Get Mystery Box with random crypto!

ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ guramaylebooks — ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ guramaylebooks — ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @guramaylebooks
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.57K
የሰርጥ መግለጫ

ምንም አይነት መፅሀፍ ይዘዙን ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናመጣሎታለን፡
በሚያስገርም "ከ10-50%" በሆነ የዋጋ ቅናሽ ሞክረው ይዩን በአገልግሎታችን ይደሰታሉ
Free delivery
@Guramaylebooks
@Guramayelie 0912319263

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-07-27 12:06:45
ድሬ !!!
4.2K viewsedited  09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 17:58:05
የኢትዮጵያ ታሪክ ከዓፄ ይኹኖ አምላክ እስከ ዓፄ ሱስንዮስ ከ1270 - 1632 ዓ.ም

ይህ መጽሐፍ የመካከለኛውን ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ በጥሩ አተያይ የሚያትት አዲስ መጽሐፍ ሲኾን የሰለሞናዊውን ሥርወ መንግሥት ከአነሳሱ እስከ ውድቀቱ እና በወይ ባህር ክልል የነበረውን የሙስሊሙንና የአውሮፓውያንን ፉክክር የሚዳስስ በእስታኤላዊው ፕሮፌሰር ሞርድኃይ አቢር የተፃፈ ሲሆን በበሳል የአተረጓጎም ብቃት በማውሮ አዛሪዮስ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል።

መጽሐፉ አስቸጋሪውንና ውስብስቡን የመካከለኛውን ዘመን የሚተነትንንና የዘመኑን የታሪክ ክፍተት የሚሞላ እንዲሁም የእስልምና ኃይሎች መነሳትን የኦሮሞን መስፋፋት ፣ የሰለሞናዊው መንግስት የውድቀት ምክንያቶች፣ በቀይ ባህር ዳርቻ የነበሩት የትግራይ ሹማምንቶች የአውሮፓውያንን ሽርክና በተጓዥነት ስም የሚመጡ አውሮፓውያን ስውር ፍላጎት ጭምር ተተንትኖበታል።


የኢትዮጵያ ታሪክ ከዓፄ ይኹኖ አምላክ እስከ ዓፄ ሱስንዮስ ከ1270 - 1632 ዓ.ም ተርጓሚ ማውሮ አዛሪዮስ
የገፅ ብዛት - 314 የተለጠፈበት ዋጋ - 380 ብር
መሸጫ ዋጋ - 250 ብር >= 3 Free delivery
Contact us @Guramayelie 0912319263
1.4K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 10:07:14
ሚካኤል አስጨናቂ የጻፋቸውን ወጎችና አጫጭር ታሪኮች ለኅትመት ከመብቃታቸው አስቀድሞ አነባቸው ዘንድ ያቀረበውን ግብዣ በአክብሮት ተቀብዬ ተመልክቻቸው ነበር።
ምስክር ለመቆም በቂ ይመስሉኛል።
እጅግ መልካም የሆነ የማስታወስና የመተረክ ብቃት ያለው ማዕከላዊ ጸሐፊ (ደራሲ) ሆኖ አግኝቼዋለሁ መጽሐፉን የሚያነቡም ቢያተርፉ እንጂ እንደማይከስሩ ስምዐ - ጽድቄን አስቀምጫለሁ።
በእርግጠኝነት ተወዳጅ መጽሐፍ ለመሆን የሚቻለው ሥራ ነው። "ሸግዬ ሸጊቱ" !።!
ገጣሚ፣ ደራሲ እና ባለቅኔ ኤፍሬም ሥዩም ስለመጽሐፉ የሰጠው አስተያየት።


ሸግዬ ሸጊቱ ሚካኤል አስጨናቂ
የገፅ ብዛት - 292 የተለጠፈበት ዋጋ - 350 ብር
መሸጫ ዋጋ - 260 ብር >= 3 Free delivery
Contact us @Guramayelie 0912319263
2.0K views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 10:46:09
ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የኢድ-አል አድሃ በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን ።
2.1K views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 07:28:38
"ጎሹ አረጀና ልቡ ቢዘናጋ
ጉራምባ ወረደ አንበሳን ሊወጋ
ጎሹ እስከነልጁ ጉራምባ ላይ ወርዶ
ያንበሳውን ፊት ቢያይ ወደቀ ተዋርዶ።"

