽጽራዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

ቅዱሳት መጻሕፍት

1.የእግዚአብሔር ቃል ዘላለማዊና የማይለወጥ መሆኑ እውነት ነውን?

መልሱ፦ በመጽሐፍ ቅዱስ አዎን/በቁርአንም አዎን

ኢሳይያስ 40፡8 ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

ዮሐንስ 1፡1 በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

1ኛ የጴጥሮስ 1፡23 ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።

----------------------------

ዩኑስ 10፡64 ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡

ቃፍ 50፡29 «ቃሉ እኔ ዘንድ አይለወጥም፡፡ እኔም ለባሮቼ ፈጽሞበዳይ አይደለሁም» (ይላቸዋል)፡፡

2.መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው የሚለው ተቀባይነት አለውን? (ተውራት፣ ዘቡርና ኢንጂል)

መልሱ፦መጽሐፍ ቅዱስ አዎን / አዎን ቁርአን

ሮሜ 15፡4 በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና።

1ኛቆሮ 14፡37 ማንም ነቢይ ወይም መንፈሳዊ የሆነ ቢመስለው ይህች የጻፍሁላችሁ የጌታ ትእዛዝ እንደ ሆነች ይወቅ፡፡
----------------------------------

አል-ኒሳእ 4፡136 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልክተኛው በዚያም በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ፣ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ፣ እመኑ፤ በአላህና በመላክቱም፣ በመጽሐፎቹም፣ በመልክተኞቹም፣ በመጨረሻውም ቀን የካደ ሰው፣ (ከሰውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ።

አል-ዐንከቡት 29፡46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፤ ከነሱ ነዚያን የበደሉትን ሲቀር በሉም ፦ በዚያ ወደኛ በተወረደው፣ ወደናንተም በተወረደው አመንን፤ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፤ እኛም ለርሱ ታዛዦች ነን።

አል-ሹራ 42፡15 ለዚህም (ድንጋጌ ሰዎችን) ጥራ፤ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፤ ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል፤ በላቸውም፦ ከመጽሐፍ አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ፤ በመካከላችሁም ላስተካክል ታዘዝኩ፤ አላህ ጌታችን፣ ጌታችሁም ነው፤ ለኛ ሥራዎቻችን አልሉን ለናንተም ሥራዎቻችሁ አልሏችሁ፤ በኛና በናንተ መካከል ክርክር የለም፤ አላህ በመካከላችን ይሰበስባል። መመለሻም ወደርሱ ብቻ ነው።

ይቀጥላል ..........


join


ለጎደኞቻችሁ share በማድረግ እንዲትተባበሩ በጌታ ፍቅር አሳስባችኋለሁ !!

https://t.me/IWNRSATT

ክፍል ሁለት

ይቀጥላል .........
175 viewsSintayehu Nigatu, 13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 16:53:16 የመጽሐፍ ቅዱስና ቁርአን ንጽጽራዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

የሚለው ዝግጅት ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ የሚጻፍ መሆን ስገልጽ በታላቅ ደስታ ነው ።

የሚጻፈው በሳምንት ሁለት ጊዜ ሲሆን እሁድና ዕሩብ ነው ።የሚሆነው ተከታትላችሁ በመማር ለሙስልም ወንድሞች የመመስከር ችሎታችሁን እንዲታዳብሩ በጌታ ፍቅር ስጋብዛችሁ በታላቅ ደስታ ነው ።

በተጨማሪ ለጎደኞቻችሁ share በማድረግ ከእኔ ጋር አብሮነታችሁን እንዲታሳዩ በጌታ ፍቅር አሳስብችኃለሁ !!

የጌታ ሠላምና ፀጋ ይብዛላችሁ !!

