Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር እና ጠበሳ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fonkabcha1 — ፍቅር እና ጠበሳ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fonkabcha1 — ፍቅር እና ጠበሳ
የሰርጥ አድራሻ: @fonkabcha1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.10K
የሰርጥ መግለጫ

😘ወንዱ ሴት ለማናገር ብለህ ወሬ ጠፍቶብህ ትደናበር ይሆን ሴቱአስ እንደወንዱ ሆነሽ ታቂያለሽ?
😘 ሴት ልጅ ወደ አንተ መሳብ እንዴት እንደሆነ ያቅትህ ይሆን አንቺስ ያቅትሽ ይሆን?
😘 ፍቅር ማለት ምን ማለት እንደሆነ አታቁም ይሆን?
አያሳስባቹ ቤተሰባዊ ቻናል ይቀላቀሉን።
😘ለማንኛውም መልእክት ሆነ አስተያየት 👇👇👇👇👇
@Amirlovelys

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 22:00:55 #ምርጥ ( #ምርትነሽ_የማነ)

እቴትዬና..... እሜ
አደዬና ......ሀርሜ
በየ ፈርጀ ........ፈርጁ
በእያንዳንዱ ቋንቋ ፥ ቃላት ቢወዳጁ
አንቺን .....እኮ እናቴ
የጠዋት አስኳላ ፥ የልጅነት ሀብቴ
ኑር አንተ ለኔ .......ባይ
ቅንጣት ሳይታወስ ፥ ላንቺ ያንቺው ጉዳይ
በጉያሽ አቅፈሺኝ ፥ በጪንጫ ተኝተሽ
ውሀ ባፍሽ ርቆ ፥ ወተቱን ያጠጣሽ
ማጀት ያጠቆረሽ
ረሀብ ያከሳሽ
ጎኔን ....... ጨርቄን...... ማቄን
የሚሉት ጥበቃ ፥ ከራስ በላይ ንፋስ ፥ ሰይሞ መዳከር
ላንዲት ነብስ ስስት
ላንድ አካል መንቧቸር
ከራስ በላይ ልጄ'ን
በሚል ልግስና ፥ እድሜን በመቸርቸር
ብ 'ርክ በማለት ፥ ብርክሽን የረሳሽ
በመከነ ቀለም ፥ ብዕርሽ የጠፋች።
ያ..............#ፀሀይ ውበትሽ
ኩሽና ተሳስሮ ፥ ከምጅጃ ግርጌ፥ ዕድያው የቀረ
ወዘናሽ ተሟጦ ፥ ገፅሽ የጠቆረ
በመጨናበስ #ነው
አካልሽ ለጋሱ ፥ አይነ ግቡ መልኬን ፥ ዛሬ የወቀረ ።

የአፍላነት ግዜሽ
ጥንቡሳሱን ጥሎ ፥ ያለ እድሜሽ ያረጀሽ
ደ 'ስታን ልክ እንደ መርዝ
ለልጅ በመኖር ውስጥ ፥ ዘመንሽ የቀማሽ
በአለሙ መሀል ፥ ለአለም እንግዳ
ትክሻሽ የሳሳ ፥ ቅስምሽ የተጎዳ
የህይወት ቀንበር ተጫኝ
ለፍሠሀ ባዳ !!
ሀኪም እናታለም
#ኮስማናዋ #እናቴ!!!
የህይወት መቅድሜ
የጉም ቀን መብራቴ
ተስፋ አለምሽ ይጥና
#በርቺልኝ በሞቴ
እናትነትሽ ነው ፥ በዚህ ልፋጭ አለም ፥ የቀን ክራሞቴ።

የሰማዩ ንጉስ የምድሩም ጌታ
ከምንም አብልጦ ፥ እናቱን ይወዳል
ትንሽም ሲራሩ
እናቴ ያሉ እንደው ፥ ምዕንተ ማርያም ፀሎት ይማለዳል
ውህብቶ ብዙ ነው ፥ ዳና በመከተል ፥ በገፍ ይሰደዳል
እናቴ ለሚሉት እናት መሆን ያውቃል
ስለዚህ ....
ልጄን ብለሽ አንቺ ፥ ፊቱን እንደ ሰማሽ
ያብቃኝ ....
አንቺም ያብቃሽ....
ለልጅ የተሰዋ
አድሮ የበረታ ፥ የህላዌ ጥዋ
ብሩህ ጀምበር ገጥሞ
በልጅ የፈዘዘ ፥ ዳግም በልጅ ቀልሞ
እንጥፍጥፍ አለም ....በእድሜ ስልቻ ፥ ጠብቆ ተቀምቅሞ
እያጠነጠነ...... የግዜ ሰሌዳ ፥ በመቁጠሪያ ሲታሽ
አድማስ ተሻጋሪ ... #ቦግ!!! ብሎ ማታሽ

ውድ ሸማሽ ሆኜ ፥ መቀነት ያውለኝ
ለውበት ...ለድጋፍ ፥ መጠቅለል የቀናኝ
ገንዘብ ....መቋጠሪያ
ውጋት ......ማባረሪያ
ላዱኛ ቀን ብርታት
ለጭንቅ ቀን ፅናት
አድርጎ .....እኔን ላንቺ ፥ ፈቅዶልኝ ፈጥሪ
የእናቱን ቀን አውጪ ፥ በወዘናው ጣሪ
ግብ ቀንቶት ፅናቴ
ሹልክ ብለሽ ወጥተሽ ፥ ከኑሮ ግርግር
ከእንጉርጉሮ አለም ፥ ጠማማ ውንግርግር
ምርቃትሽ ደርሶኝ ....መነን ሁኚ እናቴ
ባንቺ ውስጥ እንደኖርኩ ፥ በኔ ትኖሪ ዘንድ ፥ ይባረክ ጉልበቴ።

#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

@fonkabcha1
@fonkabcha1
120 viewsPassenger, 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:04:23 ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​


☞ ያንተ ጓደኛ ይሄ ነው ?!


ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ  የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል.....አለቃውም 'መሞቱ ለማያጠራጥር ሰው ብለህ ህይወትህን አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህም' .በማለት ፍቃድ ይነፍገዋል፡፡

ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡ ከፍለጋ በኋላ እሱም ሞት አፋፍ ላይ ባደረሰው ሁኔታ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል፡፡ አለቃውም "ይሞታል ብዬህ አልነበረም? ለሚሞት ሠው ብለህ
ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ?" በማለት ይወቅሰዋል፡፡

ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበር፡፡ "አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ
ደርሸበት ያለኝን ብነግርህ ትረዳኝ ነበር " አለው፡፡

አለቃውም "ምን አለህ?" ብሎ ጠየቀው፡፡

ወታደሩም "እንደምትመጣ እርግጠኛ ነበርኩ "፡፡

እውነተኛ ጓደኛ ማለት ሁሉም ሠው ሲሸሽህ እሱ ግን
የሚፈልግህ ነው
  

@fonkabcha1
@fonkabcha1
259 viewsPassenger, 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:46:15 ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​


አለሁኝ_በደህና

በዕውቀቱ ሥዩም
.
አንቺ እንደምን አለሽ
… እኔ አለሁ በደህና
ይመስገን ዳመና
በገበሬው አጥንት – መሬቴን እያረስኩ
በገበሬው እንባ – ማሳ እያረሰረስኩ
እንጀራ ቢጠፋ – ገበሬ እየጎረስኩ።
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና
.
ሰው ሲያፈርስ እያየሁ
ሰው ሆኖ ቡልዶዘር
አንዱ ጭጋ ነገር ሌላው የብረት ዘር
በፈረሰ ሰው ላይ በቆመ ሰገነት
ሲዖል አናቱ ላይ በታነፀ ገነት
ይኽን ኑሮ ብለው ጥቂቶች ሲኖሩ
…ያለምንም ፀፀት
…ያለምንም ሃፍረት
ይህንን እያየሁ በታላቅ ፅሞና
ኣለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና።
በምቾት መዲና
የነዳያን ትዝብት እንደ ሀሩር ልፎኝ
በጠዳ ጎዳና ለማኝ ብላቴና
እንደ ጉቶ አንዳቅፎኝ
ሃፍረት እንደ ዝናር ከፊት ከኋላ ኣቅፎኝ
ልክ እንደ ደባሎች ለመኖር እያቀድሁ
በጌቶች መሶብ ላይ እጀን እየሰደድሁ።
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና
.
ወይ በሩን አሳዪን ወይ ጠቁሚን መላ
መዓበል ሲቃረብ ያመልጣል ሽመላ
በነፋስ ገፅ ፊት ይሸሻል ዳመና
የኔ ሃዘን ያለበት ያ’ገሬ ሰው ግና
በስጋ ደም አጥንት የተሰራ ይመስል
እንደ ኮንሶ ሃውልት የመቃብር ምስል
አይሸሽ አያባርር ወይ አይተነፍስ ቃል
እንጨት ሆኖ ቆሞ ሰደድ ይጠብቃል።
.
ይህንን እያየሁ ሁኘ በጥሞና
አለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና
አንቺ ግን አለሽ ወይ እኔ አለሁ በደህና
ኣለሁ ግርምት ኖሮኝ
ምላሱን በምላጭ እንደተሰለበ
............የማስበው ኖሮኝ
.................የምለው ቸግሮኝ ።


@fonkabcha1
@fonkabcha1
36 viewsPassenger, 19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:23:19 ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​


አቢ ማርዬ

ሆያ ሆዬ ጌታው ደጃፉን ክፈተው
አንተን አደለም ወይ የምንጋተተው?
ሙደ ገድ አትሁን ጀለስካ በርግደው
ጃን ሜዳ ተወልዶ ኤድና ሞል ያደገው
ቾምቤ ከተፍ አለ ሳቢ ቢጎትተው
እና እንደምታዪው ሲስቱካ ማርዬ
አመድ ውረጅልኝ ይልሻል ባርዬ
የቻት ግዜ ማጣት ቀልድ አይደል እሙዬ
ውረጂ.....ውረጂ.....ውረጅ ለባርዬ
ከጠዋት ጀምሬ ስንቱን አባብዬ
ቋጣሪ ፈትቼ ንፉግ አታልዬ
እናት ቀለል አርጉት ፋዘር አይገጅሩ
እንደ እድሜዎት ሳይሆን እንደ ጊዜው ኑሩ
አመድ ጨላ ሆኖ አትደራደሩ
የፀዳ ቅላፄ ያበደ ጉሮሮ
ቢልቦርድ የሚረታ ራንኩን ሰባብሮ
ይዘን ከቻስ አልን በኒሳን ፓጃሮ
በራቫ በቪላ ልባችን ታውሮ