ደጃዝማች ካሳ ኃይሉ ‹‹ዳግማዊ ቴዎድሮስ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› ተብለው ከመንገሳቸው በፊት ከግዛት ባላባቶች ጋር ካደረጓቸው ታላላቅ ጦርነቶች መካከል አንዱ የነበረው ኅዳር 19 ቀን 1845 ዓ.ም ጉር አምባ ላይ የተካሄደውን የጉራምባ ጦርነት ላይ ደጃዝማች ጎሹ ዘውዱን ከሸነፉ በኋላ የተገጠመላቸው ግጥም ነው።
ደጃዝማች ጎሹ ዘውዴ የራስ ኃይሉ ዮሴዴቅ የልጅ ልጅ (የወይዘሮ ድንቅነሽ ኃይሉ ልጅ) እንዲሁም የዳሞቱ ባላባት የደጃዝማች ዘውዴ ልጅ ናቸው፡፡ ልጃቸው ደጃዝማች ብሩ ጎሹ ከአባቱ ጋር ሆኖ ጉር አምባ ላይ ከደጃዝማች ካሣ ጋር እየተዋጋ ሳለ፣ አባቱ ደጃዝማች ጎሹ መመታታቸውን ሲያይ ሸሽቶ ዳሞት ገብቶ ነበር፡፡ በኋላም ተይዞ ድንጋይ ተሸክሞ ደጃዝማች ካሣን ምህረት ጠይቋል፡፡ ከመጽሐፉ የተወሰደ።


ዐፄ ቴዎድሮስ እና የኢትዮጵያ አንድነት
ከተክለ ጻድቅ መኲሪያ
የገፅ ብዛት - 514 የተለጠፈበት ዋጋ - 456 ብር
መሸጫ ዋጋ - 390 ብር >= 3 Free delivery
Contact us @Guramayelie 0912319263
2.1K viewsedited  04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 22:32:43
ሙሉ በሙሉ እውነተኛ ታሪክ
የሞት ፍርድ የተፈረደባት አንዲት እንስት ይቅርታ ጠይቂና የሞት ፍርዱ ይነሳልሽ ብትባል እንቢ አሻፈረኝ ትላለች፡፡
ምሕረትን እንዳትቀበል ያደረጋት፣ ሕይወቷን ያስመረረውና የሞት ጽዋውን ያሰኛት ምክንያት ምን ይሆን?
ከእስር ቤት የምትወጪበት አንድ ተስፋ ተገኝቷል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ የይቅርታ መልዕክት ፅፈሽ ይቅርታ እንዲደረግልሽና ሁለተኛ ወንጀል ላለመስራት ቃል የምትገቢ ከሆነ ከእስር ቤት እንደምትወጪ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡”
“ይቅርታ እኔ ነፃ መሆን አልፈልግም፡፡ ለሰራሁት ወንጀል ደግሞ ይቅርታ መጠየቅ አልፈልግም፡፡ በዚያ ላይ እናንተ ወንጀል ብላችሁ የምትጠሩት ወንጀል አይደለም” አልኩት፡፡ “ከዚህ ወጥቼ አንተ እንደምትለው እንደገና መኖር ብጀምር መግደሌን አላቆምም፡፡ ስለዚህ የይቅርታ ደብዳቤ ለፕሬዚዳንቱ መላክ አያስፈልግም፡፡ እኔ በመኖርም፣ በመሞት… በሁለቱም አሸናፊ ነኝ፡፡”


ማራ ትርጉም መላኩ ዓለም
የገፅ ብዛት - 206 የተለጠፈበት ዋጋ - 250 ብር
መሸጫ ዋጋ - 170 ብር >= 3 Free delivery
Contact us @Guramayelie 0912319263
2.4K views19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:55:40
ስለሃገሩ ተናግሮ አይጠግብም ሃገር በቀል እውቀቶች ላይ ብዙ ለፍቷል ኢትዮጵያዊነት በደምስሩ ውስጥ ገብቷል። ይጠቅማል ያላቸውን እውቀቶች፣ኢትዮጵያዊ ፍልስፍናዎች ሳይደክም ለትውልዱ ዘርቷል አሁንም እየዘራ ይገኛል።በሃይማኖቱ ድርድር አያውቅም ሃሰተኞችና አላዋቂዎችን ይሞግታል ።ዘረኞች እጅግ አብዝተው ይጠሉታል ። ኢትዮጵያዊነት ላይ ያጠነጠኑ በዙ አጫጭር ስልጠናዎችን ሰጥቷል።ላመነበት ጉዳይ ወደ ኋላ አያውቅም።
መምህር ፋንታሁን ዋቄ ።
አሁን ላይ ያየውን የምእራቡን እሳቤ ከተለያዩ እይታ አንጻር አይቶ በመጽሐፍ መልክ ይዞልን ብቅ ብሏል ።
"ሥዝም ሰብዊነት /secular humanism / የልማታዊ ወንጀሎች ምንጭ" ።
ይህ መጽሐፍ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቢያነበው ያተርፍበታል። ተጽሐፈ ዲበኩሉ።


