Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​​​​​​​​​ ሴትን አላምንም ክፍል 19 ፀሀፊ ሱ | ፍቅር እና ጠበሳ

​​​​​​​​​​​​​​​​​​


ሴትን አላምንም

ክፍል 19

ፀሀፊ ሱለይማን መሀመድ


የሰማሁት ድምፅ አስደንግጦኝ የሳሎኑን በር በኃይል ከፍቼው ስገባ ያየሁት ነገር አረጋጋኝ ፤  አህላምዬ የመኝታ በሩን ባላት ጉልበት መታው ስለነበረ ነው ያ ከፍተኛ ድምፅ የተሰማው ፤ መኝታ ክፍል ገብቼ ላረጋጋት ብሞክርም  መረጋጋት አልቻለችም ከባድ ፈተና እንደተጋረጠብኝ ታወቀኝ። እርሷን ትቼ ወደ ሳሎን ተመለስኩኝ ፤ ተስፋ ቆረጥኩኝ ወገግታው ሲጨልም ብርሃን ከእኔ ሲሸሽ ታየኝ ፤ የመኖሬ ምክንያት የሆነችው አህላም ዛሬ ከፍቷታል ፤ የሚያፅናናኝ  የለም ምክሯ ሁሌም ተስፋ የሚሆነኝ ሚስቴ ዛሬ ምክርን መቀበል አዳግቷት ትራሷን ታቅፋ እያለቀሰች ነው ፤ አህላምዬ ባላጠፋችው ጥፋት እራሷን እየቀጣች እንደሆነ ቢገባኝም ካለችበት ሀዘን ልመልሳት አልቻልኩም ፤ አሁን የመከራና ናዳ ሊወርድብኝ እንደሆነ ታወቀኝ። የእኔ የምላቸውን ሁሉ አጥቼ አህላምዬ ነበር የቀረችው ፤ የሁሉ ምትክና የእናቴ አደራ የሆነችው ሚስቴ ዛሬ ተረታለች ፤ ሰማዩ ሲጠቁር ፣ የህይወቴ ነጐድጓድ ሲያጓራ ፣ መከራዬ ሲያጉረመርም ፣ የዘመን ህመሜ ሲነሳ ተሰማኝ ። ውሀ እየጠጣሁኝ ውሀ ጠማኝ  ፣ የሰማዩ ባህር ቁልቁል የተናደብን መሰለኝ፣ ያንዘፈዝፈኝና መለስ ብሎ ደግሞ ያቃጥለኛል ፣ ከአጠገቤ ብን ብላ ስትጠፋ ታወቀኝ ፤ "አበደ ሰዒድ አበደ! ብለው ሰዎች የከበቡኝ መሰለኝ ፤ ዛሬ ሁሉም የሉም እናቴም የለችም።  

ካሂሊል ጂብራን አልኩኝ በውስጤ ስለ እናት የተናገረው ትዝ ብሎኝ

በሰው ልጆች ከሚጠሩት ቃላት ሁሉ እጅግ የተዋበ ቃል "እናት" የሚለው ቃል ነው። እጅግ ቆንጆ አጠራርም "እናቴ" የሚለው ነው። በተስፋ እና በፍቅር የተሞላ፣ ከልብ የሚመነጭ ፣ ጣፋጭ እና መልካም ቃል ነው። እናት ሁሉንም ነገር ናት በሃዘን ጊዜ መፅናኛችን፣ በስቃይ ጊዜ ተስፋችን፣ በደከምን ጊዜ ጥንካሬያችን ናት። የፍቅር ፣ የምህረት ፣ የርህራሄ እና የይቅር ባይነት ምንጭ ናት ፤ እናቱን ያጣ ያለ ማቋረጥ የምትባርከውና የምትጠብቀውን ንፁህ ነፍስ አጥቷል ፤ አዎ ዛሬ ምንጬ በደንብ ደርቆ አቧራ መልበሱ ታወቀኝ።


