Get Mystery Box with random crypto!

ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ guramaylebooks — ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ guramaylebooks — ጉራማይሌ Delivery 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @guramaylebooks
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.57K
የሰርጥ መግለጫ

ምንም አይነት መፅሀፍ ይዘዙን ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ እናመጣሎታለን፡
በሚያስገርም "ከ10-50%" በሆነ የዋጋ ቅናሽ ሞክረው ይዩን በአገልግሎታችን ይደሰታሉ
Free delivery
@Guramaylebooks
@Guramayelie 0912319263

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-08-14 15:15:41
3.5K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 15:15:05
Can't hurt me - David Goggins

ለዴቪድ ጎጊንስ ልጅነት ቅዠት ነበር -- ድህነት፣ ጭፍን ጥላቻ እና አካላዊ ጥቃት ቀኖቹን ቀለም ቀይረው ሌሊቱን አስጨናቂ ነበር። ነገር ግን እራስን በመግዛት፣ በአእምሮ ጥንካሬ እና በትጋት በመስራት ጎጊንስ ራሱን ከጭንቀት ከተጨነቀ እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት ካለው ወጣት ወደፊት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሃይሎች ተምሳሌትነት እና ከአለም ከፍተኛ የጽናት አትሌቶች ተርታ ተቀየረ። እንደ Navy SEAL፣ Army Ranger እና Air Force Tactical Air Controller በታሪክ ውስጥ የላቀ ስልጠናን የጨረሰ ብቸኛው ሰው በተለያዩ የጽናት ዝግጅቶች ላይ መዝገቦችን በማስመዝገብ የውጪ መፅሄቶችን በማነሳሳት ስሙን በአሜሪካ ውስጥ በጣም ጥሩ (እውነተኛ) ሰው ብሎ እንዲሰይመው አድርጓል

አልችልም በሚለው ውስጥ፣ አስደናቂ የህይወት ታሪኩን ያካፍላል እና አብዛኞቻችን 40% አቅማችንን ብቻ እንደምንጠቀም ገልጿል። ጎጊንስ ይህንን የ 40% ህግ ብሎ ይጠራዋል እና የእሱ ታሪክ ማንኛውም ሰው ህመምን ለመግፋት ፣ ፍርሃትን ለማጥፋት እና ሙሉ አቅሙን ለመድረስ የሚፈልገውን መንገድ ያበራል...
3.4K viewsedited  12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 19:25:27
+ + + ጽዋዔ በመምህር ያረጋል አበጋዝ ምልከታ + + +
ታላቁ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ አንጾኪያ በነበረበት ወቅት የአደረጋቸው ነገሮችና የአስተማራቸው ትምህርቶች ቤተ ክርስቲያን እና ሀገር በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ሕዝብን እንዴት ማገልገልና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ማሻገር እንደሚቻል በተግባር ያስተምሩናል፡፡
ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ሰፊ ጥናትና ዳሰሳ በማድረግ የአዘጋጀው ይኽ መጽሐፍ፤ በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የአንጾኪያ የተጋድሎ ሕይወት አንጻር ካህናት ሕዝባቸውን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት መምራትና ማሻገር እንደሚገባቸው ያሳየናል፡፡ ተግባራዊ ትምህርት የሚሰጥ የሆነውን ይህን መጽሐፍ በመጻፉም ሊመሰገን ይገባዋል፡፡
መምህር ያረጋል አበጋዝ
ጸሐፊና ሰባኬ ወንጌል


ጽዋዔ ዲያቆን ታደሰ ወርቁ
የገፅ ብዛት - 440 የተለጠፈበት ዋጋ - 385 ብር
መሸጫ ዋጋ - 330 ብር >= 3 Free delivery
Contact us
@Guramayelie 0912319263
4.7K viewsedited  16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 22:34:59
6.0K views19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 21:28:49
የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ አራት አዳዲስ መጽሐፍት በአንድ ላይ የታተሙበት!

የደስታ ቀናት እንደ ሰማይ ሲርቁ…
ክፉ ቀናት እንደ አጀብ ሲከቡን…
ሞት አንድ አማራጭ ሆኖ ሲቀርብ…
ውስጣዊ ሰላማችን ሲረበሽ…
እርጋታ ፈጽሞ ሲጠፋ….

