Get Mystery Box with random crypto!

በድጋሚ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመዳን አስተምህሮ  ·        ሁሉም ሰው ኃጢአተኛ ነው። o    | ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)

በድጋሚ

መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመዳን አስተምህሮ


 ·        ሁሉም ሰው ኃጢአተኛ ነው።
o   ሁሉም በክርስቶስ ከማመኑበፊትኃጢአተኛ ነው
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርምክብርጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ ፫፣ ፳፫
- ከዚህ ኃጢአት /እና ሞት/ መዳን አለብን፤መድኃኒቱምኢየሱስ ነው፤
እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸውያድናቸዋልናስሙንኢየሱስ ትለዋለህ።  ማቴ ፩፣ ፳፩

o   በክርስቶስ ካመንን በኋላምእንኳኃጢአት ይኖርብናል - ባልዳነሥጋባልዳነች ዓለም ስለምንኖር
ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥​እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
፩ ዮሐ ፩፣ ፰
- ከዚህ ኃጢአት መንጻት አለብን፤ /ከዳንንበኋላበየጊዜው ስለምንቆሽሽ/
የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአትሁሉያነጻናል።  ፩ ዮሐ ፩፣ ፯

        ሁሉም የሚድነው በክርስቶስ በማመንብቻ ነው።
በልጁየሚያምን የዘላለም ሕይወትአለው፤  ዮሐ ፫፣፴፮
        ሌላ መድኃኒት የለም
መዳንምበሌላበማንምየለም፤እንድንበት ዘንድየሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስምከሰማይ በታች ሌላየለምና።  የሐዋ ፬፣ ፲፪
        አምነን መዳናችንን የምረጋግጠውአሁን ነው።
እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁንኵነኔየለባቸውም። ሮሜ ፰፣ ፩
        ካላመንንም ፍርዱ አሁን ነው።
በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምንግንበአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን​ተፈርዶበታል።። ሮሜ ፰፣ ፩


        ማመን ማለት ስለክርስቶስ መረጃ እናእውቀትመያዝ ሳይሆን የክርስቶን አዳኝነትከውስጥ መቀበልነው። ይህም እምነት ከልብየሆነ እና የተፈተነ  ሊሆንይገባል፡፡
- በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ራሳችሁንፈትኑ፤ ፪ ቆሮ ፲፫፣ ፭
/በሃይማኖት - ማለት በእምነት እንጂበተቋምአይደለም፤  ያን ጊዜ ተቋም አልነበረም።/
- ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋውወርቅይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነእምነታችሁ፥ ኢየሱስክርስቶስ ሲገለጥ፥ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝዘንድ አሁንለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩፈተናአዝናችኋል።  ፩ ጴጥ ፩፣ ፮ - ፯
        በክርስቶስ አምነን ከዳንን በኋላመልካም ሥራእንሠራለን።
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድእግዚአብሔር​አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙንሥራለማድረግበክርስቶስኢየሱስ ተፈጠርን።  ኤፌ ፪፣ ፲
/ተፈጠርን፡ ሲል- አዲስ ማንነትን ያሳያል፣ እንጂአዲስየሚፈጠር ነገር የለም።/
መልካም ሥራ የሕይወት መገለጫ ፍሬ ነው፡፡የሕይወትሕግ እንደሚያሳየው ሕይወት ሳይኖርፍሬ አይመጣም፡ - ያልጸደቀ አያፈራም፡ /ዛፍምቢሆን/፡ ጽድቅ ደግሞበክርስቶስ ነው፡፡
          በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነትበኩልእንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።    ገላ ፫፤፳፬
 በኛ ሕይወት የሚገለጠው መንፈሳዊ ፍሬየመንፈሳዊሕይወት /የመንፈስ ቅዱስ ውጤትነው፡፡ /ገላ ፭ ፣፳፪
        በሥራችን መጠን ክብር፣ ሽልማት፣አክሊል፣ ዋጋ፣ደመወዝ.. እናገኛለን።
እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደሥራውመጠንእከፍልዘንድዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። ራእ ፳፪፣ ፲፪
        የምንድነው በእምነት እንጂ በሥራአይደለም።
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህምየእግዚአብሔርስጦታ ነው እንጂ ከእናንተአይደለም፤ ማንምእንዳይመካ ከሥራአይደለም።  ኤፌ ፪፣ ፰ - ፱
/እዚህ ሥራ የተባለው ከኛ የሆነውን ሁሉያካትታል፣መልካም ሥራ፣ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት..
የምንድነው በኛ ሥራ ሳይሆን ክርስቶስበመስቀል ላይበሠራው ታላቅ የማዳን ሥራበማመን ነው፡፡
መዳን በኛ ሥራ ነው ካልን ቢያንስ ሁለትጥያቄዎችንመመለስ አለብን፡፡
1.     በሥራችን የምንድን ከሆነ የክርስቶስ ሞትጥቅሙምንድን ነው?

የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስበሕግ በኩልከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱሞተ።

ኤፌ ፪፤ ፳፩

2.     ስንት መልካም ሥራ ስንሠራ ነውለመዳንየምንበቃው?
እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደትበሚሆነውመታጠብና በመንፈስ ቅዱስበመታደስ አዳነን እንጂ፥እኛ ስላደረግነውበጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤  ቲቶ ፫፤ ፭
በክርስቶስ አምነን ከዳንን በኋላም ኃጢአትእንሠራለን፡ነገር ግን ወደነው፣ ሆን ብለን፣በተደጋጋሚ ሳይሆን - ሥጋችን ስላልዳነበእርሱ ግፊት ሲሆን ይህም ድልልናደርገውየሚገባ የሥጋ ትግል ነው፡፡ የጾምናጸሎትሚና እዚህ ላይ ወሳኝ ነው፡፡
በእኔ ማለት በሥጋዬበጎነገርእንዳይኖር አውቃለሁና፤ፈቃድ አለኝና፥መልካሙን ግን ማድረግ የለኝም።​የማልወደውን ክፉን ነገር አደርጋለሁና ሮሜ ፯፣፲፰
        በክርስቶስ አምነን ከዳንን በኋላምኃጢአት ስንሠራየምንነጻው በንስሃ- በክርስቶስ ደም ነው። ይህም ንስሐመግባትበየጊዜው ልናደርገው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅርሊለንከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅነው። ፩ ዮሐ፩፣ ፱
የልጁም የኢየሱስክርስቶስደምከኃጢአት ሁሉያነጻናል። ፩ ዮሐ ፩፣ ፯
ለኃጢአት የተከፈለ ውድ የሕይወት ዋጋየክርስቶስስለሆነ ሌላ የሚያነጻ ነገር የለም፡ሊኖርም አይችልም፡፡
/ልብ እንበል፡- ሊያነጻን፣ ያነጻናል - ስለመንጻት/ስንቆሽሽ/ እንጂ ስለመዳን አይደለም።/

ቢገባንም ባይገባንም የእግዚአብሔር ቃልእውነት ነው፤ይሠራል።

ካመንንበት እና ከተቀበልነው በኛም ሕይወትይሠራል፤​ይለውጠናል፡፡


እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌንየሚሰማየላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወትአለው፥ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደፍርድአይመጣም። ዮሐ ፭፣ ፳፬

---------------------------//-----------------



https://t.me/IWNRSATT