አረ .....በቃ ......በቃ
ጉሮሮዋችን .....ነቃ
አረ ላሽ አይነፋም...አንድ አመድ አይጠፋም

የሚል ሆዬ ክሩ
የhope entertegnment እህት ኩባንያ
የሳባት እታለም ለዘመኑ ባዳ
የቅዬው ታውሷት... የወዛ አኮፋዳ
እንኩ በሉ ልጆች..ብላ ሙልሙል ብትልክ
የሰፈሩ ውሪ በፈገግታ ሙክክ
...
...
ማዘርዬ... ሼም ነው
ኮይን ይውረዱ እንጂ ፥ ሙድ መያዝ ምንድነው?
ላሽ ይሄን ውሰዱት ፥ የቡቺ ምግብ ነው
ብትባል በግንባር
ዘመን ተገልብጦ...ጊዜው ተለውጦ
ትውፊት አርጅቶ አቡዬ ዘንጦ
በመስጠት አፈረች ባይተዋር እሙዬ
ሆያ ሆዬ የሚል አባቡ ማርዬ
ላጋፋሪ ድግስ ጭሱን ተከተሎ የሚደርስ ኢጆሌ
ጎፈሬው ደመና ቅንድቡ አይነኩሌ
ሽመል ያነገበ ቀምጣላ ኮበሌ
እታለም ናፈቃት ...
ባያት አስተምህሮ በልጅ አቅል ማጣት
ትወቅሰው
ትከሰው
ትነግረው....ቢጠፋት።

             #አብርሀም_ተክሉ


@fonkabcha1
@fonkabcha1
166 viewsPassenger, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:38:13 ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​

  
                   _አንድ ቀን ይበልጣል_

አንዳንዴ
ን...ፍ...ቅ ያልሽኝ ጊዜ

አለ አደል ዝምብሎ ድንገት በሚመስል
አስቤሽ አስቤሽ ሆዴ ብ...ብ...ት ሲል

ወይም ...

ፍጥረት አስጠልቶኝ
ትዝታሽ ጎትቶኝ
በናፍቆት መንጋጋ ልቤ ሲጎረመድ
እጥፍ ያለ ጊዜ አንጀቴ እንደ ገመድ

ካፊያ ያረጠባት ክብሪቴን ተርኩሼ
ስትሄጅ የገዛሁት ማርቦሎ ለኩሼ

ለካ አልነገርኩሽም
ያኔ ስትሄጂ

አቅም ያለኝ መስሎኝ ልቤን አባብዬ
የሸኘሁበትን መንገድ ተከትዬ

  ቻው ብዬሽ ስመለስ
አላስቀምጥ ብሎኝ
አቦል ቡና ናፍቆት ያንጀቴን ስርጣስርጥ እየቦረቦረ
ጭስ ያድነኝ መስሎኝ የገዛሁት ነገር ማርቦሎ ነበረ

ብቻ ግን
አንዳንዴ
ን...ፍ...ቅ ያልሽኝ ጊዜ

አለ አደል ዝምብሎ ድንገት በሚመስል
አስቤሽ አስቤሽ ሆዴ ብብት ሲል

ወይም...

ፍጥረት አስጠልቶኝ
ትዝታሽ ጎትቶኝ
በናፍቆት መንጋጋ ልቤ ሲጎረመድ
እጥፍ ያለ ጊዜ አንጀቴ እንደ ገመድ

ካፊያ ያረጠባት ክብሪቴን ተርኩሼ
ስትሄጅ የገዛሁት ማርቦሎ ለኩሼ
      
            እንደዚህ እላለሁ

ለምን እኔ ብቻ
እንድትመጪ ብዬ
ያስቆመሸን መንገድ እቦረቡራለሁ
እስከመቼ ድረስ
ተስፋን እንደግጥም ሳነብ እኖራለሁ ?

እባክሽ እቴ ሆይ
እንደምንም ብዬ እንደምንም ብለሽ
እንዴትም ሞክሬ እንዴትም ሞክረሽ

ባክሽ እንገናኝ
ላይነ ስጋ እንብቃ
የኔና አንቺ ርቀት ከነጥብ አይስፋ
አንድ እቅፍ ይበልጣል ከዘላለም ተስፋ

ግጥም  አማረ ዘውዱ
2014ዓ/ም
@fonkabcha1
@fonkabcha1
194 viewsPassenger, 05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:38:13 ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​


                  ያምና ናፍቆት
ሚካኤል አስጨናቂ

እሷን አስብና !
የቀድሞዋ ፍቅሬን፦
ያምናዋ ወዳጄን...
እኔ ባጠፋሁት ፥ በበደልሁት በደል
ይቅርታ ማለቷን ፥ ከኔ እንዳትነጠል
ደግሞ አንቺን አይቼ ...
በምትምሽው ገደል ፥ በለኮስሽው እሳት
ሳለ ያንቺው ጥፋት!
እኔው ይቅር ብዬ ...
ደጅሽ ላይ ተጥዬ ...
በተማጥኖ እንባ ፥ ወራት ባስቆጥርም
ፍቅሬን ስትገፊ ፥ ልብሽ እንዲለግም
አገኘሁ እላለሁ!
ያምና ብድራቴን
እሷ ላይ የቆየኝ
የሐጥያት ውርሴን ።
ይኸው ዛሬም ድረስ!
እሷ ባቀናችው ፥ ጎጆ በማይበቁ
ለሷ በቀለድሁት ፥ ቀልድ በማይስቁ
እሷን ባስለቀሳት ፥ መርዶ በማያዝኑ
እሷን በማረካት ፥ ቦታ 'ማይዝናኑ
ከክፍቱ ጎኔ ፥ መሙላት በማይችሉ
አንዴ በሚረዝሙ ፥ አንዴ በሚጎድሉ
በግዑዛን ሴቶች ፥ መንደር ተሰልፌ
አምናን እራባለሁ ፥ ዘንድሮን ታቅፌ።


@fonkabcha1
@fonkabcha1
172 viewsPassenger, 05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 22:20:29 ​​የቀጠለ ......

