Get Mystery Box with random crypto!

☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA

የቴሌግራም ቻናል አርማ huda4eth — ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA
የቴሌግራም ቻናል አርማ huda4eth — ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA
የሰርጥ አድራሻ: @huda4eth
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.10K
የሰርጥ መግለጫ

☀ሁዳ መልቲሚዲያ - ‌🇭‌🇺‌🇩‌🇦 ‌🇲‌🇺‌🇱‌🇹‌🇮‌🇲‌🇪‌🇩‌🇮‌🇦 -قناة هدى الاسلامية
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ንፁህ ኢስላማዊ እውቀት ይደርሳቸው ዘንድ እንሰራለን!
ለአስተያየት @nuugaa

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-01 21:36:35
ሰለምቴው ቄስ አብረሃም ታሪክ በአማረኛ ትርጉም
-----------------
ደቡብ አፍሪካዊው ቄስ አብረሃም ከ3 ወራት በፊት እስልምናን ተቀሽሎ በቤተክርስቲያኑ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮቹን በሙሉ አስልሞ ሲያበቃ አላህ ደግሞ ሀጅ እንዲያደርግ ወፍቆት የሀጅ ስነስርአትን አጠናቋል!

ሙሉ ታሪኩን ከማረኛ ትርጉም ጋር የናነተው ሁዳ መልቲሚዲያ / Huda Multimedia ይዞላችሁ ቀርቧል!

ለሌሎች ይደርስ ዘንድ ሼር በማድረግ ሀላፊነትዎን ይወጡ!









4.3K views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 21:36:08 ሰለምቴው ቄስ አብረሃም ታሪክ በአማረኛ ትርጉም
-----------------
ደቡብ አፍሪካዊው ቄስ አብረሃም ከ3 ወራት በፊት እስልምናን ተቀሽሎ በቤተክርስቲያኑ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮቹን በሙሉ አስልሞ ሲያበቃ አላህ ደግሞ ሀጅ እንዲያደርግ ወፍቆት የሀጅ ስነስርአትን አጠናቋል!

ሙሉ ታሪኩን ከማረኛ ትርጉም ጋር የናነተው ሁዳ መልቲሚዲያ / Huda Multimedia ይዞላችሁ ቀርቧል!

ለሌሎች ይደርስ ዘንድ ሼር በማድረግ ሀላፊነትዎን ይወጡ!



4.1K views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 12:31:29
"የተቀበሩ ሙታን እርዱን ድረሱልን ብንላቸው ይሰሙናል! አላህ ዘንድም ያማልዱናል"

የሱፍያ ማምታቻ

ወዳጆቼ ከአላህ ውጪ ያለን የሞተ አካል ወደ አላህ እንዲያቃርብ መለመን ከኢስላም መልክት ጋር የሚጣረስ እንጂ የኢስላም አይደለም።

አላህ ነብያትን ሁሉ የላከው እርሱን በብቸኝነት እንድንለምን እንጂ ሙታን ላይ ልባችንን እንድናንጠለጥል አይደለም። እነዚህን ከአላህ አዘናጊዎች ተጠንቀቁዋቸው!!

"እነዚያ ከአላህ ውጪ የሚለምኗቸው ምንም መፍጠር የማይችሉ ፍጡራን ናቸው። በህይወት የሌሉ ሙታን ናቸው። መቼ እንደሚቀሰቀሱ እንኳ አያውቁም።" (ቁርአን ሱረቱ ነህል 17)

"አዋጅ ጥርት ያለው ዲን ለአላህ ነው! እነዚያ ከአላህ ውጪ አውሊያእ (ወዳጆችን) የያዙ ሰዎች "እኛኮ ወደ አላህ እንዲያቃርቡን እንጂ እያመለክናቸው አይደለም!" ይላሉ። አላህ ሲለያዩበት በነበረው ነገር ይፈርዳል! አላህ ውሸታምን እና ከሀዲን ወደ ቅናቻው አይመራም"
(ሱረቱ ዙመር 3)
4.4K viewsedited  09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 11:28:27
 ስታርድ እዝነት ይኑርህ

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِنَّ اللَّهَ كَتَبَ الْإِحْسَانَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ، فَإِذَا قَتَلْتُمْ فَأَحْسِنُوا الْقِتْلَةَ، وَإِذَا ذَبَحْتُمْ فَأَحْسِنُوا الذَّبْحَ، وَلْيُحِدَّ أَحَدُكُمْ شَفْرَتَهُ فَلْيُرِحْ ذَبِيحَتَهُ﴾