ዲ/ን ስንታየሁ ንጋቱ

https://t.me/IWNRSATT

ክፍል አንድ

89 viewsSintayehu Nigatu, edited  13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 13:14:56

የተመረቀው ብቸኛው መንገድ

የሰው ልጅ ትዕዛዝ ከመተላለፉና ኃጢአት ከመሥራቱ በፊት
የሚከተሉት ሦስት እድሎች ነበሩት፡፡
ሀ) ያለምንም መከልከል ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ማድረግና
ኀብረት ማድረግ ይችል ነበር፡፡
ለ) ከእግዚአብሔር ጋር ከነበረው ግንኙነትና ኅብረት የተነሳ ፈጣሪውን
ያውቅ ነበር፡፡
ሐ)ምድራዊ ኑሮ መኖር ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ሕይወት ነበረው፡፡
የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ተላልፎ ኃጢአት ባደረገ ጊዜ ግን ሰው
እነዚህን ከላይ የዘረዘርናቸው ዕድሎች ሁሉ አጣቸው፡፡ በዚህ
ምክንያት እነዚህን ዕድሎች መልሶ ለመጐናፀፍ ሦስት ዓይነት ነገሮች
አስፈለጉት፡፡ እነርሱም፥

ሀ. እርቅ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ኃጢአት የፈጠረው ርቀት
ተወግዶ እንደገና ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ የሚያስችል መንገድ
አስፈለገው፡፡

ለ. መንፈሳዊ ብርሃን ሰው በአእምሮ ብቻ ስለ እግዚአብሔር ማወቁ
ቀርቶ እግዚአብሔርን በግል ሕይወቱ ለማወቅ መንፈሳዊ ጨለማውን
የሚገፍለትን ትክክለኛውን መረዳት የሚሰጠው ብርሃን አስፈለገው፡፡

ሐ. አዲስ ልደት፥ ሰው መንፈሳዊነትን ለማግኘት ከመንፈስ ቅዱስና
ከእግዚአብሔር ቃል እንደገና መወለድ አስፈለገው፡፡
ለብዙ ሺህ ዘመናት ሰው እነዚህን ፍላጐቶቹን ማሟላት የሚችልለት
ሳያገኝ ቀረ፡፡ ስለዚህ ሰው ለችግሩ ዘለቄታ ያለው መፍትሔ ሳያገኝ
ኖረ፡፡ ነገር ግን ጊዜውና ሰዓቱ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን
ኢየሱስ ክርስቶስን ለዚሁ ዓላማ መርቆና ሹሞ ወደዚህ ዓለም ላከለት፡፡


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መጥቶ ያስተማራቸው
ትምህርቶችና ያበሰራቸው የምሥራች አዋጆች እንዲሁም በመስቀል
ላይ የሰራው ሥራ ከላይ የተገለጸውን የሰው ዋና ፍላጎቶች የሚያሟላ
ነበር፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14 ቁጥር 6 ላይ እንደምናነበው፤
“ኢየሱስም፥ እኔ መንገድና ዕውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ
አብ የሚመጣ የለም፤” አለ፡፡

ሀ.“እኔ መንገድ ነኝ።” ሲል ሰው ወደ እግዚአብሔር መምጣት
የሚችልበት የተመረቀው ብቸኛ መንገድ እርሱ ብቻ መሆኑን መግለጹ
ነው፡፡ በሌላም ቦታ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እኔ የበጐች
በር ነኝ” ሲል ተናግሯል፡፡ (ዮሐንስ 10፥7)ከእርሱ ሌላ ወደ
እግዚአብሔር መምጣትና እርቅ ማድረግ አይቻልም፡፡

ለ.“እውነት ነኝ።” በማለቱ ደግሞ የሰውን የአዕምሮ ጨለማ
የሚገፍ ብርሃን (እውነት) እርሱ ብቻ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ ሰው
እግዚአብሔርን ማወቅ የሚችለው በግል ኢየሱስን በማወቅ ብቻ ነው፡፡ (ዮሐንስ 14፥9)

ሐ.“ሕይወት ነኝ” ሲል ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ
ከመንፈስ ቅዱስና ከቃሉ ዳግመኛ በመወለድ አጥቶት የነበረውን
ዘላለማዊና መንፈሳዊ ሕይወት እንዲሚያገኝ ለመጠቆም ነው፡፡
ሐዋርያትም ሌላ ሳይሆን እርሱ ራሱ ክርስቶስ “ነኝ” ሲል ያወጀውን
ቃል አምነው በመቀበል “መዳን በማንም የለም፣ እንድንበት ዘንድ
የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ከሰማይ በታች ሌላ ስም የለምና፡፡”
(የሐዋርያት ሥራ 4፥12) በማለት የእርሱን ብቸኛ መድኃኒትነት
አውጀዋል፡፡
የሰውንና የእግዚአብሔርን ግንኙነት በተመለከተ ጉዳይ በመካከል ሆኖ
ሰውንና እግዚአብሔርን ለማስታረቅ የሚችል ክርስቶስ ብቻ መሆኑ
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተደጋግሞ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ “አንድ
እግዚአብሔር አለና፤ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው
መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፣ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፡፡”(1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5)