መግጠም ማበድ አይደለም ፤ ፎቶዋን ይዞ መዞር  እብድ አያሰኝም ፤ በየቀኑ ማልቀስ እብድ አያስብልም ፤ ለምን አብዳለው ደህና ነኝ ብላኝ የለ?


ተ ፈ ፀ መ





በቀጣይ ስራዎች ምንገናኝ ይሆናል አብራችሁ ስለቆያቹ ከልብ እናመሠግናለን

በዚው ቻናል ቀጣይ ስራዎች ይቀርባሉ…

አመሰግናለው!
@fonkabcha1
@fonkabcha1
249 viewsPassenger, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 22:14:47 ​​​​​​​​​​​​​​​​​


ሴትን አላምንም

የመጨረሻው ክፍል


ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ



ሄሎ አለኝ የአህላምዬ የማይመስል ድምፅ

አህላም ነሽ?

አይደለሁም ሐያት ነኝ ሰዒድ ብላ መለሰችልኝ ፤ ድምፇ ይቆራረጣል አንዳች የመረበሽ ስሜት ያለው ይመስላል.....

ሀዘን ጥላውን ጥሎብኝ ብቸኝነት እንደ ብርድ ሰቅዞ የያዘኝ መሰለኝ ፤ የአህላም ድምፅ የለም  እህቷም የሀዘን ቀንዲሏን ልትነፋ በሚመስል ድምፅ መናገር እያቃታት አህላም ትንሽ አሟታል ፤ ከቻልክ ሆስፒታል ና ግን ብዙም አይደለም ህመሙ ፤ ማየት ከፈለግክ ብዬ ነው ብላ ያለችበትን ሆስፒታል በምልክት ነግራኝ ስልኩ ተዘጋ ፤ ከዚህ ቡኃላ መድረሻዬን እንጂ በምን መንገድ እየሄድኩኝ እንደሆነ አልገባኝም ግን አንድ ቦታ መድረስ ነበረብኝ።

መንገዴ ላይ ሁሉ መልኳና ያ ውብ ገፅታዋ የሰርግዋ ቀን የነበረው ፈገግታዋ ይታየኛል፤ እርሱን ሳስብ አቅምና ጉልበት እየሆነኝ ወደ ሆስፒታሉ ለመድረስ እጓጓለው።

በቀዩ ገላዋ ላይ ነጩን ቬሎ ለብሳ ፤ ነጫጭ ጉትቾችን በጆሮዎቿ ላይ አንጠልጥላ ፣ ያ ውብ በሆነው አንገቷ ላይ ሀብል አድርጋበት ፣ በሚያስደምም እግሮቿ ላይ ነጭ ጫማ ተጫምታ ከሰርጉ አዳራሽ ላይ ቁማ ያየሗት ሚስቴ ዛሬ ታማ ሀኪም ቤት ገብታለች ፤ ዛሬ እርሷን ማዳን ካልቻልኩኝ ምኑን ባል ሆንኩኝ ፣ ምኑን ብረት መዝጊያ ተባልኩኝ ፣ ዘላላም የአንቺው ነኝ ብዬ ቃል የገባሁላትስ ምኑ ጋር ነው?

ሆስፒታል ስደርስ በሰዎች ግርግር ተሞልቷል ፤ ዙሪያውን ሳጠና የአህላም ወንድምና እህት ሌሎች ብዙ ቤተሰቦቿ በትካዜ ቆመዋሉ ፤ እንባ እየተናነቀኝ  ሰውነቴ እያንቀጠቀጠኝ ቢሆንም ወደ ሐያት ጠጋ ብዬ።

አህላምስ? አልኳት

ውስጥ ገብታለች ዶክተሮች እያዯዋት ነው።

ምን ሆና ነው? እንባዬ እየፈሰሰ

እኔ እንጃ ሰሞኑ ልቤ እያለች ነበር የድካም ስሜት እየተሰማት ነበር ፤ ዛሬ ግን ተዝለፍልፋ ወደቀች በስልክ ስታወራህ ደህና ነኝ ስትልህ የነበረው እንዳትጨነቅ ነው ፤ መታመሟን ብናቅም ለአንተ መናገር እንደሌለብን አስጠንቅቃን ነበር ፤ ሰዒድ ከአንተ ጋር ከመጣች ቡኃላ ሁኔታዋ ልክ አይደለም ፤ እንቅልፍ አተኛም ፣ ታለቅሳለች ፣ ምግብ አትበላም ደግሞ መተንፈስም እየከበዳት ነበር ዛሬ ግን ደከመች ብላ አለቀሰች።