“አላህ ኢኽሳንን (ማሳመርን) በሁሉም ነገሮች ላይ ፅፏል። የገደላችሁ እንደሆነ አገዳደልን አሳምሩ። አንዳችሁ ባረደ ግዜ አስተራረዱን ያሳምር ማረጃውን ይሳል። የሚታረደውንም እንስሳም ያሳርፍ።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 1955

በሌላ ሀዲስ፦

﴿جاءَ رجلٌ إلى رسول الله ﷺ فقـال: يـا
رسـول الله إني لأذبحُ الشّـاةَ وأنـا أرحمها،
فقال ﷺ : والشاةُ إن رحِمتَها رحِمَك الله﴾

“አንድ ሰው ወደ አላህ መልዕክተኛ (ﷺ) በመምጣት እንዲህ አላቸው፦ ‘እኔ በጌን አርጄ ለሷም እዝነትን አድርጌ ነበር’ ረሱል (ﷺ) አሉት፦ ‘ለሷ ለበግህ እዝነትን እንዳደረክ አላህ ለአንተም ይዘንልህ።’”

ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 1081

@BuhariMuslimAmharic

#ሼር_አርጉ
⊱⊰━━━━━━━⊱⊰━━━━━━━⊱⊰
@mehlitube
لبيك اللهم لبيك .. لبيك لا شريك لك لبيك .. إن الحمد والنعمة لك والملك لا شريك لك
عيد مبارك تقب الله منا ومنكم  صالح الأعمال
ኑር ሚድያ ብርሀናዊ 20ት
https://t.me/Mahfuzmuhdin

ካመት አመት በደስታ እንገናኝ
t.me/huda4eth
5.7K viewsedited  08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 11:27:55
4.3K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 17:02:49                  

عيدكم مبارك

Eid Mubarak

ዒድ ሙባረክ

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال

ከእኛም ከእናንተም አሏህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን

"ليس العيد لمن لبس جديد
إنما العيد لمن نجا يوم الوعيد"

  ዒድ እኮ አይደለም አዲስ ለለበሰው
ዒድማ ለዛ ነው ከዛቻው ቀን ለተረፈው
           •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
محبكم:  عزالدين إلياس خضر

           •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
       
5.5K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 14:15:50
ከግዚያት በኋላ ብእሬን አነሳው ፣
የውስጤን ቃጠሎ ድንገት ቢያበርደው ፣

በጀማል ሁሴን

#ሰጋጁን_ገደሉት
#ሙስሊምጠልነት
#ኢስላምጠልነት
#Islamophobia
#EthiopianMuslimsUnderAttack
#share
3.4K views11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 07:54:31 መረጃዎችን እንሰብስብ፣እናደረጅ!!!