ከእርሱም ሌላ በመስቀል ላይ ደሙን ለሰው ልጆች ደህንነት ያፈሰሰ ማንም የለም፡፡

አንዳንድ ሰዎች ከተሾመው ብቸኛ መንገድ ሌላ ምርጫ ያለ እየመሰላቸው “እኛ የምናምነው እምነት …” እና “እናንተ ደግሞ
የምታምኑት እምነት …” ሲሉ ይናገራሉ፡፡ አንድ ነገር እውነት
የሚሆነው እኛ ስላመንበት አይደለም፡፡

ሰው በአንድ ነገር ማመን ያለበት ያ ነገር እውነት በመሆኑ ብቻ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ
አንድ ሰው መሬት ጠፍጣፋ ነች ብሎ ቢያምን የእርሱ እምነት መሬት ክብነቷን ትታ ጠፍጣፋ እንድትሆን አያደርጋትም፡፡ መሬት ክብ እንደሆነች የምናምነው በመጽሐፍ ቅዱስም የተደገፈ ሳይንሳዊ ሐቅ በመሆኑ ነው፡፡

እምነት “የሚያድን እምነት”የሚሆነው እምነታችንን ከምናደርግበት ነገር ማንነት የተነሳ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ተማሪ አንዱን ዛፍ
ጆዖግራፊ አስተምረኝ ብሎ ቢያምንበትና ቢጠመጠምበት ዛፉ
ጆዖግራፊ ሊያስተምረው አይችልም፡፡ ምክንያቱም ዛፍ ጆዖግራፊ የማስተማር ችሎታ የለውም፡፡ ልክ እንደዚሁ ከተመረቀው ብቸኛ
መንገድ በቀር ደህንነትን የሚሰጥ ሌላ አማራጭ እንዳለ መድከም
ከንቱ ድካም ብቻ ነው፡፡

ሰው ደህንነትን በተመለከተ የሚያደርገው ምርጫና ውሳኔ አይስክሪም ለመግዛት ከሚያደርገው ምርጫና ውሳኔ የተሻለ ሊሆን ይገባል፡፡ አንድ
ሰው አይስክሪም ሲገዛ የሚመርጠው እርሱ የወደደውንና የፈቀደውን ነው፡፡ ነገር ግን አይስክሪም ለመግዛት ያደረገውን ምርጫና ውሳኔ መድኃኒት ለመግዛት ቢያስፈልገው ሊጠቀምበት አይችልም፡፡ ሰው
መድኃኒት የሚገዛው ደስ የሚለውን በመምረጥ ሳይሆን ከህመሙ ሊያድነው የሚችለውን ብቻ ነው፡፡ የነፍስ ደህንነትም ጉዳይ የሚመሰረተው በመድኃኒቱ ፍቱንነት ላይ እንጂ ሰው በወደደውና “ያድነኛል” ብሎ በመረጠው ምርጫ ላይ አይደለም፡፡

አንዳንድ ሐኪሞች በሽተኞቻቸውን መርምረው ምንም በሽታ ሳይገኝባቸው ሲቀርና፤ “ያመኛል እስቃያለሁ” ማለታቸው የማያቆም
ሲሆን ጉዳዩ የበሽታ ሳይሆን በአእምሮ ያለ የሐሳብ ጉዳይ ነው ብለው በመገመት ‘ፕለሲቦ’ የተባለ መድኃኒት ያዙላቸዋል፡፡ ‘ፕለሲቦ’ መድኃኒት ሳይሆን በመድኃኒት መልክ የተሰራ የስኳር እንክብል ነው፡፡