በደከመሽ ሰዓት ጥላሽ ኝ ብዬ ዛሬ ግን ጥላዋን ነጠቅኳት ፤ ጋሻሽ ነኝ ከችግሮችሽ ሁሉ የምከላከልልሽ ብዬ ቃል ገብቼ ዋሸሗት ፣ የደስታሽ ጊዜ ደስታሽን አድምቄ በችግርሽ ሰዓት ችግርሽን ተከፍዬ ከጐንሽ እቆማለው ብዬ ዛሬ ግን ብቻዋን ለእነዛ ህልምን በሳጥን ለሚያደርጉ ነጭ ለባሾች ሰጠሗት።

የአህላም ቤተሰብ? ሁለት ዶክተሮች ነበሩ

ሁሉም ተሰብስቦ ሄዶ "እኛን ነን"አያሉ

አንደኛው ዶክተር

አዝናለው! ህይወቷን መታደግ አልቻልንም ፤ አረፈዳቹ ፈጣሪ መፅናናቱን ይስጣቹ ብሎ ወደ መጣበት ተመለሰ።

የእኔ ናፍቆት ፣ የህይወቴ ማዕረግ ነፍሷ ከስጋዋ ተነጠለ ፤ የዘመናት ውጥኗ እና ያ መልካም ስብዕናዋ በጨረቅ ተሸፈነ ፤ ረጋ ባለ ድምፅ ጠርቼ አቤት የምትለኝ  አህላም ዛሬ ጮኼ ብጠራትም ጆሮ አልሰጥ አለችኝ።

ሁሉም ይጠሯታል የእኔ ልጅ ፣ የእኔ ከርታታ ፣ አባቷን  መሳይ ፣ እህቴ ፣ የእኔ እናት ፣ አበባዬ ፣ ለማን ጥለሽኝ ሄድሽ እያለ ያለቅሳል።

እኔስ ማን ብዬ ላልቅስ እናቴ ፣ እህቴ ፣ አባቴ፣ ጓደኛዬ ፣ ሚስቴ? ሁሉ ነገሬ እኮ ነች ፤ ሁሉ ነገሬን አጣሁኝ በመንገድ ላይ ተጠልፍኩኝ ፣ የበራው ሻማዬ ጠፋ ፣  ጐጆዬ ላይ ዳግም ትልቅ ጨለማ ተጋረደበት ፤ ደህና ነኝ ብላ እርሷ ግን የለችም ፤ አህላምዬን አጣሗት ፀ በስልኳ ውስጥ የሚሰማው የህመም ድምፅ በደህና ነኝ ቃል እየተሸፈነብኝ ፣ ለማሜ ምን ብዬ ልናገር? አደራዋን የበላሗት እናቴስ ነፍሷ እንዴት ያርፍ ይሆን?


አላውቅም መንገድ ላይ እየሄድኩኝ ነው ፤ ሰዎች እኔን አበደ ይሉኛል ግን ምንድን ነው ማበድ ፤ ቀኑ ምን እንደሆነ አለማወቅ ፣ የተቀደደ ልብስ መልበስ ፣ ጫት እጅ ላይ ይዞ መዞር ነው?

እኔ አላበድኩም ሁሉም ሰው መንገድ ላይ እያየ ይሸሸኛል አብጄ ነው እንዴ?

የአንዲትን ቆንጆ ሴት ፎቶ ይዞ ከተማ ላይ መዞር ፣ የሆነ ሆስፒታል ሂዶ ህልሜን መልሱልኝ ማለት እብደት ነው እንዴ?

እኔ አላበድኩም ፤ ምኑ ነው እብደት?

ስምሽን ሲጠሩ ማልቀስ ነው እብደት?
እንደ ጅል መሳቅ ነው እብደት?
ከሰካውት ሰንደል ጠረን መሳብ ነው እብደት? 
በጫት ገለባ መሬቱን መሞንጨሬ ነው እብደት?

እንድረሳት ያ ሁሉ መሆኔ ነው እብደት?

 
ለምን አትተውኝም? 

ልረሳትስ ብል መች እረሳታለው ፤ ሁሉ ቦታ እርሷ አለች ያልተራመድንበት  ያልተጓዝንበት መንገድ የት አለ?  ያልተቀመጥንበት ያለወራንበት ጐዳና መች ተዘረጋ?

ጐዳናው ላይ መቀመጥ ነው እብደት ፣ ማብድ ምን እንደሆነ አህላምዬ ታቀዋለች ፤  እርሷን አግኝታቹ ጠይቋት እኔ ግን አላበድኩም ፤ አቅሌ እርሷን እንጂ አያስብም ፤ ይህ ለኔ እብደት አይደለም። 

ግን ይህው እርሷን እየጠበቅኩኝ ፣ ስለእርሷ እየገጠምኩኝ አለሁኝ መግጠም ማበድ ነው?