…ያን ጊዜ “ጌታ ሆይ እስከመቼ?” እንላለን፡፡ ደግሞም በልጅነት ሰቆቃ በአባቶቻችን አንደበት
#እስከማዕዜኑ? እንላለን፡፡

“እንደ ልጄ እንደ ዳዊት ቀና ሁን፣ እንደ ታላቁ ታጋሽ እንደ ኢዮብ ሁንልኝ፣ የቀጠርኩልህ ቀን ሲደርስ የመከራህን ቀናት አስረሳሃለሁ! እንደ ተወዳጁ ልጄ እንደ ወልድ ትንሳኤህ እስኪገለጥ እርጋታን ገንዘብህ አድርግ!” ይለናል፡፡ በቃሉ ያባብለናል፡፡

የህማማት ቀናቶቻችን እንደ ግዮን ወንዝ የረዘሙ ሲመስሉ፣ የህዝባችን እፎይታ፣ የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት እንደ ጌታችን መምጫ ቀን ሲርቁብን፣ ህይወት ከንቱ መኖርም ምናምንቴ መስሎ ሲታይ… የስጋ ድካም ከዘለዓለማዊው እጣ ፈንታችን ሊያናጥበን ሲል… ያን ጊዜ የታላላቅ አባቶች ምክር፣ የቅዱሳን ጥበብ፣ የታጋሾች ምስክርነት ያስፈልገናል፡፡

የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ አራት መጽሐፍት በአንድ ላይ
#እስከማዕዜኑ በሚል ርእስ የተዘጋጁትም ለዚሁ ዓላማ ነው፡፡

በሕይወታችን ያሉ እስከመቼ የምንልባቸውን መከራዎች እንዴት እንደምንወጣቸው የሚያስተምር ድንቅ መጽሐፍ ነው-
#እስከማዕዜኑ!

እስከማዕዜኑ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
የገፅ ብዛት - 304 የተለጠፈበት ዋጋ - 254 ብር
መሸጫ ዋጋ - 230 ብር >= 3 Free delivery
Contact us
@Guramayelie 0912319263
5.6K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 21:28:32
... አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
"መንፈሳችንን ነፃ ስለ ማውጣት"

በአንተ ውስጥ መልካም ነገርን ብታገኝ እንኳ በዚህ ነገር አትታበይ ወይንም አትመካ።

በራስህ ጽድቅ ራስህን አትዋጋ፤ ነገር ግን ክብርህን ሁሉ ለእግዚአብሔር ስጥ። ለእናንተ የሚገባው ለእርሱ አይደለም፤ እርሱ ቸር ነውና መልካሙን ሁሉ ፈጣሪ እንደኾነ ደግ ነገር በእርሱ ነውና። እሱ እራሱ ጥሩ ነው። ስለሆነም ጥሩነት በራሱ ያለ እርሱ ምንም ማድርግ አይችልም። ስለዚህ የእግዚአብሔርን ክብር ዘርፈህ ለራስህ አትስጠው። እርግጥ ነው፤ ልክ እንደ ጨረቃ ልታበሩ ብትችሉ እና ሙሉ ጨረቃ እስክትሆኑ ድረስ ብርሀናችሁ ቢጨምርም፣ በነገሩችሁ ሁሉ ውስጥ ጨረቃ ብርሀኗን ከፀሐይ የምታገኝ (የፀሐይን ብርሀን የምታንፀባርቅ) የራሷ የብርሀን ምንጭ የሌላት ግዑዝ መሆኗን ልብ አድርግ። ስለዚህ ፀሐይ ከሌሎች ጨረቃ በባህሪዋ ጨለማ ስለሆነች ልናያት ሁሉ አንችልም። አሁን ጨረቃ በፀሐይ ፊት ስለብርሀኗ ለመናገር ትደፍራለችን?!


መንፈሳችንን ነጻ ስለማውጣት
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
የገፅ ብዛት - 166 የተለጠፈበት ዋጋ - 250 ብር
መሸጫ ዋጋ - 190 ብር >= 3 Free delivery
Contact us
@Guramayelie 0912319263
3.7K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 23:45:09
ንግግር ለመጀመር አትጣደፍ። ጥድፊያ መሸበርንና ሁኔታዎችን መቆጣጠር አለመቻልን ያሳያል።
ድሉ ያለው ፍርሀት አልባ በሆነው የአእምሮ መዋቅር ውስጥ ነው። ፕሮፌሰር ዎልተር ዲል ስኮት "በቢዝነስ ውስጥ ስኬት እና ውድቀት የሚመጣው ከአእምሯዊ አቅም ይልቅ በአእምሯዊ አመለካከት ነው" ሲል ይናገራል። የፍርሃት አመለካከትን አስወግዱ። እናም ይህንን ከፍርሃት የነጻ አመለካከት ማግኛ ብቸኛው መንገድ ደግሞ አመለካከቱን ማግኘት ብቻ እንደሆነ አስታውሱ።
በእርጋታ ከልብ ተንፍሱ ፤ ንግግራችሁን ልክ ለአንድ ትልቅ ጓደኛችሁ እያወራችሁ እንደሆናችሁ በተረጋጋ የወግ ድምጽ ጀምሩ። ንግግራችሁንም እንደፈራችሁት መጥፎ ሆኖ አታገኙትም። ይህ ልክ ውሃ ውስጥ ጠልቆ እንደመግባት ዓይነት ነገር ነው። ውሃው ውስጥ ጠልቃችሁ ከገባችሁ በኋላ ውሃው ይረጋጋል። ስለ እውነቱ ከሆነም ለጥቂት ጊዜ ንግግሮችን ካደረጋችሁ በኋላ የውሃ ጠለቃውን በደስታ የምትጠብቁ ይሆናል። ከታዳሚው ፊት ቆማችሁ ታዳሚውን ሃሳቦቻችሁ ደስታን የሚያጭሩላችሁ መሆኑን ታዳሚው ያስብ ዘንዳ ታደርጋላችሁ።


