Get Mystery Box with random crypto!

የሚታደርጉትን ሁሉ በጥንቃቄ አድርጉ በዚህ ርዕስ በቅርብ ጊዜ አንድ መልእክት መጻፈ ይታወሳል ።ዛ | ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)

የሚታደርጉትን ሁሉ በጥንቃቄ አድርጉ

በዚህ ርዕስ በቅርብ ጊዜ አንድ መልእክት መጻፈ ይታወሳል ።ዛሬም ብሆን ይህንኑ ርዕስ በመጠቀም ሌላውን ጉዳይ ማንሳት ግድ ሆነብኝ ።ምክንያቱም የዛሬው ሾልኮ ገቢ ሐሰተኛ ነው ።

ብዙ ጊዜ የሚንከተላቸው ሰዎች ማናቸው የሚለውን ጥያቄ ሳንጠይቅ እንከተላቸዋለን ።በኃላ ግን በተሳሳተ አቅጣጫ መሆናችንን ካወቀን እንቆጫለን !!

ዛሬ ለመንገር ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የተባለው ግለሰብ ማነው ? የሚል ይሆናል ።

ዳግ ሂዋርድ ሚልስ ከስድሳ (60) በላይ መጽሐፎች የጻፈና united denominations originating from the lightouse group church መስራችና ባለራዕይ በመሆን ይታወቃል ። የሆነው ሆኖ ዛሬ በእርሱ ዙሪያ መጻፍ ያስፈለገው ለምንድን ነው ?? ብባል ብዙ አገልጋዮች ፣ወጣቶች እና አንባቢ የሆኑ ክርስቲያኖች መጽሐፎቹን ያነባሉ ።ነገር ግን ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የሐሰት ትምህርት አስተማሪ መሆኑን አለመረዳታቸው ደግሞ እጅግ በጣም የሚገርም ነገር ነው ።

እኔ ዛሬ ይህን ለመጻፍ የተነሳውት መጽሐፎችን አታነቡ ለማለት ሳይሆን ሲታነቡ ግን በጥንቃቄ እንታነቡ እጋብዛለሁ !! እውነት ለመናገር ከመጽፎቹ የተጠቀምኩት ነገር የለም ማለት ባልችልም ግን የስህተት አስተማሪ መሆኑን እንድታውቁ እፈልጋለሁ ። ለጠቅላላ ዕውቀት ብንጠቅምም ከመዳን ጋር በሚገናኙ ነገሮች ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ።

ማነኛውም ሰው ፊጹም ላይሆን ይችላል ።ነገር ግን በራሱ ድካም ለሌላው መሰናክል ሲሆን ዝም ማለት የለበትም ።
ስህተቱን ምንድን ነው ?
ለዚህ ጥያቄ ከእኔ በላይ መጽሐፎቹ በግልጽ ሊያስረዱ ይችላሉ ። ይንም ለአብነት ያህል ድነትን እንዴት ልትሰብክ ትችላለህ ከሚለው መጽሐፍ በላይ በኩል ያለውን ፎቶ አቅርብያለሁ !!
ይቀጥላል .