የሸገር ከተማ አስተዳደር/የኦሮሚያ ክልል መንግስት የፈፀማቸው መስጂዶችን የማፍረስ ዘመቻ የፈጠራቸው ችግሮች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከባድ ዋጋ እያስከፈሉን ይገኛሉ።የሚመለከተው የመንግስት አካልም የሸገር ከተማ አስተዳደር/የኦሮሚያ ክልል መንግስት ህዝበ ሙስሊሙን እና ተቋሙን በመናቅ እየፈጠረ ያለውን ሀገራዊ ቀውስ ትኩረት ሰጥቶ ለማስቆም አልቻለም።በቀጣይ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት አስቸኳይ መፍትሄ ያስፈልጋል።
በሸገር ከተማ አስተዳደር ግብታዊ እርምጃ በዘመቻ የፈረሱ መስጂዶችን የሚያሳዩ መረጃዎች እና ማስረጃዎች በአብዛኛው ተሰናድተዋል።የቀሩትም በመሰናደት ላይ ይገኛሉ።
-----
በሁለቱ ጁምዐዎች በአዲስ አበባ ከተማ በአንዋር እና በበኒ ኑር መስጂድ የሆነውን በትክልል ሊያስረዱ የሚችሉ:-የምስል፣የድምፅ እና የድምፅ ከምስል ማስረጃዎች ሌላ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ድምፅ ሳይጨመርባቸው መሰብሰብ፣ማደረጃት እና መሰነድ ያስፈልጋል።ይህ ስራ ኮሚቴው እየሰራ ላለው ስራ ግብአት ይሆናል።
**
በተለይ በሁለቱ ጁምዐዎች (ግንቦት 18/2015 እና ግንቦት 25/2015) በፀጥታ አካላት በተተኮሱ ጥይቶች ተመተው የሞቱ ምእመናን እና ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በሚመለከት በአዲስ አበባ ፖሊስ በኩል (ለህዝብ ይፋ እንደተደረገው ሁሉ) የሚሰራው የማጣራት እና የምርመራ ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚቴውም ይህን ጉዳይ የመከታተል እና የሆነውን የማጣራት ለህዝብ ሙስሊሙ ብሎም ኃላፊነቱን ላሸከመው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጠቅላላ ጉባኤ ይፋ የማድረግ ኃላፊነት ስለተጣለበት ሁሉም በቻለው አቅም በእጁ ያሉትን መረጃዎች በመጠበቅና ከላይ በተጠቀሰው አግባብ ለኮሚቴው በማዘጋጀት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት ያስፈልጋል።
**
"የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው" የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በኡማ ሆቴል በተካሄደ የአንደኛ አመት አስቸኳይ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ የተሰየመና ከሸገር ከተማ መስጂዶችን የማፍረስ ዘመቻና ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሐገራችን ክፍሎች "መስጂዶቻችንን አታፍርሱ!!!" በማለት ድምፁን በሰላማዊ መንገድ ለማሰማት በወጣ ምእመን ላይ የተወሰደው ኢ-ሰብአዊና ኢህገ-መንግስታዊ የሆነ የግድያና የደረሱ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳትን የማጣራት፣መረጃና ማስረጃን መሰረት በማድረግ ህግና ስርአት እንዲከበር፣ ተጠያቂነትም እንዲሰፍን የማድረግ እና ለችግሮቹ መነሻ ለሆኑ ጉዳዮችም አፋጣኝ የጋራ መፍትሄ ለማበጀት የተቋቋመ ኮሚቴ ነው።
**
በመሆኑም ማንኛው ከላይ ከተጠቀሱ መሰረታዊ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ያላቸው መረጃና ማስረጃዎች በእጁ ያለ አካል መረጃዎቹን በሚመቸው መልኩ ለኮሚቴዎቹ እንዲያደርስ እየጠየኩ ኮሚቴው መረጃዎቹን የማሰባሰብ፣የማደረጀት፣ የመሰነድ እና የህግ ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚጠቀም ይሆናልና መረጃዎቻችንን አወንሰብስብ፣ እናደረጅ!!!

Mohammed Abate
3.9K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-05 07:22:49
ፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን በዋሺንግተን ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ
----------------------
ዋሺንግተን ዲሲ ከኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊትለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ የፊትለፊታችን ጁሙዓ ጠራ!

የመስጂዶቻችን መፍረስ ሳያንስ ለመስጂዶቻችን ድምፅ ለመሆን የወጣውን ሙስሊም ያለ አንዳች ርህራሄ ወደ ፊትለፊቱ በመተኮስ መግደል የጀመረው ገዢው ፓርቲ መስጂድን አፍርሶና ሙስሊሙን ገድሎ መረጋጋትን የሚጠብቅ መስሎት ከነበረ በእርግጥ መሳሳቱን የሚያሳዩ ጅምሮችን ከሀገር ውጪ ያሉ ዳያስፖራዎችም እነሆ ጀመሩት!!!

በሰላማዊ መንገድ ድምፅንና በደልን የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው እነሆ ድምፅ ሊሆኑን በዋሺንግተን ዲሲ ጁሙዓ ኢትዮጵያ ኢንባሲ ፊትለፊት በፈርስት ሂጅራ ሰብሳቢነት ይሰየማሉ!!!

ምናልባት ብልጥ የሆነ አመራር ካለ ነገሩን ከወዲሁ መስመር ለማስያዝ ጊዜው አለመርፈዱን አክለን ለማስታወስ እንወዳለን
3.8K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 19:08:11
እኔ አንተ አንቺ ምን አለን?
ለ16 አመት ልጅ ጥይት
ይህን ያረጋችሁ ሁሉ ከቤታችሁ ሀዘን አይጥፊ በዱንያም በአኼራ በጭቅ ላይ ጭቅ ይፈራረቅባችሁ

ኑር ሚድያ ብርሀናዊ 20ት
4.5K viewsedited  16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