2022-08-22 15:37:45
ሴትን አላምንም
ክፍል 16
ሽማግሌዎቹ የአንድ አካባቢ ሰዎች ስለሆኑና በአካባቢያቸው ትልቅ ሰው ስለሞተ ነበር በአንድ የስልክ ጥሪ ኒካሁን በሙሽሮች መግቢያ ሰዓት እናድርገው ብለው በአንደኛው ሽማግሌ በኩል ለእኔ ሽማግሌዎች መልዕክት ያስተላለፉት።
ይገርማል ሕይወት ጉራማይሌ ነች ፤ በአንዱ ቤት የድግስ ድንኳን ተጥሎ ሌላኛው ቤት ደግሞ የለቅሶ ዳስ ሁለት ዓይነት ሙሾ ሁለቱም ለእኔ ያድርገው መልዕክት አንደኛው ለእኔ ያድርገው ሞቱን ሁለተኛውም ለእኔ ያድርገው ሰርጉን ነው።
የእውነት መንገድ ለመጀመር ከሚዜዎቼ ጋር ጉዞ ጀመረናል ፤ በመዋደድ እና በፍቅር ጥላ ውስጥ ተጠልሎ የቆዬው ፍቅር ጐጆውን ሊቀለስ ውጥኑን አሳክቷል የደስታ ሲቃ ፣ የአሸናፊነት መንፈስን ተላበስኩኝ።
አዎ አህላምዬ እናቴ እና የእናቴ ምትክ ነች ፣ ለእናቴም እንደ ልጅ ሁና ፍቅርን የቸረች ሚስት ዛሬ በህይወቴ መስመር ገብታ ቃልኪዳን ልንጋባ በእምነት መስመር ልንታጠር ፣ ልብሷ ልሆን ገመናዋን ልሸፍን አህላምዬ ጋር እየሄድኩኝ ነው ፤ ወንድሟ ባለኝ መሰረት በሱፍ ተውቤና ተሽቀርቅሬ
እውነተኛ ሳቅ እና ደስታ ውስጤ ሲፀርስ እየተሰማኝ ሄድኩኝ።
የማለዳ ሃሳቤ እና የህይወቴ አጋር አህላምዬ ጋር ቤቷ ደጃፍ ደረስኩኝ። አናስገባም ሰርገኛ የሚመስል ጭንቅንቅ ሙሸራ ሳይሆን ንጉስ የሆንኩ መሰለኝ ፤ ሁሉም እኔን ለማየት የጓጓ ይመስላል በመኪናው ዙሪያ ሰዎች በእኔ ማግባት ደስታ መንዙማ እያሉ ማጀብ ጀምረዋል ፤ ፈገግ የሚያስኝ ግጥም ከመሀከላቸው ይሰማል።
ያገባም አገባ ያላገባም ያግባ
ማሜ ብቻ ቀረ ሻወር እየገባ
ማሜ ከእኔ በላይ ደስተኛ ሁንዋል የጓደኝነት ትርጉም የገባው ንፁህ እና መልካም ሰው።
"እውነተኛ ጓደኝነት ማለት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የማይሻክር በመከራ ጊዜ ጥሎ የማይሸሽ ፤ እውነተኛ ጓደኝነት ማለት በመከራም ሆነ በደስታ ጊዜ የማይሻክር ፣ እንደ አለት የጠነከረ፣ በማንኛውም ጊዜ መተሳሰብና መከባበር ያለበት ትልቅ ቁምነገር ነው።
ይህንን ትልቅ ነገር ደግሞ በስርዓት እና በአግባቡ መያዝ ትልቅ ብልህነት ነው ፤ አዋቂ ከሚያስብሉ መንገዶችም ዋናው እና አንደኛው በዚህ በመከራ በደስታ ጊዜን አብሮ መሆን ነው ብዬ አምናለሁ ።
ጓአደኛዬም መከታ ሁኖ እንደ ወንድም ወገቡን አስሮ እንደ ሚዜ ወጌን ሊያሳየኝ ከእኔ በላይ ደክሞ ነው ውጥናችን የተሳካው። የአህላምን ወንድም ጉልበት ስሜ የአክስቶቿን ምርቃት ተቀብዬ አህላም ወደ አለችበት ክፍል አመራሁ ።
