Get Mystery Box with random crypto!

⛤Ιѕℓαмιc нιѕтory⛤

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_historyyy — ⛤Ιѕℓαмιc нιѕтory⛤ Ι
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_historyyy — ⛤Ιѕℓαмιc нιѕтory⛤
የሰርጥ አድራሻ: @islamic_historyyy
ምድቦች: ስዕሎች እና ፎቶዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.48K
የሰርጥ መግለጫ

"በጊዜያቱ እምላለሁ ሰው ሁሉ በእርግጥ በኪሳራ ውስጥ ነው እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት በእውነትም አደራ የተባባሉት በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ"
ሱ,ዐስር፦(1፥3)
ለማንኛውም ጥያቄ እና ለማስታወቂያ ስራ ➱ @Mahiro_fkr
You tube channel➘➘➘
https://youtube.com/channel/UCUYbaX1b-BcwERNZybzSNYw

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-12-31 21:11:43 “የእናት ሀቅ.. መች ይለቅ!”
(እውነተኛ)-ክፍል ሁለት/መጨረሻ/
ፀሐፊ :አብዱልጀባር ፋሪስ


ታላቅ እህት ሮጣ ወደ ቤቱ ስትደርስ እናት መሬት ላይ ተዘርራለች። አይኗን ማመን አልቻለችም። ...ይሄኔ ኡኡታዋን አቀለጠችው። የአካባቢው ሰው ወደ ቦታው አቤት ሲል ተሰበሰበ። ነገሩ ካለቀ ወዲህ ምን ይፈይድና ነው። ህዝቡ ጉድ እንዲል... ልጅ እናቱን ገድሎ ሬሳዋ ላይ ቆሟል። እህት በልቅሶ እናት ላይ ተደፍታ ታለቅሳለች። “አ... ወይኔ ሀደኮ, ሲ አጄሴ ሚቲ” እህት በኦሮምኛ እያወራች ትንሰቀሰቃለች። ህዝቡ ለቅሶና ዋይታውን አቀለጠው። በአቅራቢያ ለሚገኘ ፖሊስ ጣብያ ተደውለ። ልጅ በነብስ ግድያ ወንጀል እጅ ከፍንጅ በመያዙ ዘብጢያ ወረደ።

መንደርተኛ ለተራ ሞት እንደሚያለቅስ የታወቀ ነው። በዚች ሚስኪን እናት ሞት ደግሞ ይበልጥ ልባቸው ተሰብሯል። ሀዘናቸውን አሟሟቷ እጥፍ ድርብ አድርጎ፣ ለቅሶው እና ወሬው ሀገር አዳርሶ ነበር። መቼስ ሬሳን ተሸክመው አይቆዩና.. እናት ልትቀበር በእስልምና ስርዓት መሰረት ሰውነት ተገነዘ። በነጭ አቡጀዲ(ከፈን) ተጠቅልላ ወደ ማይቀረው ቤቷ መጓዟ ነው። በእግሯ ላትሄድ ሸክም አይቀርላትም... ይሄኔ ነው ሀገር አይቶት የማያውቅ ጉድ እንግዳ የገጠማቸው።

የእናት እሬሳ(ጀናዛ) ተገንዞ ከተከፈንበት ቦታ ንቅንቅ አልልም አለ። የሀገሩ ወጣት፣ ወጠምሻ ሊያነሳው ቢሞክር ፍንክች አልልም አለ። በተቀመጠበት ቦታ እንደ አለት ደርቆ ወደ ላይ ሚያነሳው ጠፋ። የሀገሬው ሰው ጉድ ብሎ... ምን እናድርግ ሲል፣ ከፈሎዎቹ ሼኽ ይጠራና መፍትሄ ያበጅልን ሲሉ ሀሳብ ሰጡ። በአካባቢው ለሚገኙ ሼኾች ጉዳዩ ተነግሮ ወደ ቦታው ፈጥነው ደረሱ። እነሱም ለማንሳት ቢሞክሩ እንቢ አላቸው።

