Get Mystery Box with random crypto!

☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ huda4eth — ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA
የቴሌግራም ቻናል አርማ huda4eth — ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA
የሰርጥ አድራሻ: @huda4eth
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.10K
የሰርጥ መግለጫ

☀ሁዳ መልቲሚዲያ - ‌🇭‌🇺‌🇩‌🇦 ‌🇲‌🇺‌🇱‌🇹‌🇮‌🇲‌🇪‌🇩‌🇮‌🇦 -قناة هدى الاسلامية
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ንፁህ ኢስላማዊ እውቀት ይደርሳቸው ዘንድ እንሰራለን!
ለአስተያየት @nuugaa

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-04 18:21:11
በአላህ ፈቃድ ዛሬ እሁድ ግንቦት 27/2015 ወደ ምእራብ ኢትዮጵያ በተደረገ ቃፊላ የዳዕዋ ጉዞ 500 ሰዎች በኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ እጅ ኢስላምን ተቀብለዋል።

አላህ ፅናትና ጥንካሬን እንዲለግሳቸው እንለምነዋለን።

አልሐምዱሊላህ

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
Ibnu Mas'oud Islamic Center

@merkezuna
4.7K views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 18:15:58
አንድ ወንድሜ እንዲህ ብሏል:-

"አሰላሙዓለይኩም ሁዳ እንዴትነህ ሀቢቢ
ለወንድማችን እርዳታ እሚሆን በቲኒሹ ሰበብ ለመሆን ሸር አድርጊያለሁ አላህ አፊያውን ይመልስለት የምንግዜም ዱዓችንነው አብሺሩ ሁሉም ለኸይርነው"

በማለት ለወንድማችን ሙከረም አስተዋፅኦ አበርክቷል።
4.1K viewsedited  15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 17:23:26
#Update
#የእናቱ_አካውንት_ሞባይል_ባንኪንግ_መስራት_ጀምሯል።

ይህን ተማሪ ሙከረም አስራር

አላህ  ሂወቱን ካተረፈል በኋላ  ጤናውን  ለመመለስ
የ ቤተሰቦቹ አቅማቸው ደካማ ነው
እንደምታቁት የሎሚ ሜዳ ልጅ  ለድንገተኛ አደጋ የሚሆን ገንዘብ ይቅር እና የእለት ወጪም ከጉሊት ቸርችረው ነው ሚተዳደሩት ሙከረም ደግሞ የቤቱ የመጀመሪያ ልጅ ነው።

በጣም የሚገርመው
አባትየው አካውንት እንኳን ስለሌለው አብሯቸው እየተሯሯጠ ያለውን የወንድሙ ማለትም የልጁን አጎት አካውንት ነው የሰጠን አሁን ግን የእናቱን አካውንትም አጊንተናል

ስለዚህ  ሙሉ ጤናው ተመልሶ እንድናይ ሁላችንም የአቅማችን በፍጥነት ልንረባረብ
የግድ ነው።

አካውንት ቁጥር የእናት ነው።

1000063481908 ዛይዳ አብዶ ኢሳ

0911836854 (ሱፍያን አጎት ነው)
0921893173 (ዛይዳ እናት ናት)
0920030742 (አስራር አባት ነው)

ቀኑ ደርሶ ለዲናችን ሂወታችን እስክንሰዋ
ገንዘባችንን እየሰዋን የተጎዱትን እየተንከባከብን እንቆያለን
4.3K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 11:57:11 በአላህ ፈቃድ የሰማእት ወንድሞቻችን የቀብር ስነስርዓት በኮልፌ መካነ መቃብር

እለተ ጁሙዓ ግንቦት 24 ቀን 2015 የብልፅግና ወታደሮች አንዋር መስጂድ ሰግደው በሰላም ሲወጡ በነበሩ ንፁሀን ሙስሊሞች ላይ በከፈቱት ተኩስ ነፍሳቸውን የተነጠቁ 4 ወንድሞቻችን በእለተ ቅዳሜ ግንቦት 25 የቀብር ስነስርዓታቸው ተከናውናል።

በእለቱ በርካታ ሙስሊሞች ሽኝት ያደረጉላቸው ሲሆን ጀናዛቸው ላይም የሽኝትና ዱዓ ሶላት ስነስርአት ተደርጓል።

ሁዳ መልቲሚዲያ ሙሉ ቆየረታውን እንደሚከተለው አዘጋጅተነዋል።



4.4K viewsedited  08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 08:10:32 የፈተና መንስኤዎች እና መፍትሄዎቻቸው

መደመጥ ያለበት ጠቃሚ #ወቅታዊ ትምህርት

በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እየደረሰ ላለው ችግር ሰበቡ ምንድነው?

ከነዚህ ችግሮች መውጫ መንገዱ ምንድነው?