በሸተኞቹም ለበሽታው መድኃኒት ተገኘ ብለው ያንን ‘ፕለሲቦ’
ውጠው ከበሽታቸው የዳኑ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን የስሜትና
የአስተሳሰብ ነገር እንጂ ‘ፕለሲቦ’ ምንም መድኃኒትነት የለውም፡፡
እንደዚሁም ከተመረቀው ብቸኛ መንገድ (ከክርስቶስ)በቀር ደኅንነት
የሚገኝበት መንገድ የለም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ
የዓለም መድኃኒት (መድኃኒዓለም) እንደሆነ በማመንና “መድኃኒቴ”
ብሎ እርሱን በመቀበል መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ ልዩነቱም
የመጀመሪያውን አጋንንትም እንኳ ስለማይክዱትና ስለሚናገሩት ሲሆን
ሁለተኛውን ግን በግል ሕይወቱ መድኃኒትነቱን የቀመሰና ያወቀ ሰው ብቻ ለማለት ስለሚችለው ነው፡፡

ቀደም ሲል ላነሳነው ዋና የነፍስ ፍላጐትዎ ብዙ ባለመድኃኒቶች
ሞክረው መፍትሔ አላገኙም ይሆናል፡፡ ካላገኙ ለምን የተመረቀውን ብቸኛ መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስን አይሞክሩም?
“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም
አሳርፋችኋለሁ፡፡” (ማቴዎስ 11፥28)

https://t.me/IWNRSATT
110 viewsSintayehu Nigatu, 10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 21:00:08
በምህረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር
ዛሬም የሰው ልጆች እርሱ በላከው በልጁ
በእየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑና ዘለዓለማዊ ህይወት እንዲያገኙ በዚህች ክቡር ሴት በኩል ይጣራል።
ይህ የመንግስት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካልና አሜን
ዮሐ 3:36_38 ይነበብ


ምንጭ ፦ salem show

https://t.me/IWNRSATT
73 viewsSintayehu Nigatu, edited  18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 20:45:36 አራቱ የብሉይ ኪዳን መስዋዕት

1.የኃጢአት መስዋዕት

ቅድስናን ያመለክታል

2.የሚቃጠል መስዋዕት

አምልኮን ያመለክታል

3.የእህል ቁርባን

ምስጋናን ያመለክታል

4.የደህንነት መስዋዕት

ሕብረትን ወይም አንድነትን ያመለክታል

-------------------------------------------
“የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ለእግዚአብሔርም ስለ ደኅንነት መሥዋዕት በሬዎችን እንዲሠዉ የእስራኤልን ልጆች ጐበዛዝት ሰደደ።”ዘጸ 24፥5

“የወይፈኑን ሥጋ ግን፥ ቁርበቱንም፥ ፈርሱንም ከሰፈር ውጭ በእሳት ታቃጥለዋለህ፤ የኃጢአት መሥዋዕት ነው።”ዘጸ 29፥14

“ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው ወይፈን እንደ ተወሰደው ይወስዳል። ካህኑም ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ያቃጥለዋል።”ዘሌ 4፥10

“ካህኑም ከኃጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ቀንዶች ያደርገዋል፤ የተረፈውንም ደም ለሚቃጠል መሥዋዕት ከሚሆነው መሠዊያ በታች ያፈስሰዋል።”ዘሌ 4፥25


“በእግዚአብሔር ፊት ያለው የናሱ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን የደኅንነቱንም መሥዋዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የደኅንነቱንም መሥዋዕት ስብ አሳርጎአልና በእግዚአብሔር ቤት ፊት የነበረውን የአደባባዩ መካከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ።”1ኛ ነገ 8፥64

https://t.me/IWNRSATT
64 viewsSintayehu Nigatu, 17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 13:57:46 ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ

ቀድሞ ለመለሰው 10 ብር ካርድ ይላካል ።

1.ሙሴ የሞተበትና የተቀበረበት ቦታ ስም ምን ይባላል ? ማስረጃስ ?



⁣            
     
     

የቤት ስራ

https://t.me/IWNRSATT
86 viewsSintayehu Nigatu, edited  10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 14:35:23 ✿ በወንጌል ወደምን ተጠራን ?

➊ ወደሚደነቅ ብርሃን

" እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤"
(1 ጴጥ 2: 9)

➋ ወደ ልጁ ሕብረት ተጠርተናል

" ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።"
(1 ቆሮ 1: 9)

➌ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ተጠርተናል

" መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ።"
(1 ጢሞ 6: 12)
100 viewsSintayehu Nigatu, edited  11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