ነገሩን በጥልቀት ሲጠይቁ የእናት አሟሟት ተነገራቸው። መፍትሄ ነው ብለው ያሰቡት እናትን የገደላት ልጅ ከእስር ቤት መጥቶ እንዲያነሳ ነው። ልጅ ከእስር ቤት ተጠራና በፖሊስ ታጅቦ እቦታው ደረሰ። ከአራቱ የቃሬዛው ቅርንጫፎች አንዱን ይዞ ሎሎች ሶስት ሰዎች ተጨምረው ብድግ ሲያደርጉት፤ እንቢ ብሎ የነበረው እሬሳ ተነሳ። መስጂድ ተወስዳ ተሰገደባት። ሰላቱ እንዳለቀ ከልጅ ጋር ሆነው ወደ መቀበርያ ቦታዋ ወሰዷት። ችግሩ እንዳለቀ በማሰብ ልጅ ወደ እስር ቤት እንዲመለስ ተደረገ። የቀብር ቁፋሮው እንዳለቀ... እናትን ወደ ለህድ (የሬሳ መጋደምያ) ቦታ ለማስገባት ቢሞክሩ.. ቢሉ.. እንቢ አላቸው። እናት በድጋሚ መሬት ላይ ደርቃ ቀረች። ልጅ ከእስር ቤት ተመልሶ መጥቶ እናቱን ተሸክሞ ወደ ለህድ እንዲያስገባ ሆነ።

በድጋሚ ልጅ መጥቶ ሬሳውን ሲያነሳው እንደ ቀልድ ብድግ ብሎ ተነሳለት። ይህንን ሁሉ ተዓምር ሀገሬው ቆሞ ይከታተላል። በድጋሚ ልጅ እናቱን ይዞ ወደ ለህድ ውስጥ ሲያስገባ... ሌላ ተዓምር ይመለከቷል። እናቱን ወደ መጋደሚያዋ እንዳስተኛት አስገራሚ ተዓምር ተከሰተ። ልጅ ጠብቶ ያደገው የእናቱ ጡት ከነበረበት መጠን ጨምሮና ረዝሞ ልጅ ላይ እንደ እባብ ተጠመጠመበት። በነገሩ ነብሱ እስክትወጣ የደነገጠው ልጅ.. ጩኸቱን አቀለጠው። ሰዉ ምን ጉድ ነው ብሎ ሲመለከት ያው ነው። የእናት ጡት እንደ ትልቅ ዘንዶ ልጅ ላይ ተጠምጥሞ ማፈናፈኚያ አሳጥቶታል።

በነገሩ በጣም ደነገጡ። የእናት ሀቅ መሆኑን ሁሉም ተገንዝቦ ነበር። ሆኖም የሞተ አይነሳና ልጅን ከእናቱ ጡት አላቅቀው ለማዳን ቢሞክሩም.. ጭራሽ እንቢ አላቸው። ይሄኔ አዋቂዎቹ የእናት ጡት ይቆረጥ ወይስ ልጅን ከነእናቱ እንድፈነው ብለው ካጤኑ በኋላ አንድ ውሳኔ ላይ ደረሱ። “የአላህ ውሳኔ እና ተዓምር ነው። ልጅን ለማላቀቅ መሞከር ከንቱ ልፋት በመሆኑ እዛው ከእናቱ ጋር ድፈኑት። ለሰዎችም አላህ ያሳየን ተዓምር ነው” ሲሉ ጉዳዩን ቋጩት። ጨካኙ ነብሰ ገዳይ ልጅ አንቆ ከገደላት እናቱ ጋር በአንድ ጉድጓድ ተቀበረ! ነገሩም በዚህ ተቋጨ።