ሥዝም ሰብአዊነት ፋንታሁን ዋቄ
የገፅ ብዛት - 471 የተለጠፈበት ዋጋ - 390 ብር
መሸጫ ዋጋ - 340 ብር >= 3 Free delivery
Contact us @Guramayelie 0912319263
2.6K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:35:15
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ከኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነጥሎ ማየት ይከብዳል፡፡ ቤተክስርቲያኒቱ ለኢትዮጵያ ህልውና ዋጋ ብትከፍልም ለውለታዋ ጥርስ እንዲነከስባት ሆናለች፡፡
ለመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክስርቲያን በምን ምክንያት ጥርስ ተነከሰባት? ውለታዋና በደሏስ ምንድነው?
እስልምና፣ ወንጌላውያን እና ካቶሊክ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጋር የነበራቸው ሙግት በአስደናቂ ሁኔታ በመጽሐፉ ውስጥ ተዳስሷል፡፡ በሙግቱ ማን ረትቶ ይሆን?
ላሊበላ ሶስት ቀናት ሞቶ የተገለጠለት አስገራሚ ሚስጥርም ተካትቶበታል፡፡ ብዙም ያልተነገረለት ላሊበላ ሞቶ የተገለጠለት ምስጢር ምን ይሆን?
ታቦተ ፂዮንን በአይናቸው ያዩት አጼ ኢያሱን ጨምሮ የጥቂት ሰዎች ምስክርነት በሚገርም ሁኔታ በመጽሐፉ ላይ ሰፍሯል፡፡ ታቦተ ፂዮንን በአይናቸው ያዩ ሰዎች ምን ተናረው ይሆን?
ኦርቶጵያ መጽሐፍ የሚነግረን ብዙ አስገራሚ ታሪኮች አሉ፡፡


ኦርቶጵያ ትርጉም ራሴላስ ጋሻነህ
የገፅ ብዛት - 352 የተለጠፈበት ዋጋ - 350 ብር
መሸጫ ዋጋ - 220 ብር >= 3 Free delivery
Contact us @Guramayelie 0912319263
2.7K views04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 19:26:24
3.5K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 19:23:25
መጽሐፉ የተተረጎመው በ1970ዎቹ ውስጥ ሲሆን፣ ተርጓሚው ማዕከላዊ ምርመራ ድርጅት እሥር ቤት ውስጥ ታሥሮ ሳለ የተረጎመው ነው። በዚያን ዘመን ወደዚያ እሥር ቤት ምንም ወረቀት የማይገባ ስለሆነ፣ ያለው አማራጭ በሲጋራ ወረቀቶች ላይ መተርጎም ብቻ ነበር! ልዩ የሚያደርገው ይሄ ነው። በአፃፃፉ ረገድ፣ ቃል በቃልም በአዛምዱ ትርጉምም በአንድምታ - ትርጓሜም የተቀነበበ በመሆኑ፣ አንባቢ በቀላሉ እንደሚረዳውና እንደሚረካበት እምነታችን ፅኑ ነው።
የተርጓሚ ነብይ መኮንን የእሥር ቤት ወዳጁ ስለመጽሐፉ የሰጠው አስተያየት።
Gone with the wind (ነገም ሌላ ቀን ነው) ከብዙ አመታት በፊት በነብይ መኮንን ተተርጉሞ ለንባብ የበቃ ምርጥ ረጂም ልብወለድ ነው።


ነገም ሌላ ቀን ነው ትርጉም ነብይ መኮንን
የገፅ ብዛት - 507 የተለጠፈበት ዋጋ - 350 ብር
መሸጫ ዋጋ - 300 ብር >= 3 Free delivery
Contact us @Guramayelie 0912319263
3.2K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