2023-04-20 08:41:19
ቃልኪዳን ችልድረንስ ኸልዝ ኬር ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን ላለፉት 3 ዓመታት ህጋዊ አካልነትን ይዞ በሃገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅትነት "ጤና ለሁሉም!" በሚል መርሕ ከጤና ጋር የተያያዙ የተለያዩ በጎ አድራጎት ስራዎችን አከናውኗል።
ከዚህም ውስጥ ጥቂቱን ለመጥቀስ
- መንግስታዊ የሆኑ ወላጅ አልባ ሕጻናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ በመቶች የሚቆጠሩ ሕጻናት እና ታዳጊዎችን የጤና እና ስነ አመጋገብ መደበኛ ክትትል
- ከሙዳይ በጎ አድራጎት ጋር በመተባበር ለተረጂዎች ነጻ የሕክምና አገልግሎት
- በአራዳ፣ የካ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከ2000 በላይ ለሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች ነጻ የህክምና እርዳታ
- በሁለት ዙር በደብረብርሃን የሚገኝው የስደተኞች ካምፕ ለሚገኙ ወገኖቻችን የአእምሮዊ እና አካላዊ የጤና ምርመራ እና ድጋፍ
ይህን ስራ ሲጀመር በ9 ሃኪሞች እና በ1 ነርስ ነበር አሁን ከ400 በላይ የሚሆኑ ነጻ የሕክምና አግልግሎት የሚሰጡ በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሞያዎችን አቅፏል።
ይህንን በጎ ስራ ለማስቀጠል የገቢ ማሰባሰቢያ እንዲሆን በሚያዚያ 22 ከጠዋቱ 1:30 ጀምሮ እስከ ረፋዱ 5:30 ድረስ የጎዳና ላይ እሩጫ እና ቤተሰባዊ መዝናኛ ቀን ተዘጋጅቷል። በዕለቱ ለሕጻናት የሚሆን የተለያዩ ጨዋታዎች፣ ሩጫ፣ ሙዚቅ እና ምግብ ተዘጋጅቷል።
ገቢውም በስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን ነጻ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚውል ነው።
ሚያዚያ 22
ፒያሳ አራዳ አካባቢ
ጠዋት 1:30 - 5:30
የአንድ ቲኬት ዋጋ 350 ብር ብቻ
ከ12 አመት በታች ለሆኑ ሕጻናት መግቢያ በነጻ ነው!
ለመመዝገብ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ፎርሙን ይምሉ
https://forms.gle/oU7pDYzkrvQbYGLy7
169 views05:41