ሻማው ሲጠፋ
~~~~
ሀዘን ካሰመጠው
ጨለማ ከዋጠው ፤
ከቀዝቃዛው ቤቴ አንድ ሻማ በርቷል
የፍቅራችን ዕድሜ አንድ ዓመት ሆኖታል፡፡

አንቺ ግን የለሽም
ሁሉ ሞልቶ ሳለ አንቺ ግን የለሽም ፤

እንደ ባለቅኔው ቃላት እንዳጠረው
ትመጪ እንደው እያልኩ ልክ እንደ ዜመኛው
ተስፋ ባጣ ሻማ እጠብቅሻለው፤
ቢሆንም አትመጪም
ግና ተስፋ አልቆርጥም ፡፡

እኚ ክፉ ሰዎች ክፉ ወዳጆቼ
ስጋዬ ያልኳቸው ክፉ ዘመዶቼ ፤
አትመጣም ይሉኛል ፥ ሞታለች ይሉኛል
"አብዷል" እያሉ አምተው ያሳሙኛል
ሄዳለችም ብለው ልቤን ያቆስሉኛል፡፡

እኔ ግን
ተስፋ ባጣ ሻማ እጠብቅሻለው
ቢሆንም አትመጪም
ይህንን አውቃለሁ
ግና ተስፋ አልቆርጥም
መቁረጥም አልችልም

ግና ፍቅሬ የት ነሽ ፥ የት ይሆን ያለሽው
ምን ባደርግሽ ይሆን እንዲ የጨከንሽው ፤
ላልተውሽ ላትረሽኝ በፍቅር የማልነው
ምንስ ባስቀይምሽ ቃሉን የረሳሽው፡፡

ጭር ካለው ቤቴ አንድ ሻማ በርቷል
የፍቅራችን እድሜ አንድ ዓመት ሆኖታል፡፡

ከአንድ አንቺ በስተቀር እዚህ ሁሉ ሞልቷል
የምንወደው ዜማ ቤት ውስጥ ያስተጋባል
የምትወጂው ምግብም ፥ ሽታው ልብ ያስርባል
የምወደው ሳህን ከፊቴ ተቀምጧል
አልጋውም ተነጥፏል
የፍቅራችን ምሽት በጨረቃ ደምቋል
ግና ፍቅሬ
አንቺ ብቻ ቀርተሽ ሁሉም ባዶ ሆኗል፡፡

ለፍቅራች ዕለት
ለዚህ ጣፋጭ ምሽት ያበራሁት ሻማ
'ላዩ ሲበራ ፥ ከታቹ የደማ ፤
ሚስጥር ይነግረኛል
እውነት ያሳየኛል፡፡

በመስኮት የገባ ንፋስ ሲያረብበት
ብርሀኑን ሊያጠፋ ገፍቶ ሲመጣበት ፤
እርሱ አጎንብሶ ፥ ንፋስ ያሳልፋል
ዕድሜ ለመቀጠል ዕድሜውን ይቀጥፋል ፤
ጭር ካለው ቤቴ ያበራሁት ሻማ
ሚስጥር ይነግረኛል
እውነት ያሳየኛል
"ፍቅርህስ ?" ይለኛል፡፡

ፍቅሬ ምን ልበለው
ቀርታለችም አልል ፥ መጥታለች አልለው
አንድ ሻማ ይዤ እጠብቅሻለው ፤
ቢሆንም አትመጪም
ይህንን አውቃለው ፤
ባውቅም ተስፋ አልቆርጥም
መቁረጥም አልችልም፡፡

ውዴ...
አንቺን ለመጠበቅ ያበራሁት ሻማ
'ላዩ ሲበራ ፥ ከታች 'እየደማ፡፡

አሁን ሻማው ጠፍቷል ፥ እኔ ግን ቆያለው
ለተስፋ ብርሃኔ ልቤን አነዳለው
ቀልጦ ያለቀ ዕለት እኔው እመጣለው፡፡
249 viewsPassenger, 19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:22:56 የታሪኩን የመጨረሻ ክፍል ነገ ይጠብቁን
@fonkabcha1
@fonkabcha1
270 viewsPassenger, 17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:21:50 ​​​​​​​​​​​​​​​​​​


ሴትን አላምንም

ክፍል 19

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ


የሰማሁት ድምፅ አስደንግጦኝ የሳሎኑን በር በኃይል ከፍቼው ስገባ ያየሁት ነገር አረጋጋኝ ፤  አህላምዬ የመኝታ በሩን ባላት ጉልበት መታው ስለነበረ ነው ያ ከፍተኛ ድምፅ የተሰማው ፤ መኝታ ክፍል ገብቼ ላረጋጋት ብሞክርም  መረጋጋት አልቻለችም ከባድ ፈተና እንደተጋረጠብኝ ታወቀኝ። እርሷን ትቼ ወደ ሳሎን ተመለስኩኝ ፤ ተስፋ ቆረጥኩኝ ወገግታው ሲጨልም ብርሃን ከእኔ ሲሸሽ ታየኝ ፤ የመኖሬ ምክንያት የሆነችው አህላም ዛሬ ከፍቷታል ፤ የሚያፅናናኝ  የለም ምክሯ ሁሌም ተስፋ የሚሆነኝ ሚስቴ ዛሬ ምክርን መቀበል አዳግቷት ትራሷን ታቅፋ እያለቀሰች ነው ፤ አህላምዬ ባላጠፋችው ጥፋት እራሷን