ወዳጆቼ አሁን ላይ ልጅ እናቱን መግደል፤ አባቱን ማሰቃየት፤ ብሎም ህይወቱን ማጥፋት እየበዛ ይገኛል። ከዚህ በታች ሳይሆን አሳሳቢውም እናትና አባትን አለማክበር.. ትዕዛዛቸውን አለመፈፀምም ሌላው ትልቅ ወንጀል ነው።ወዳጆቼ! ወላጆቻችሁ የእናንተ ጌጥ ብቻ ሳይሆን መነሻችሁም ናቸው። በነሱ የሚያፍር እና መብታቸውን የማይጠብቅ ከእንደዚህ አይነቱ ውርደት እስከ መጪው አለም ቅጣት ቢጠነቀቅ ይሻለዋል። አደራችሁን በህይወት ላሉት እዝነትና ርህራሄን ሰጥተን፥ ከትዕቢትና ግልምጫ በመቆጠብ ደስተኛ እናድርጋቸው። የሞቱብንን ደግሞ በፀሎታችን ሁሌም ልንዘክራቸውና መሀርታ ልንለምንላቸው ይገባል።

ታሪኩ ፍፁም እውነትኛ ነው። እኔም ለማመን ከብዶኝ ነበር.. ነገር ግን በዘመናችን የተከሰተና ከአካባቢው ሰዎች ምስክር የተሰጠው ነው አ። መማሪያ ሚፈልግ ይህ በቂና ከበቂም በላይ ነው። እኔ የሰማሁትን ለናንተ በማካፈል ግዴታዬን ተወጣሁ። እናንተም ሼር በማድረግ ግዴታችሁን ተወጡ። ለቻናሌ ሳይሆን ለመልዕክቱ ስትሉ ለምታውቁት ሰው ሁሉ አስተላልፋ። አብራችሁኝ ስለነበራችሁ አመሰግናለሁ። አላህ ያክብርልኝ!

join & share
https://t.me/+jPQLXna9F-E3ZDQ0
633 viewsМαнɪᴛɪ, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 21:11:42 “የእናት ሀቅ.. መች ይለቅ! ”
(እውነተኛ)-ክፍል አንድ
ፀሀፊ ፡አብዱልጀባር ፋሪስ


ይህንን ታሪክ የምጽፍላችሁ በቅርቡ አያቴና እናቴ ካካፈሉኝ ነው። እውነተኛ እና እዚሁ ሀገራችን ውስጥ የተከሰተ ጉድ የሚያስብል ነው። በመጀመርያ ቻናሌን ሁሌም Unmute በማድረግና pin to top የሚለውን ተጭነው በቀላሉ መከታተል ይችላሉ። ቻናላችን ፍፁም ከCopy paste የፀዳ ነው። በዚህም አዳዲስ ፅሁፎችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ወሬ ሳላበዛ ታሪኩን ልቀጥል..

ታሪኩ በቅርቡ ከአንድ ወይም ሁለት አመት በፊት የተከሰተ ነው። እናት ከልጆቿ ጋር ኑሮዋን መስርታ መኖር ከጀመረች ሰነባብታለች። የመጀመርያ ትሁን ባይነገረኝም ታላቅ ልጇ ትዳር መስርታ መኖር ጀምራለች። ታድያ ታናሹ ወጣት ልጅሆዬ እናቱ ላይ እንደ ልቡ ይደነፋል። በዚህ ስራው እናት ከልብ ትፈራዋለች። ፍራቻዋ የመነጨው እሱ ለሷ ከሚያሳያት ትዕቢት እንጂ ሌላ አይደለም። ይገርማል የሰው ነገር! ሽንቱን በእጇ ጠርጋ ያሳደገችው እናቱን ግልምጫው አንሶ ሊመታት ይቃጣዋል። ምን ዓይነት ጭንቅላት ነው ይህን ሚቀበለው!!

እናም ከእለታት በአንዱ ቀን ልጅ ለእናቱ የሞባይል ስልኩን ቻርጅ እንድታስደርግለት አስጠንቅቆ ይሰጣታል። ወቸው ጉድ! እናቱን ይልካል.. እናት በትዕዛዙ መሰረት ገበያ ስትወጣ ስልኩን በጡቶቿ መሃል ቋጥራ ከምትይዘው ብር ጋር አያይዛ ታስቀምጠዋለች። ግብይቷን እንደጨረሰችም የልጇን ስልክ ቻርጅ ለማስደረግ ብትመልከት ከቦታው አጣችው። በድንጋጤ በአካባቢዋ ፈለገች።

