Get Mystery Box with random crypto!

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ finottebirhan — ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ finottebirhan — ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @finottebirhan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.16K
የሰርጥ መግለጫ

የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ለማንኛውም ጥያቄ
@Finotebrhan

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 10:17:29
#ብፁዕ_ወቅዱስ_ፓትርያርክ_አቡነ_ማትያስ_በውጭ_ሲከታተሉት_የቆዩትን_ሕክምና_አጠናቅቀው_ጳጉሜን_1_ቀን_2014 ዓ.ም ወደ ሀገረ ኢትዮጵያ ይገባሉ !!!
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሀገረ አሜሪካ ሲከታተሉት የቆዩትን ሕክምና አጠናቅቀው የፊታችን ማክሰኞ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ቅዱስነታቸው ከሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ ካለባቸው የጤና እክል አኳያ በአሜሪካ ሕክምናቸውን ለመከታተል ጉዞ ማድረጋቸው ይታወሳል።

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጤንነት በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከጳጉሜን 1 ቀን ጀምሮ ወደ መንበራቸው እንደሚመለሱ ታውቋል።
#ምንጭ
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ
111 views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:25:47
ጠቅላላ ጉባኤ

የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት የ42ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ነሐሴ 29 ሰዓት 3:00 ይካሄዳል ።
#የእርስዎ ሃሳብ ለሰንበት ት/ቤታችን እድገት ወሳኝነት አለው እና በጠቅላላ ጉባኤው ላይ በመገኘት የአባልነት ግዴታዎን ይወጡ ::
155 views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 17:41:14
የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት #የተከታታይ_ኮርስ_ትምህርት_ለማስተማር_ዝግጅቱን ጨርሶ ምዝገባ ጀምሯል:: በዚህ መሰረት በተለያየ ምክንያት ላቋረጡ እንዲሁም ለአዲስ ጀማሪዎች የኮርስ ትምህርት መማር ለሚፈልጉ በሙሉ በሰንበት ት/ቤቱ ጽህፈት ቤት በመምጣት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ስንገልፅ በደስታ ነው ::
#የተከታታይ_ትምህርት_ንዑስ_ክፍል
335 views14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 15:34:45
#እንኳን_ደስ_አላችሁ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለብፁዕ አባታችን ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ ሰጠ።#ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር የሚኖሩ፤ ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብሩ፤ ታላቅ አባት በመሆናቸው የክብር ዶክትሬቱ እንደተሰጣቸው የዩኒቨርስቲው መረጃ ያሳያል።

በተጨማሪም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለክቡር ዶክተር ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአትሌቲክ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ፋና ወጊ አትሌት እና የኢትዮጵያዊነት ተምሳሌት!
176 views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:38:50 #ትምህርተ_ሃይማኖት_ርትዕት

ክፍል 2

#ሥነ_ፍጥረት

#ሥነ ፍጥረት ማለት ያማረ የተዋበ ፍጥረት ማለት ነው ። "እግዚአብሔርም የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ አየ " እንዲል ዘፍ 1:31#አንድም ሥነፍጥረት ማለት የተስማማ ስምሙ ፍጥረት ማለት ነው ። የማይስማሙ ውሃን ከእሳት ፣ ነፋስን ከአፈር አስማምቶ ፈጥሮዋል #ስምሙ_ፍጥረት ይባላል።እግዚአብሔር ፍጥረት የፈጠረበትን ሥርዓት የምንማርበት ትምህርት ሥነ ፍጥረት ይባላል ። እግዚአብሔር በ6 ቀን 22 ፍጥረታትን ፈጠረ ። ዘፀ 20:8 ሃያ ሁለት የተባሉትም በዓይነታቸው ተመድበው ነው ። አፈጣጠራቸው #በ3 ወገን ነው ። #1ኛ. በሃልዮ / በማሰብ / -7ፍጥረታት #2ኛ.በመናገር /በነቢብ/ -14ፍጥረታት #3ኛ.በመስራት /በገቢር/ -1 ፍጥረት ሰውን ፈጠረ

#የእለተ_እሑድ_ፍጥረታት

እሑድ ማለት አሐደ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መጀመሪያ አንደኛ ማለት ነው ። እግዚአብሔር በመጀመሪያ የፍጥረት ቀን እሑድ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ 7 አንድም 8 ፍጥረታትን ፈጠረ ። እነሱም #ነፋስ_እሳት_መሬት_ውሃ_ጨለማ_ብርሃን_ሰማያትና_መላዕክት ናቸው ። 8ፍጥረት መባሉ ስለምንድነው ቢሉ 7 የሚሉ ሊቃውንት ጨለማና ብርሃንን አንድ አርገው ቆጥረው ሲሆን 8 የሚሉት ደግሞ ለየብቻ ቆጥረው ነው