እየቀጣች እንደሆነ ቢገባኝም ካለችበት ሀዘን ልመልሳት አልቻልኩም ፤ አሁን የመከራና ናዳ ሊወርድብኝ እንደሆነ ታወቀኝ። የእኔ የምላቸውን ሁሉ አጥቼ አህላምዬ ነበር የቀረችው ፤ የሁሉ ምትክና የእናቴ አደራ የሆነችው ሚስቴ ዛሬ ተረታለች ፤ ሰማዩ ሲጠቁር ፣ የህይወቴ ነጐድጓድ ሲያጓራ ፣ መከራዬ ሲያጉረመርም ፣ የዘመን ህመሜ ሲነሳ ተሰማኝ ። ውሀ እየጠጣሁኝ ውሀ ጠማኝ  ፣ የሰማዩ ባህር ቁልቁል የተናደብን መሰለኝ፣ ያንዘፈዝፈኝና መለስ ብሎ ደግሞ ያቃጥለኛል ፣ ከአጠገቤ ብን ብላ ስትጠፋ ታወቀኝ ፤ "አበደ ሰዒድ አበደ! ብለው ሰዎች የከበቡኝ መሰለኝ ፤ ዛሬ ሁሉም የሉም እናቴም የለችም።  

ካሂሊል ጂብራን አልኩኝ በውስጤ ስለ እናት የተናገረው ትዝ ብሎኝ

በሰው ልጆች ከሚጠሩት ቃላት ሁሉ እጅግ የተዋበ ቃል "እናት" የሚለው ቃል ነው። እጅግ ቆንጆ አጠራርም "እናቴ" የሚለው ነው። በተስፋ እና በፍቅር የተሞላ፣ ከልብ የሚመነጭ ፣ ጣፋጭ እና መልካም ቃል ነው። እናት ሁሉንም ነገር ናት በሃዘን ጊዜ መፅናኛችን፣ በስቃይ ጊዜ ተስፋችን፣ በደከምን ጊዜ ጥንካሬያችን ናት። የፍቅር ፣ የምህረት ፣ የርህራሄ እና የይቅር ባይነት ምንጭ ናት ፤ እናቱን ያጣ ያለ ማቋረጥ የምትባርከውና የምትጠብቀውን ንፁህ ነፍስ አጥቷል ፤ አዎ ዛሬ ምንጬ በደንብ ደርቆ አቧራ መልበሱ ታወቀኝ።


መሀመድ ውጪ ቆይቶ መጣ ፤ ለረዥም ደቂቃ ፀጥ ብሎ አጠገቤ ተቀመጠ ፤ ተነስቶ አህላምዬ ጋር ሄደ አሁንም እያለቀሰች ነው።

ምን ይሻላል ? አለ ረጋ ባለ ድምፅ

እኔ እንጃ ማሜ አላውቅም

ያ ጠንካራ መንፈሴ ተረታ ፤  ጓደኛዬ ምን ይሻላል አትበለኝ የሚሻለውን ምረጥ እና አድርግ ፤ ስለምን ላስብ ሀዘኗ ልቤን ይጎዳዋል ፣ ለቅሶዋ ህልሜን ያበላሸዋል ፣ በመንገዴ ሁሉ እርሷ አለች ዛሬ ግን እንዳየሗት ሁናለች ፤ ማሜ እባክህን ዕርዳኝ አልኩት።

እየፈራ እየቸረ ቤተሰቦቿ ጋር ለጥቂት ጊዜ ትሂድ ያለው አማራጭ ይህ ነው አለኝ ። ከእህቶቿ የአንደኛዋን ስልክ ስጠኝ እና እናናግራት እና ትምጣ ፤ ያለውን ነገር እናስረዳት አሁን ያለን አማራጭ ይህ ነው ፤ ሰዒድ ያሉብህ ዕዳዎች ከአቅም በላይ ሁነዋል ብዙ ቼኮች የሰዎች እጅ ላይ አለ ፤ አህላም ስራ መበላሸቱን እንጂ ይህንን ሁሉ አታውቅም ፤ ስለዚህ ለትንሽ ጊዜ ከዚህ ትራቅ ማስተካከል ያለብን እናስተካክል አለኝ፤ እኔም እየከበደኝም ቢሆን በሀሳቡ ተስማማሁኝ። እህቷ ጋር ተደወለ እቺኛዋ የሞተችዋ ታላቅ ነች ነገሮችን በእርጋታ ማየት የምትወድና ቅን ልብ ያላት ሴት ነች ፤ "ሐያት" ከመሀመድ ጋር ተደዋወውለው ያለውን ነገር አውርተው መጣች ፤ መሽቶ ስለ ነበር እዚሁ አድርው ነገ መሄድ እንዳለባት ተስማማን ፤ እነሱ ያወራሉ እንጂ እኔ አቅም አጥቻለው ፤ በራሴ ሕይወት ላይ ሀሳብ መስጠት ተስኖኛል ፤ አህላም ለአንድ ደቂቃም ሳታየኝ ነጋ ፤ ማሜ በጠዋት መጥቶ ስለነበር ከእህቷ ጋር አህላምን አነጋገሯት ፤ "አህላምም" ትንሽ እየደከማት ስለነበር በሀሳበቸው ተስማማች ፤ ሀዘኑ በአንድ ቀን ጎድቷታል ፤ መሀመድ እና ሐያት ቀድመው ከቤት ወጥተው እኔና እርሷ ብቻ ቀረን። ተነፋፍቆ እንደተገናኝ ሰው አቅፈችኝ የኔ ውድ? " ህልምህን አጨለምኩብህ ፣ ተስፋህን ሰረቅኩህ ፣ እባክህ ይቅር በለኝ እባክህ" ለቅሶዋን  ማየት ከበደኝ።

አህላምዬ

