Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​ | ፍቅር እና ጠበሳ

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​


አለሁኝ_በደህና

በዕውቀቱ ሥዩም
.
አንቺ እንደምን አለሽ
… እኔ አለሁ በደህና
ይመስገን ዳመና
በገበሬው አጥንት – መሬቴን እያረስኩ
በገበሬው እንባ – ማሳ እያረሰረስኩ
እንጀራ ቢጠፋ – ገበሬ እየጎረስኩ።
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና
.
ሰው ሲያፈርስ እያየሁ
ሰው ሆኖ ቡልዶዘር
አንዱ ጭጋ ነገር ሌላው የብረት ዘር
በፈረሰ ሰው ላይ በቆመ ሰገነት
ሲዖል አናቱ ላይ በታነፀ ገነት
ይኽን ኑሮ ብለው ጥቂቶች ሲኖሩ
…ያለምንም ፀፀት
…ያለምንም ሃፍረት
ይህንን እያየሁ በታላቅ ፅሞና
ኣለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና።
በምቾት መዲና
የነዳያን ትዝብት እንደ ሀሩር ልፎኝ
በጠዳ ጎዳና ለማኝ ብላቴና
እንደ ጉቶ አንዳቅፎኝ
ሃፍረት እንደ ዝናር ከፊት ከኋላ ኣቅፎኝ
ልክ እንደ ደባሎች ለመኖር እያቀድሁ
በጌቶች መሶብ ላይ እጀን እየሰደድሁ።
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና
.
ወይ በሩን አሳዪን ወይ ጠቁሚን መላ
መዓበል ሲቃረብ ያመልጣል ሽመላ
በነፋስ ገፅ ፊት ይሸሻል ዳመና
የኔ ሃዘን ያለበት ያ’ገሬ ሰው ግና
በስጋ ደም አጥንት የተሰራ ይመስል
እንደ ኮንሶ ሃውልት የመቃብር ምስል
አይሸሽ አያባርር ወይ አይተነፍስ ቃል
እንጨት ሆኖ ቆሞ ሰደድ ይጠብቃል።
.
ይህንን እያየሁ ሁኘ በጥሞና
አለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና
አንቺ ግን አለሽ ወይ እኔ አለሁ በደህና
ኣለሁ ግርምት ኖሮኝ
ምላሱን በምላጭ እንደተሰለበ
............የማስበው ኖሮኝ
.................የምለው ቸግሮኝ ።


@fonkabcha1
@fonkabcha1