እነዚህ እና መሰል ወሳኝና አንገብጋቢ ነጥቦች ተዳሰውበታል

በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

በዕለተ ቅዳሜ ,በቀን 26/09/2015 EC ከመግሪብ በኃላ።

በላፍቶ ቢላል መስጂድ የተደረገ ልዩ ሙሀደራ

ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ
6.5K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 22:03:32 በገጠመን ፈተና ላይ ሌላ ችግር የምትፈጥሩልን ሰዎች እባካችሁ ታቀቡልን!
-----------------
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሆይ! እየደረሰብን ያለው መከራ የሸገር ሲቲ የመስጂድ ፈረሳን ተከትሎ ፅንፍ የረገጠው ርህራሄ ቢሱ የብልፅግና አመራር በንፁሀን ላይ የከፈተው የ"ተኩሰህ ግደል" ዘመቻ መሆኑን በአይናችን እያየን ነው።
ይሁንና ይህን ፈተና አስታከው ችግሩ ከመጅሊስ የመጣ አስመስለው የቀድሞውን ስርአት አስናፋቂ እንባ አላቃሾችን እያየን ነው።

እነሆ አእምሮ ላለው ሁሉ ቆም ብሎ ራሱን ጠይቆ እንዲመልስ አንድ ጥያቄ እጠይቀዋለሁ:-

አፈሙዝ ደቅኖ እየገደለ ያለውን ስርአት የተጋፈጡት ሙፍቲ ቢሆኑ ምን ያመጣሉ??

ይህን ጥያቄ ቆም ብላችሁ አስባችሁ መልሱት!!

ችግሩ ከአመራር ስርአቱ እንጂ ከመጅሊሱ እንዳልሆነ እያየነው ያለው እውነታ ነው። መጅሊሱ ደግሞ ያለ ርህራሄ እየገደለ ያለውን ስርአት ተጨባጭ እያየ ህዝበ ሙስሊሙን "ተዘጋጅ፣ መስጂድህን ጠብቅ፣ ራስህን አስከብር..." ወዘተ የመሰለ ቀጭን ትእዛዝ ቢያስተላልፍ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት!!
እንኳን እንዲህ ብሎ ቀርቶ እንዲሁም እያየነው ነው።
ስለሆነም ጉዳዩን እንደ መጅሊስ አመራሮች ስናየው የእውነትም ግራ ቀኝ አይቶ መነጋገር ካለበት አካላት ጋር ተመካክሮና ተወያይቶ አስቦና ወስኖ ነው እንጂ መልክት ወደ ሙስሊሙ ማስተላለፍ ያለበት እንዲሁ በለው እንዲል የምትጠብቁ የዋሆች ጉዳዩ ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀው ከባለ ወታደሩ መንግስትና እስኪሪብቶና ወረቀት ከያዘ መጅሊስ መሀል ያለ ፍጥጫ መሆኑን ልብ ልትሉ ይገባል።

ከዚህ በመቀጠል ሌላው ወሳኙ ነጥብ ፈተና ሲመጣ ሙስሊም ከመቼውም የበለጠ ይተሳሰራል፣ አንድነቱን ይጠብቃል፣ ይናበባል። በዚህ አካሄዱ ነው ድል ማድረግ የሚችለው።

ስለሆነም አንድነቱን በሚያፍረከርክ ፅሁፎችና ጉዳዩን የእርስበርስ መጠላለፍ በሚያደርጉ የሚዲያ ስራዎች ላይ የተጠመዱ አካላትን ፈፅሞ ልንነቃባቸው ይገባል። የፈተና ሰአት ላይ እንገኛለንና እየመራ ካለው አመራር ጋር ጉዞን ወደፊት ማድረግ ብቻና ብቻ የሚያዋጣን ሰአት ላይ ነን!! በዚህ ሰአት "ሙፍቲዬ ናፈቁን" ጨዋታ በፈተናችን ላይ ሌላ አንድነትን የማጣት ፈተና ከመጨመር ውጪ ምን ይጠቅማል!!!

በፈተና ሰአት ተረጋግቶ ማሰብን ነው የኛ ነብይ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ያስተማሩት። ይህን ተግባራዊ ማድረግ ካልቻልን ድል እየራቀን ይመጣልና ቆም ብለን እናስብ!!!

ወሰላም!!!!!!!!!!

ኑርሁሴን ጋሹ
7.3K views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 22:03:30
በገጠመን ፈተና ላይ ሌላ ችግር የምትፈጥሩልን ሰዎች እባካችሁ ታቀቡልን!


ይነበብ
4.6K viewsedited  19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 16:40:59
ፈፅሞ ከሌላ አለም የመጡ የሚመስሉት ሱፍይ ነን ባዮች አመለካከታቸው ከስያሜያቸው አለመግጠሙ ስህተት ላይ ለመሆናቸው ግልፅ ማሳያ ነው!
----------------------

ሱፍይ ነን ይሉሀል! ቀጥሎ ከተሰዉፍ በሚፃረር መልኩ የስልጣን ሽሚያ ሲወዘውዛቸው ታያለህ!!