ስትባክን ውላ ምንም ልታገኝ ስላልቻለች በፍራቻ ወደ ታላቅ ልጇ ቤት አመራች። 9 ወር በሆዳ ተሸክማው፣ 2 ዓመት ያጠባችውና ተንከባክባ ቆንጥጣ ያሳደገችው ልጁን ትፈራዋለች። የሰው ነገርኮ ጉድ ነው ወዳጆቼ! ግና ልጇ ቤት ደርሳ ችግሩን ነገረቻት። ስልኩ ካስቀመጠችበት መጥፋቱንና ልጅየውም እንደሚገላት አስረድታ አብራት እንድትሄድ ተማፀነቻት። ልጅ ምንም ሳይመስላት “ኧረ እማዬ ምንም አያደርግሽም። ይልቅ እመጣለሁ። ሂጂ” ብላ ከነፍርሃቷ አሰናበተቻት። እናት ሁሉ ነገር ጠቦባታል። ቤት ስትደርስ አንዳች ክፋ ነገር እንደሚገጥማት ጠርጥራለች። ከዚህ ስሜት ጋር ቤት ደረሰች። ቤት ስትደርስ አንዳች ክፋ ነገር እንደሚገጥማት ጠርጥራለች። ማይደረስ የለምና ከዚህ ስሜት ጋር ቤቷ ደረሰች። ልጅየው ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ሆኖ ቤት ተቀምጧል። እናት ከበሩ እንደገባች በጥያቄ ጀመራት። “ስልኬን ስጪኝ” ብሎ ከተቀመጠበት ወደሷ ተራመደ። አንዳች ነገር እንዳይደርስባት የሰጋችው እናት ተርበደበደች። ልጇ ከሚያደርስባት ክፋ ነገር ለማምለጥም እንዲህ ብላ የጠፋውን ስልክ እንደምትክሰው ለማሳመን ንግግር ጀመረች..

“ይሃውልህ የኔ ልጅ! እኛ ቤት ያለችውን ላም ከነ ጥጃዋ ወስደህ መሸጥ ትችላለህ። በምታገኘው ብርም የጠፋብህን ስልክ ትተካለህ። ስልክህ ካስቀመጥኩበት ወድቆ ጠፍቷል” አንዳች ነገር እንዳይደርስባት ትንቀጠቀጣለች። ልጅ ይሄንን ንግግር እየጠበቀ ይመስል እናቱን ዘልሎ አንነቃት። ጎሮሮዋን ይዞ ትንፋሽ እስኪያጥራት አንጠራራት።

ውይይ የሰው ጭካኔ!! እናትን አንቆ ለመግደል ይቃጣል። ሊያውም በተልካሻ ምክንያት። ምናለ እንኳን ስልኩን ልጁን እንኳ ብትደግልበት ባይነካት። እኮ! እናት ናት። እሷ ባትወልደው ከየት አባቱ ይገኝና ነው?!! የጠፋበትን ስልክ ዋጋ እጥፍ የሚሆን ንብረትም "ተክተህ ውስድ" ብላ እየተማፀነችው፤ በእንቢተኝነቱ ፀና። እንዳነቃትም እዛው ገደላት። አዎ! እናቱን አንቆ ገደለ።

ያ አላህ! ለተራ ስልክ ብሎ እሱንም ስልኩንም እንዲገኝ የመጀመርያ ሰበብ የነበረችውን እናቱን ገደለ። በድርጊቱ በጣም ነበር ያዘንኩት። እናቴ ይህንን ስትሰማ በጣም ነበር ያለቀሰችው። የሞተችውን ባታውቃትም፤ ሰው ሊያውም እናት በልጇ ታንቃ ስትሞት መስማት ይዘገንናል። ታላቅ እህት ሮጣ ወደ ቤቱ ስትደርስ እናት መሬት ላይ ተዘርራለች። አይኗን ማመን አልቻለችም። ይሄኔ ኡኡታዋን አቀለጠችው...