የእኔ ውብ ከጨርቃ በላይ ደምቃ በነጭ ቬሎዋ አሸብርቃ የእኔን መምጣት ትጠባበቃለች ፤ ብርሃን ፈነጠቀልኝ ገና እስከዛሬ ድረስ ተደብቆኝ የነበረው ጀምበሬ ወጣ ህልሜም ተፈታ ።
ሰዎች ስለእርሷ ቢጠይቁኝ መልሴ ብዙ ነው ፤ እርሷን በምን አየሀት ተመኘኃት ቢሉኝ በቤተሰቧ እንደምትወደድ ፣ ሰው አክባሪ ናት ብዬ ለመመስከር ከእኔ ቀድሞ የሚገኝ ያለ አይመስለኝም ።
ግንባሯን ስሜ ፣ የቃልኪዳን ቀለበቷን አስሬ ወደቤታችን በደስታ ተመለስን የእውነት መንገድ ተጀምረ ፤ የትዳር ጐጆአችን ተቀለስ ደስ የሚሉ ሁለት ዓመታት በፍቅር አለፉ።
በትዳር ህይወታችን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በፍቅርና በደስታ አልፈዋል ፤ 2ተኛ ዓመት ላይ ከባድ የህይወት ፈተና አጋጠመን ማሚ በጠና ታማ አረፈች የሱቅ ስራ እየተበላሸ መጣ።
"በትካዜ እና በጭንቀት ኳተንኩኝ ፤ አህላምዬ ከምን ጊዜውም በላይ የሚስትነት ፍቅሯን እየቸረቸ ታበረታኝ እኔ አለሁህ ትለኝ ነበር።
በመኃከላችን ልጅ ባለመኖሩ ቢከፋኝም አንድም ቀን ሂደን ችግራችንን እንመርመር ብያት አላውቅም ፤ አንድ ቀን ግን አህላምዬ ቤት ስገባ ጠብቃ ሰዒዲዬ ዛሬ ማውራት ያለብን ነገር አለ ብላ ጠራችኝ ፤ ያ ሁልግዜም እንደ ፀሀይ ፈክቶ የሚታየው ፈገግታዋ ዛሬ ደፍርሷል ፣ ውብ አይኖቿ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይታይባቸዋል ፤ ቢሆንም ግን ፍቅሯ ከመቀነስ ይልቅ ጨምሮ ሁሌም ድካሜን ማቅለያ ጭንቀቴን መርሻ ሁና ደስተኛ አድርጋኛለች።
ሰዒድዬ " የኔ ውድ ባል ማሚ ከሞተች ቡኃላ ተስፋ የመቁረጥ ነገር እያየሁብህ ነው ፤ አንተ እኮ ጠንከራ እና የመከራ አለት የማይፈረካክስህ ለሰዎች የችግር አቅላይ ሰው ነበርክ ፤
ታድያ ዛሬ ያ ወኔህ ያ አልረታም ባይነትህ የት ገባ የመኖሬ ምክንያት ፣ የህይወቴ አጋሬ ፣ የእህቴ ምትክ ሁነህ ለእዚህ አብቅተህኝ ዛሬ ግን ያ ከማንም በላይ የምወደው እና የማውቀው ባሌ አልመስል ብለህኝ ሳዝን እና ስከፋ ቆይቻለው።
የኔ ውድ በደረሰብህ ሀዘን ይሄ ሁሉ ጊዜ መብከንከኑን ተወት አድርግና ኃይልህ ሳይባክን ለትላልቅ እንደዚሁም ዋጋቸው ከፍ ላለ ጉዳዮች ቆጥበው ፤ የሚያዳክምህ ከፊት ለፊትህ የተገተረው ግዙፍ ተራራ ሳይኾን ጫማህ ውስጥ የተሰነቀሩ ደቃቅ ጠጠሮች ናቸው ፤ የኔ ፍቅር በጊዜ ውስጥ ትናንት የትዝታ ፣ ነገ ደግሞ የተስፋ ጎተራ ናቸው ፤ ካመለጠ ትናንት....