መሀመድ ውጪ ቆይቶ መጣ ፤ ለረዥም ደቂቃ ፀጥ ብሎ አጠገቤ ተቀመጠ ፤ ተነስቶ አህላምዬ ጋር ሄደ አሁንም እያለቀሰች ነው።

ምን ይሻላል ? አለ ረጋ ባለ ድምፅ

እኔ እንጃ ማሜ አላውቅም

ያ ጠንካራ መንፈሴ ተረታ ፤  ጓደኛዬ ምን ይሻላል አትበለኝ የሚሻለውን ምረጥ እና አድርግ ፤ ስለምን ላስብ ሀዘኗ ልቤን ይጎዳዋል ፣ ለቅሶዋ ህልሜን ያበላሸዋል ፣ በመንገዴ ሁሉ እርሷ አለች ዛሬ ግን እንዳየሗት ሁናለች ፤ ማሜ እባክህን ዕርዳኝ አልኩት።

እየፈራ እየቸረ ቤተሰቦቿ ጋር ለጥቂት ጊዜ ትሂድ ያለው አማራጭ ይህ ነው አለኝ ። ከእህቶቿ የአንደኛዋን ስልክ ስጠኝ እና እናናግራት እና ትምጣ ፤ ያለውን ነገር እናስረዳት አሁን ያለን አማራጭ ይህ ነው ፤ ሰዒድ ያሉብህ ዕዳዎች ከአቅም በላይ ሁነዋል ብዙ ቼኮች የሰዎች እጅ ላይ አለ ፤ አህላም ስራ መበላሸቱን እንጂ ይህንን ሁሉ አታውቅም ፤ ስለዚህ ለትንሽ ጊዜ ከዚህ ትራቅ ማስተካከል ያለብን እናስተካክል አለኝ፤ እኔም እየከበደኝም ቢሆን በሀሳቡ ተስማማሁኝ። እህቷ ጋር ተደወለ እቺኛዋ የሞተችዋ ታላቅ ነች ነገሮችን በእርጋታ ማየት የምትወድና ቅን ልብ ያላት ሴት ነች ፤ "ሐያት" ከመሀመድ ጋር ተደዋወውለው ያለውን ነገር አውርተው መጣች ፤ መሽቶ ስለ ነበር እዚሁ አድርው ነገ መሄድ እንዳለባት ተስማማን ፤ እነሱ ያወራሉ እንጂ እኔ አቅም አጥቻለው ፤ በራሴ ሕይወት ላይ ሀሳብ መስጠት ተስኖኛል ፤ አህላም ለአንድ ደቂቃም ሳታየኝ ነጋ ፤ ማሜ በጠዋት መጥቶ ስለነበር ከእህቷ ጋር አህላምን አነጋገሯት ፤ "አህላምም" ትንሽ እየደከማት ስለነበር በሀሳበቸው ተስማማች ፤ ሀዘኑ በአንድ ቀን ጎድቷታል ፤ መሀመድ እና ሐያት ቀድመው ከቤት ወጥተው እኔና እርሷ ብቻ ቀረን። ተነፋፍቆ እንደተገናኝ ሰው አቅፈችኝ የኔ ውድ? " ህልምህን አጨለምኩብህ ፣ ተስፋህን ሰረቅኩህ ፣ እባክህ ይቅር በለኝ እባክህ" ለቅሶዋን  ማየት ከበደኝ።

አህላምዬ

"አንቺ ፈልገሽ ያደረግሽው ምንም ነገር የለም ፤ ይህ የአላህ ውሳኔና ፍቃድ ነው ፤ አላህ ለምን እንዲህ አደረግክ የማይባል ጌታ በፍጡራኑ ላይ ምንም ነገር የሚያደርግ ጌታ ነው ፤ አንቺ ብቻ ሳትሆኚ ብዙዎቹ የእዚህ ችግር ሰለባ ናቸው ፤ እኔ ደግሞ አንቺን ብዬ እንጂ ለልጅ ብዬ አላገባሁም ፤ ከምንም በፊት አንቺ ትቀድሚያለሽ ፤ ደግሞ እወቂ አላህ ያሻውን የሚሰራ ጌታ ነው "ለነብዩላህ ዘከርያ በእስተርጅና ልጅን የሰጠ ፣ ነብዩላህ አዩብን ከዛ ከመከራ ፣ ከበሽታ እና ከድህነት ሕይወት ዳግም ወደ አዲስ ሕይወት የመለሰ ጌታ ነው። ስለእኛ ከእኛ በላይ አላህ ያውቃል ፤ ለትንሽ ቀን ቤት ሂጅና ተረጋጊ ፤ እኔ ሁሌም የአንቺው ነኝ ብዬ ግንባሯን ስሜ ሸኘሗት።