ልጁ ምን እንደገጠመው በክፍል ሁለት(በመጨረሻው)ይቀጥላል... እባካችሁ ሼር!! በናንተ ምክንያት ብዙ ሰው የእናቱን ክብር ሊያውቅና ሊረዳ ይችላል። ታሪኩ በጣም አሳዛኝ ነው። በዚህ አላበቃም የልጁ ጉዳይ። በክፍል 2 እንገናኝ። ቸር ቆዩልኝ!!

https://t.me/joinchat/jPQLXna9F-E3ZDQ0
833 viewsМαнɪᴛɪ, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 23:20:43
ባለ ትዳር ነሽ ወይስ ገና አላገባህም
ወይስ መንገድ ላይ

ስለ ፍቅር እና ትዳር በጣፋጭ ትረካዎች እያዋዛ የሚያቀርብ ፍቅር የሆነ ቻናል ይዘን ብቅ አልን!

JOIN በማለት ብቻ ቤተብ ይሁኑ!
343 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 20:50:38
ሁላችሁ ተሳተፉ ውዶቼ የጁምአ ቀን ጥያቄ ነው 200 ብር ሽልማት አለው!

1, ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ የጁምአ ቀን ሱና አይደለም??

ሀ) ሲዋክ መጠቀም ለ) ለወንድ ሽቶ መጠቀም

ሐ) ገላን መታጠብ መ) ለሴት ሽቶ መጠቀም

ሁላችሁም ተሳተፉ መልካም ጁምአ መልካም ዕድል
97 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 21:53:39
ነሺዳ ይወዳሉ እንግዲያውስ ይሄ ቻናል ሊያመልጦት አይገባም አዳዲስ ነሺዳዎች የድሮ ነሺዳዎች በቃ ምን ልበላችሁ የፈለጋችሁትን ነሺዳ ማግኘት ትችላላችሁ።
የTelegram ምርጥ ምርጥ ነሺዳ መረጥ መረጥ አርገው join ይበሉ ይደሰቱ ደሞ በትንንሽ Size መሆኑን አይዘንጉ!
ከናንተ ሚጠበቀው JOIN ማለት ብቻ ነው

@adis_neshida @adis_neshida
1.0K viewsA͛bu~di , 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 20:58:46 አስቲ ማነው ረመዳን የናፈቀው
181 viewsA͛bu~di , 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 20:58:41
ነሺዳ ይወዳሉ እንግዲያውስ ይሄ ቻናል ሊያመልጦት አይገባም አዳዲስ ነሺዳዎች የድሮ ነሺዳዎች በቃ ምን ልበላችሁ የፈለጋችሁትን ነሺዳ ማግኘት ትችላላችሁ።
የTelegram ምርጥ ምርጥ ነሺዳ መረጥ መረጥ አርገው join ይበሉ ይደሰቱ ደሞ በትንንሽ Size መሆኑን አይዘንጉ!
ከናንተ ሚጠበቀው JOIN ማለት ብቻ ነው

@adis_neshida @adis_neshida
181 viewsA͛bu~di , 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 20:23:34
ከእያንዳንዱ ስኬታማ ወንድ ጀርባ ሴት አለች…
የበለጠ ስኬት ከፈለጉ ፣
ብዙ ሴቶች ሊኖሩህ ይገባል!"
┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄
t.me/+jPQLXna9F-E3ZDQ0
766 viewsA͛bu~di , edited  17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 22:49:36 ሀናን እባላለው አሁን 22 አመቴ ነው ከልጅነቴ ጀምሮ ቤተሰቦቼ በዲን ትምህርት ኮትኩተው ነው ያሳደጉኝ ከቤተሰቦቼ ውጪ ምንም ህይወት አላውቅም ነገር ግን ዩኒቨርሲቲ ከገባው እና አንድ ወንድ ከተዋወኩ ቡሀላ ብዙ ነገሮቼ ተቀያየሩ ከእለታት አንድ ቀን....

ሙሉውን ለማንበብ ክፈት የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ!


ክፈት
ክፈት
674 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 19:33:08
~

«ሟች ማለት ሩሁ ከሰውነቱ የወጣችበት ማለት አይደለም ፣ ይልቁንስ ለጌታው በሱ ላይ ያለበትን ሀቅና መብት ያልተገነዘበ ነው።»

ኢብኑል_ጀውዚይ ረሒመሁሏህ
1.9K viewsA͛bu~di , 16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