ያልመጣ ነገ ይሻላል ፤ በእጅ ያለ ዛሬ ግን ከሁሉም ይበልጣል። ዛሬ ሁሌም ያለ እየመሰለ የማይደገም ተመልሶ የማይመጣ ለአንድ አፍታ ለቅፅበት ታይቶ ዳርቻ ከሌለው የዘላለም ጠፈር ገብቶ የሚሰወር በትናንትና እና በነገ መኃል የተሰነቀረ ዕንቁ ነው። የዛሬ ሚስጢሩ እና ጉልበቱ ያለው ደግሞ "አሁን" ነው። "ቅድም" እና "ቡኃላ" ግን ያለ ቦታቸው ዛሬ ውስጥ የተደነቀሩ የትናንትና እና የነገ ሽርፍራፊዎች ናቸው። ካመለጠ ትናንት ያልመጣ ነገ ይሻላል ፤ በእጅ ያለ ዛሬ ግን ከሁሉም ይበልጣል። ውዴ ነገአችንን እናስተካክለን ዛሬያችን እናሳምር ዳግም ጠንክረን ወደ ስራ እንመለስ።
ሌላው ደግሞ ውዴ እየፈራንም ያላወራንበት የልጅ ጉዳይ ብናነሳው ጥሩ ነው ፤ ልጅ እንደምትወድ አውቃለው ሀዘንህም የዚህን ያህል የበረታው ማሚ የአንተን ልጅ ሳታይ መሞቷም ጭምር ነው ፤ የኔ ውድ ምን ትላለህ ነገ ሂደን ብንመረመር አለችኝ። አዎ ልጅ እወዳለው ግን የአህላምዬ ይበልጣል ፤ መንገድ ላይ ያገኝችው ልጅ ሁሉ የእርሷ እየመሰላት አቅፋ ትስማለች ወደእኔ ዞር ብላ እንደዚህ ቆንጆ ልጅ እንወልዳለና? ስትለኝ ሁሌም ፈገግ ብዬ በሚገባ ነበር ምላት።
አሁን ግን ሁለት ዓመት አልፎን ወደ ሶስተኛ ዓመት ልንሸጋገር ጥቂት ነው የቀረን ፤ እኔም በሀሳቧ ተስማምቼ እሺ ብያት መሽቶ ስለነበር ወደ መኝታችን አመራን። አይነጋ የለ ነግቶ በቀጠሮዋችን መሰረት ወደ ሀኪም ቤት ለመሄድ መንገድ ጀመርን።
የእኔ ህይወት ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ዳክሯል ፤ ያሳለፍኳቸውን አስቀያሚ የህይወት ጉዞዎቼን ያኖርኩባት ትንሿ ዲያሪዬ የበዛ ሀዘን እርሷ ላይ ከመፃፏ የተነሳ ያለ ገደብ ባለቀሰች ምኞቷ ነበር። ሀበሻ የሀዘን ታሪክ ይወዳል ሀዘኔን በመፅሀፍ ላሳትመው እንዴ እያልኩ ለሳቅ የማይሆን ቀልድ መቀለድ ከጀመርኩኝ ሰነባብቻለው ፤ ድንገት አንዳች ድምፅ ከሄድኩበት ሀሳብ መለሰኝ። አንድ ልቡ ጠርቶ ልብሱ የጎደፈው ፣ እጁ ላይ ማንም ሊያያቸው የማይፈቅዳቸው ሁለት ፎቶዎች በደረቱ ይዞ "ሴት አላምንም፣ሴት አላምንም" እያለ መንገድ ላይ የሚበጠብጥ ወጣት ከንቱ ከሆነው ቀልዴ አባነነኝ። ከእርሱ ድምፁ ጋር ህፃናቶችም "ሴት አላምንም መጣህ እያሉ ያበሽቁታል" ፎቶዎቹ ግን እነዛ ፎቶዎች ውስጥ ማን እንዳለ ማወቅ ፈለግኩኝ ረዝም ሰአት ሃሳቤን ወሰደው ከቅርብ ርቀት ላይ ስለ ነበር ለማየት አልተቸገርኩም ደነገጥኩኝ ከመቼው በላይ የማይረሳኝ የፊት ገፅታ ግን እንደዚህ እንዴት ሆነ አዎ እራሱ ነው....
ይቀጥላል.... 17
@fonkabcha1
@fonkabcha1
211 viewsPassenger, 12:37