#የሰኞ_ፍጥረት

በውሆች መካከል ጠፈር ይሁን ብሎ ተናግሮ ከበላያችን የምናየውን ሰማይ ፈጠረና ውሆችን ወደ ላይና ወደታች ከፈለ ፡ ጠፈርንም ሰማይ ብሎ ሰየመው ። ሰማዩም ሙሉ ነጭ አይደለም በውሀና በመሬት ከነበረው ጨለማ ቀባ አድርጎ ፈጥሮታልና ። ሙሉ ነጭ ቢሆን እንደ ፀሐይ ዓይናችንን እየወጋ ለማየት እንዳይከለክለን ነው ። ዝርግነቱም እንደ ወለል ቀጥ ያለ ሳይሆን እንደ ጋሻ ጎበብ ያለ ነው ። ስለምን እንዲህ አደረገው ቢሉ ከጠፈር(ከሰማይ) በታች ያሉ ብርሃናት ብርሃናቸውን የሚነዙ ወደ ላይ ነውና ወደታች ወደምድር እንዲመልሰው ብሎ ነው

#የእለተ_ማግሰኞ_ፍጥረታት

በቃሉ በማዘዝ 3 ፍጥረታትን ፈጠረ ። እግዚአብሔር ቡቃዮችን ፍጥረታትን ሲፈጥር በአበባ በፍሬ ማለትም አበባ ፍሬ እንደያዙ ነው የፈጠራቸው እንጂ በቡቃያነት አይደለም ። ተፈጥሯቸው ከ4ቱ ባህርያተ ስጋ ከመሬት ፣ ከነፋስ ፣ ከእሳት እና ከውሃ ነው ። በባህርያቸው 3 ተግባር አላቸው

#1.ምግብ መውሰድ #2.መርዘም #3.መስፋትና መወፈር እነዚህን መምህራን በ3 መደብ ይመደቡአቸዋል

#1.የሣርና የእህል ዘር አይነት #2.የአትክልት አይነት #3.ሌሎች ዛፍና እንጨት አይነት። በፍሬ አሰጣጣቸው #1.በስራቸው የሚያፈሩ #2.በጎናቸው የሚያፈሩ #3.በአጽቃቸው የሚያፈሩ ተብለው ይመደባሉ ። በፍሬ አሰባሰባቸው ደሞ #1.በጣት የሚለቀሙ #2.በማጭድ የሚታጨዱ #3.በምሳር ሚቆረጡ /በቁፋሮ የሚወጡ/ ተብለው ይመደባሉ ። የማክሰኞ ስነፍጥረት የድንግል ማርያም ምሳሌ ናቸው ይኸውም የመጀመሪያዋ ምድር ያለዘር እፅዋትን እንዳስገኘች ድንግልም ያለ ወንድ ዘር ክርስቶስን አስገኝታለች

Comment @finotebrhan

@finotebrhan
@finotebrhan
@finotebrhan
234 views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 18:56:03 #ክርስቲያናዊ_ስነ_ምግባር

ክፍል 3

#የእግዚአብሔር_የአምላክህን_ስም
#በከንቱ_አትጥራ

ስም ሲባል አንድ ነገር ከሌላው ተለይቶ የሚታወቅበት መጠሪያ ነው ። ስም ጠባይን ግብርንና ሁኔታን እንደሚገልጥ ሆኖ ሊሰየም ይችላል ። እግዚአብሔርም ባሕርዩን ሕልውናውን ግብሩን የገለፁ ብዙ ስም አለው ። በሐዲስ ኪዳንም እግዚአብሔር ወልድ በስጋ ሲገለጥ #አማኑኤል #ኢየሱስ #ክርስቶስ በሚባሉ ስሞች ተጠርቷል። የእግዚአብሔር ስም ባዶ ቃል አይደለም። ኃይሉን ግርማውን ይዞ ይገኛል ። የማይታየው እግዚአብሔር ራሱን የገለጠው በስሙ አማካኝነት ነው

በተለይም ክርስቶስ በስጋ በተገለጠ ጊዜ ስሙን ለዓለም አስታውቋል ።/ ዮሐ 17:26/ ስሙም ከሁሉ በላይ ነው ። /ፊል 2:9/ ስሙ #ቅዱስ ነውና አክብረን ልንይዘውና ልንቀድሰው ይገባል እንጂ በከንቱ ልንጠራው አይገባም ። መላዕክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሚያመሰግኑት አምላክ መሆኑን አውቀን ስሙን በከንቱ መጥራት ግብሩን ማርከስ ነው

በማህበር ስንኖር ከሳሽ ተከሳሽ ስለሚኖር የክርክሩ መፈፀሚያ የእውነት ማረጋገጫ መሐላ ስለሆነ ዳኛው እንዲምል ካስገደደው መማል ይፈቀዳል ። /ዘፀ22:11 ዕብ6:13/ ከዚህ ሌላ ቃል ለመግባት አንድ ነገርን ለመስራት መሐላ መማል ቃል መስጠት የእግዚአብሔር ስም መጥራት የሚያስፈልግባቸው ጊዜ አለ ። እንዲሁም እግዚአብሔርን ለማገልገል ሲሉ ብፅዓት የሚያደርግ አለ ይኸውም በቤተክርስቲያን ስርዓት የተፈቀደ ነው። ለምሳሌ በድንግልና ለመኖር