"አንቺ ፈልገሽ ያደረግሽው ምንም ነገር የለም ፤ ይህ የአላህ ውሳኔና ፍቃድ ነው ፤ አላህ ለምን እንዲህ አደረግክ የማይባል ጌታ በፍጡራኑ ላይ ምንም ነገር የሚያደርግ ጌታ ነው ፤ አንቺ ብቻ ሳትሆኚ ብዙዎቹ የእዚህ ችግር ሰለባ ናቸው ፤ እኔ ደግሞ አንቺን ብዬ እንጂ ለልጅ ብዬ አላገባሁም ፤ ከምንም በፊት አንቺ ትቀድሚያለሽ ፤ ደግሞ እወቂ አላህ ያሻውን የሚሰራ ጌታ ነው "ለነብዩላህ ዘከርያ በእስተርጅና ልጅን የሰጠ ፣ ነብዩላህ አዩብን ከዛ ከመከራ ፣ ከበሽታ እና ከድህነት ሕይወት ዳግም ወደ አዲስ ሕይወት የመለሰ ጌታ ነው። ስለእኛ ከእኛ በላይ አላህ ያውቃል ፤ ለትንሽ ቀን ቤት ሂጅና ተረጋጊ ፤ እኔ ሁሌም የአንቺው ነኝ ብዬ ግንባሯን ስሜ ሸኘሗት።

እሷን ሸኝቼ ትንሽ ህመም እና የድካም ስሜት ሲታየኝ ሆስፒታል ሄድኩኝ ፤ ሆስፒታሉ በር ላይ እናቱን እና እህቱነሸ በሞት የተነጠቀው  ያ ወጣት ቆሞዋል።  ዛሬ ምርር ብሎ ነው የሚናገረው "ሴትን አላምንም አዎ ሴትን አላምንም" ፤ እንኳን ሴት እናታችሁን አትመኑ አለሁልህ ብላ ጥላኝ ሄደች ፣ መጣሁኝ ብላ ለዘለዓለሙ ተለየችኝ ፣ ብቻዬን አስቀረችኝ ፣ ሴትን አትመኑ ፤ እህቴም ሴት ነበረች ሁሌም የአንተው ነኝ  እንዳላለችኝ ዋሽታኝ ሄደች ፣ ጠብቀኝ ደርሻለው ብላ ቀረች ታድያ ማንን ልመን እኮ ሴትን ? የታለ ቆሜ እድርሀለው ልጅህን ተንከባክቤ አሳድግልሀለው ብለው ቃል የገቡልኝ?  የታለች የሰርግህ ቀን የሸሚዝህን ቁልፍ  ከእኔ ውጪ ማንም አይቆልፍልህም ብላ ቃል የገባችዋ እህቴ? ቃልዋን አፍርሳለች ! ለምን ሴትን አምናለው የታለች እናቴ ፣ የታለች እህቴ?

 አዎ! አምናችሁ እዚህ አትግቡ እዚህ የገባ አይወጣም ፤ እናቴ መናኸርያ ቀጥራኝ እዚህ ነበር ያገኝሗት ፤ እዚህ ምን አለ ? እዚህ እኮ ህልምን በሳጥን አድርገው የሚሰጡ ሰዎች ናቸው ያሉት እያለ ይጮሀል ፤ የተሰበሰበው ሰው በሀዘን ዳር ቁሞ ይመለከተዋል ፤ አዎ አላምንም እናንተም አትመኑ እያለ ሄደ ፤ እኔም ስለ ወጣቱ ንግግር እያሰብኩኝ ወደ ውስጥ ገብቼ ህክምናዬ ጨርሼ ወጣሁኝ።

አህላምዬን በስልክ እያገኝሗት ሁለት ቀን አለፈ ፤ ድምፇ ብዙም ደስ የሚል ስሜት የለውም ሀዘኑ ይሆናል ብዬ አስብያለው ፤ እኔም ቼክ የሰጠሗቸው ሰዎች እንዲታገሱኝ ከማሜ ጋር አብረን እየሄድኩኝ ተማፅኖዬን ቀጥያለው።

ቢሆንም አህላም ከሄደች ቡኃላ  በስቃይ ላይ ስቃይ በህመም ላይ ህመም ተደራርቦ የልቤን ቁስል አመረቀዘው ፤ ተደብቄ ስለ እናቴ እያለቀስኩ ያሳለፍኩት የመከራ ጊዜ ዳግም ተመልሶ መጣብኝ ፤ አህላምዬ እናቷ ቤት መሄዷን ሳስብ ዓለም የሸሸኝ መሰለኝ ፤ ውስጤ እያለቀሰ ልቤ እየደማ ቀናቶች አለፉ ፤ ዛሬ በጣም ናፍቃኛለች ሀዘኔን እንዳታየው መጨነቄን እንዳትረዳ ነበር እስካሁን ቤትም ሄጄ ያልዘየርኳት ፤ ባለ መምጣቴ ቅር ቢላትም ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም ፤ ስራዬ ከተበላሸ ቡኃላ ቤተሰቦቿ ጋር መሄድ ከባድ ሁኖብኝ ነበር ፤ ወንድሟም የሰው ብር እንዳለብኝ ከሆኑ ሰዎች ሰምቶ ስለነበር የበፊት ፍቅሩ ዛሬ ላይ የለም ፤ ዛሬ ግን ላገኛት መሄድ አለብኝ ስልኬን አውጥቼ ስደውል አይነሳም ደጋግሜ ሞከርኩት ከብዙ ጥሪ ቡኃላ ስልኩ ተነሳ

ሄሎ አልኩኝ ተቻኩዬ

ክፍል ሀያ ይቀጥላል
@fonkabcha1
@fonkabcha1
265 viewsPassenger, 17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