ተሰዉፍና ስልጣን እኮ ሀራምባና ቆቦ ናቸው¡¡

ስላሴን እየሰበከ አምላክ አንድ ነው እንደሚለው ነሷራ እርስ በርሱ የተጣረሰ አካሄድ ላይ ናቸው!!

በዚህ በፈተና ሰአት እንኳ ከሙስሊሙ መፍትሄ አምጪነትና ተቆርቋሪነት ይልቅ ለሙስሊሙ ሌላ ችግር ሆነው ነው የቀረቡት!!

ከና ስልጣን ከያዘ አመት ያልሞላውን መጅሊስ ያውም በስልጣኑ አመታት የሚፈራረቁ ችግሮች የገጠመውን መጅሊስ በረባ ባረባው ችግሮችን ሁሉ ወደመጅሊሱ እያላከኩ ዳግም ወንበር ላይ ቁብ ለማለት ይጋጋጣሉ!!

ኧረ እፈሩ በአላህ!! ባይሆን ሙስሊሙ የገጠመው ችግር ይታያችሁ!! ችግርን አብሮ መወጣት ካቃታችሁ ዝምታችሁም መልካም ነውኮ!!! ለምን ሌላ ችግር ትሆናላችሁ??

ሙፍቲንኮ 3 አመት ገዝተው አየናቸው!! ልክ ስልጣን የያዙ ሰሞን አገባባቸውን አሳምረው የኋላ ኋላ እንደ ብልፅግና "ከኔ በቀር ማን አባቱ" በማለት የመጅሊሱ መቋቋም ዋና ችግር ሆነው አረፉት!!

ይኸው ነው!!

እናም እባካችሁ የሙስሊሙ ችግር ይሰማችሁ ይመማችሁ!! እንጂ ለሙስሊሙ ችግርና እንቅፋት አትሁኑ!!

ኑርሁሴን ጋሹ!
5.2K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 14:54:41
የመስጂድ ፈረሳውም ሆነ የሙስሊም መገደል ሌላኛው አውዱ ወንጌል በሀይልና በስልጣን የመስበክ ውጤት ነው።
ማረጋገጫ ለፈለገ ይኸው የሀሰቱ ነብይ እዩ ጩፋ እንዲህ ሲል አስቀድሞ ነግሮሀል:-

"ከዚህ በኋላ የትኛውም ሀይማኖት ይጣሳል!
እያባበልን የምንሰብክበት ዘመን አልፏል!
በሀይልና በስልጣን እንሰብካለን!!"

ስለዚህ በጉልበት እየሰበኩን መሆኑ ነው!!
5.4K views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 11:48:03
በስደት እንኳ ወደ አውሮፓ ወደ ሰው ሀገር የገቡ አፍሪካውያን ህገወጥ አገባብ ከመግባታቸው ጋር ሰብአዊ መብታቸው ሳይጣስ የመኖር መብታቸው ሳይደፈር በማረፊያ ጣቢያዎች ምግብና መጠጥ እየሰጡ ህጋዊ እስከሚሆኑ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል!!!
----------------------

የመኖር መብት የየትኛውም መንግስት ስልጣን አይደለም። የመኖር መብትን በእጁ ያደረገ አንድ አላህ ብቻና ብቻ ነው። መንግስት የሰዎችን የመኖር መብት እንዲህ እንደቀልድ መቅጠፍ ከጀመረ ነውጥ ይሆናል!! ሰው መሞትን ይፈራል!! ነገር ግን መሞት የግድ እንደሆነ ያመነ ቀን ግን መሳሪያ አያስቆመውም።

የሰለጠኑት ሀገራት ዜጎቻቸው ላልሆኑ አፍሪካውያን እንኳ የመኖር መብታቸውን አክብረው ጠለላ ይሰጧቸዋል!!

በሀገራችን ደግሞ በሰላም ሰግዶ በመበተን ላይ የነበረን ሙስሊም አፈሙዝ ደቅነው እንደቀልድ ይቀጥፏቸዋል። የራሳቸው ዜጎች ላይ ይህን ያህል ጨክነውባቸዋል።

በትላንትናው እለት ፍፁም ለመግደል ታጥቀው የመጡት የመንግስት አካላት ሙስሊሙ በአንዋር መስጂድ በሰላም ሰግዶ በመበተን ላይ ሳለ ነበር ተኩስ የከፈቱበት!! ከዛም ለመግደል የፈለጉትን ቁጥር ያህል ሰው ገደሉ! ያሰሩትን አሰሩ።

በመሰረቱ ጥያቄውም የፍትህ ጥያቄ ነበር። ፍትህን ለጠየቀ ማህበረሰብ ምላሹ ሽጉጥ ሆኖ በቀጥታ አማኝ ላይ ተተኩሶ በገፍ ሲገደል ያየነው ያለፈ ስርአት የለም። ይህ ፍፁም ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት በዘመናችን እስካሁን ካየናቸው የጭካኔ እርምጃዎች የከፋው ነው።
5.3K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