የንግግር ጥበብ. ዴል ካርኔጊ
የገፅ ብዛት - 212 የተለጠፈበት ዋጋ - 250 ብር
መሸጫ ዋጋ - 190 ብር >= 3 Free delivery
Contact us
@Guramayelie 0912319263
4.0K views20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 23:44:56
ሄኖክ ስዩም በሀገራችን ጉዞና ጉብኝት የቱሪዝም ዘርፍ የተሰማራ ጋዜጠኛ ነው። ተጓዡ ጋዜጠኛ በሚል ቅፅል ስሙ ይታወቃል።
የጉዞ ማስታወሻዎችንም በመጻፍ ለሕትመት አብቅቷል ፤ ከዚህ ቀደም "የመንገድ በረከት" ፣ "ጎንደርን ፍለጋ" እና "ሀገሬን" የተባሉ ሦስት መጻሕፍትን ለተደራሲያን አቀቧል። "ደቦ" እና "አቦል" በተሰኙ የጋራ ስብስብ ስራዎችም የጉዞ ማስታወሻ ሥራዎቹን አሳትሟል። ይህ "ወደ ኢትዮጵያ ሰዎች" የተባለ ስራው ለሀገሩ ሰው የላካቸውን መልእክቶች የያዘ አዲስ አቀራረብ ነው።


ወደ ኢትዮጵያ ሰዎች
ሄኖክ ስዩም (ተጓዡ ጋዜጠኛ)
የገፅ ብዛት - 186 የተለጠፈበት ዋጋ - 250 ብር
መሸጫ ዋጋ - 190 ብር >= 3 Free delivery
Contact us
@Guramayelie 0912319263
3.8K views20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 13:12:38 "ኢትዮጵያዊነት"
ከአንዷለም ቡኬቶ የማህበራዊ ገጽ የተወሰደ።
በዚህ አስከፊ ጊዜ የሀገራችንን ስም በጥሩ ላስነሱ አትሌቶቻችን ክብር ይገባቸዋል።
እንኳን በሰላም ለሀገራችሁ አበቃችሁ።
5.0K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 15:41:54
ይህ መጽሐፍ የታላቁ ንጉሰ ነገስት የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ እና የኢትዮጵያን ታሪክ የያዘ ትልቅ ቅርስ ነው። መጽሐፉ በውስጡ የያዛቸው እጅግ በርካታ የኢትዮጵያ ታሪክ ውጣ ውረዶች አሉት። በዚያ አባጣ ጎርባጣ በበዛበት ጉዞ ውስጥ ጃንሆይ ከልጅነት ዘመናቸው ጀምሮ እስከ ስደታቸው ያለው ታሪክ በውብ የአፃፃፍ ቴክኒክ ተደራጅቶ እነሆ ለዳግም ንባብ በቅቷል።
በዚህ መፅሐፍ ውስጥ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ፀንታ እንድትቆም ልጆችዋ እና ንጉሰ ነገስትዋ የተጓዙበትን ረጅም መንገድ እና የከፈሉትን መስዋዕትነት የሚዘክር የአንድ ታላቅ ንጉስን ብዕር እናነባለን። ድንቅ መጽሐፍ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው እና በቤቱ የመጽሐፍት መደርደሪያ ላይ ሊኖሩት የሚገባ ነው። ጋዜጠኛ እና አርታኢ ጥበቡ በለጠ ስለመጽሐፉ የሰጠው አስተያየት።


ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
የገፅ ብዛት - 284 የተለጠፈበት ዋጋ - 460 ብር
መሸጫ ዋጋ - 390 ብር >= 3 Free delivery
Contact us
@Guramayelie 0912319263
4.8K views12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