እሷን ሸኝቼ ትንሽ ህመም እና የድካም ስሜት ሲታየኝ ሆስፒታል ሄድኩኝ ፤ ሆስፒታሉ በር ላይ እናቱን እና እህቱነሸ በሞት የተነጠቀው  ያ ወጣት ቆሞዋል።  ዛሬ ምርር ብሎ ነው የሚናገረው "ሴትን አላምንም አዎ ሴትን አላምንም" ፤ እንኳን ሴት እናታችሁን አትመኑ አለሁልህ ብላ ጥላኝ ሄደች ፣ መጣሁኝ ብላ ለዘለዓለሙ ተለየችኝ ፣ ብቻዬን አስቀረችኝ ፣ ሴትን አትመኑ ፤ እህቴም ሴት ነበረች ሁሌም የአንተው ነኝ  እንዳላለችኝ ዋሽታኝ ሄደች ፣ ጠብቀኝ ደርሻለው ብላ ቀረች ታድያ ማንን ልመን እኮ ሴትን ? የታለ ቆሜ እድርሀለው ልጅህን ተንከባክቤ አሳድግልሀለው ብለው ቃል የገቡልኝ?  የታለች የሰርግህ ቀን የሸሚዝህን ቁልፍ  ከእኔ ውጪ ማንም አይቆልፍልህም ብላ ቃል የገባችዋ እህቴ? ቃልዋን አፍርሳለች ! ለምን ሴትን አምናለው የታለች እናቴ ፣ የታለች እህቴ?

 አዎ! አምናችሁ እዚህ አትግቡ እዚህ የገባ አይወጣም ፤ እናቴ መናኸርያ ቀጥራኝ እዚህ ነበር ያገኝሗት ፤ እዚህ ምን አለ ? እዚህ እኮ ህልምን በሳጥን አድርገው የሚሰጡ ሰዎች ናቸው ያሉት እያለ ይጮሀል ፤ የተሰበሰበው ሰው በሀዘን ዳር ቁሞ ይመለከተዋል ፤ አዎ አላምንም እናንተም አትመኑ እያለ ሄደ ፤ እኔም ስለ ወጣቱ ንግግር እያሰብኩኝ ወደ ውስጥ ገብቼ ህክምናዬ ጨርሼ ወጣሁኝ።

አህላምዬን በስልክ እያገኝሗት ሁለት ቀን አለፈ ፤ ድምፇ ብዙም ደስ የሚል ስሜት የለውም ሀዘኑ ይሆናል ብዬ አስብያለው ፤ እኔም ቼክ የሰጠሗቸው ሰዎች እንዲታገሱኝ ከማሜ ጋር አብረን እየሄድኩኝ ተማፅኖዬን ቀጥያለው።

ቢሆንም አህላም ከሄደች ቡኃላ  በስቃይ ላይ ስቃይ በህመም ላይ ህመም ተደራርቦ የልቤን ቁስል አመረቀዘው ፤ ተደብቄ ስለ እናቴ እያለቀስኩ ያሳለፍኩት የመከራ ጊዜ ዳግም ተመልሶ መጣብኝ ፤ አህላምዬ እናቷ ቤት መሄዷን ሳስብ ዓለም የሸሸኝ መሰለኝ ፤ ውስጤ እያለቀሰ ልቤ እየደማ ቀናቶች አለፉ ፤ ዛሬ በጣም ናፍቃኛለች ሀዘኔን እንዳታየው መጨነቄን እንዳትረዳ ነበር እስካሁን ቤትም ሄጄ ያልዘየርኳት ፤ ባለ መምጣቴ ቅር ቢላትም ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም ፤ ስራዬ ከተበላሸ ቡኃላ ቤተሰቦቿ ጋር መሄድ ከባድ ሁኖብኝ ነበር ፤ ወንድሟም የሰው ብር እንዳለብኝ ከሆኑ ሰዎች ሰምቶ ስለነበር የበፊት ፍቅሩ ዛሬ ላይ የለም ፤ ዛሬ ግን ላገኛት መሄድ አለብኝ ስልኬን አውጥቼ ስደውል አይነሳም ደጋግሜ ሞከርኩት ከብዙ ጥሪ ቡኃላ ስልኩ ተነሳ

ሄሎ አልኩኝ ተቻኩዬ

ክፍል ሀያ ይቀጥላል
@fonkabcha1
@fonkabcha1