#በከንቱ_አትጥራ
ከንቱ ማለት በእግዚአብሔር የተናቀ የማይገባ ነገር ማለት ነው ። የእግዚአብሔርን ስም በእንዲህ አይነት ሁኔታ መጥራት እንደማይገባ ይህ ትዕዛዝ ያስተምረናል እነሱም ፦

1.ስጋዊ ፍቃድ 2.ጣኦትን ማምለክ 3.ሐሰተኛ ትንቢት 4.በእግዚአብሔር ስም መማል 5.በእግዚአብሔር ስም መራገም 6.በእግዚአብሔር ስም መጠንቆል ... በነዚህ ሁሉ ስሙን መጥራት በከንቱ መጥራት ነውና በማስተዋል ልንጠብቀው ይገባል

#የእግዚአብሔርን_ስም_የምንጠቀመው_ምን_ጊዜ_ነው ?
1.በፀሎት ጊዜ 2.በሰላምታ ጊዜ 3.በአምልኮ ጊዜ 4.በቡራኬ ጊዜ

...ይቀጥላል ...

Comment @finotebrhan

@finotebrhan
@finotebrhan
@finotebrhan
314 views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 22:04:03 በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአዲስ አበባ አብያተ ክርስትያናት:
21) ምዕራፈ ፃድቃን አቡነ ተ/ሐይማኖት እና ቅ/ገብርዔል ቤተ ክርስትያን

ልዩ ስም:- የካ ክ/ከተማ ሲግናል አደባባይ ወደ ዉስጥ ገባ ብሎ ወይም አድዋ ድልድይ ፖሊስ ጣቢያዉ ወረድ ብሎ ኮንጎ ሰፈር

22) ቱሉ ዲምቱ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ገብርኤልና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ

ልዩ ስም:- አ/ቃ/ክ/ከ ከቱሉ ዲምቱ አደባባይ ወደ አለም ባንክ በሚወስደው አስፋልት መንገድ ታፍ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት /በተመሳሳይ ከአለም ባንክ ወደ ቱሉ ዲምቱ አደባባይ/
ወይም ከቃሊቲ ቶታል ወደ ቱሉ ዲምቱ አደባባይ ታክሲ ተሳፍረው ሲመጡ ታፍ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት
355 views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 22:04:01 ነሐሴ 24

አቡነ ተክለሐይማኖት (ዕረፍት) እና

ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ

በአዲስ አበባበ አህጉረ ስብከት በእነዚህ አብያተክርስትያናት በአለ ንግሱ ይከበራል።

1)     ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት ኪዳነምህረት
ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ  ጉለሌ

2)     ገዳመ ኢየሱስ
ልዩ ስም፡-ልደታ ክ/ከ ሆላንድ ኤምባሲ

3)     ኮልፌ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለሐይማኖት እና  ቅዱስ ገብርኤል
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ፊሊዶሮ

4)     ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሐይማኖት
ልዩ ስም፦ልደታ /ክ/ከ መርካቶ

5)    ሲኤምሲ መካነ ጻድቃን አቡነ ተክለሐይማኖትና ቅድስት ልደታ ለማርያም
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ መሪ ሎቄ ለገጅጃ

6)    ደብረቢታንያ አቡነ ተክለሐይማኖት እና ቅድስት ልደታ ለማርያም
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ቆሬ 5 ቁጥርና 2 ቁጥር ማዞርያ

7)    ቤላ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ቤላ ፈረንሳይ ፓርክ

8)     ፍኖተሎዛ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ብርጭቆ ኮንዶሚንየም

9)    ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ  ካቴድራል
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ጉርድ ሾላ

10)    ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማያት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ አባዶ

11)    የረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ጎሮ

12)     ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድሃኔአለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ ቀጨኔ መድሃኔአለም

13)   ገነተ ኢየሱስና ገነተ ማርያም አብያተ ክርስትያናት
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ፈረንሳይ 41 ኢየሱስ

14)    መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል፤ጻድቁ አቡነ ተክለ ሐይማኖት እና ቅድስት አርሴማ  ገዳም
ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ ቀጨኔ

15)     ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔአለም ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ  ቦሌ ቡልቡላ

16)   ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ
ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ መስቀል ፍላወር

17)     ኤርቱሞጆ ፍኖተሰላም ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ እና አቡነ ተክለሐይማኖት
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ኤርቱሞጆ

18)   ደብረይድራስቅዱስጊዮርጊስቤ/ክ
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ቤተል

19)  ሰርጢ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ሰርጢ ማርያም

20) መጠሊ ደብረ አሮን ፍልፍል ዋሻ ቅዱስ ገብርኤል  እና አቡነ ተክለሐይማኖት
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ገላን ጉራ ገበሬ ማህበር መጠሊ
329 views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 07:33:14
385 views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 07:30:36 ​​​​እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!

የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው
@finotebrhan
ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ
@finotebrhan
ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች
@finotebrhan
ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ
@finotebrhan
ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/
@finotebrhan
የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል
@finotebrhan
ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው
@finotebrhan
በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን
@finotebrhan
በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን

@finotebrhan
@finotebrhan
@finotebrhan
373 views04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