Get Mystery Box with random crypto!

ጥበብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ filsifina000 — ጥበብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ filsifina000 — ጥበብ
የሰርጥ አድራሻ: @filsifina000
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.48K
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዪ ሀሳቦች ይቀርባሉ

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 16:06:23 የተከታይ ዕጣ
(ደሱ ፍቅርኤል)

ድር ሆና አገኘኃት
ሸረሪት ሆንኩና አጠመድኩ ራቴን
እሾህ ሆና መጣች
አጣሪ ሆንኩና አስከበርኩ ርስቴን
ቆሻሻ ነኝ አለች - ዝምብ ሆኜ ቀረብኳት
አበባ ነኝ ብትል - ንብ ነኝ ብዬ ሳምኳት
ይሄን ሆንኩኝ ስትል - ያን ሆኜ ሳሳዳት
በመላ ስትርቀኝ - በዘዴ ሳጠምዳት
ይኸው ብሎ ብሎ...
አውላላ ላይ ጣለኝ የመከተል ሱሴ
እሷን ሊያጠምድ ወጥቶ - ጠፋብኝ ራሴ
Join

@filsifina000
129 views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:05:16 ምን አይነት ህዝብ ነህ?
(ደሱ ፍቅርኤል)

ከጥንት አይቻለሁ የወደዱህ ሁሉ ወድቀዋል ከፊትህ
ፍቅርህን ለሚሉ ሞት ነው ሽልማትህ
ምን አይነት ህዝብ ነህ?
እኔ እወድሃለሁ
መውደዴን እንዳልገልፅ - ግን እፈራሃለሁ
ሲያከብሩህ አታከብር ሲወዱህ አትወድም
ጠላሁህ ለሚሉህ ለሚበድሉህ ነው የምታገለድም
ጨለማ ሲውጥህ
የትም ሲዘርርህ ህይዎት እንደ ፈንግል
ቅድስት ሀገር እያልክ ራስህን ሸንግል
የህልመኛ ሾተላይ
የእውር-ድንብስ ተጓዥ የባዶነት መንጋ
ፀሀይ እያጠፋህ
ጨረቃ እየጋረድክ እንዴት ብሎ ይንጋ?
ኢትዮጵያ ሀገሬ
ቅድስት ናት ብሎ ማነው ያዘናጋሽ?
እርጉም ነሽ እወቂው
ሞት ለመለመን ነው አክናድ የዘረጋሽ!
ባዶ
ባዶ
ባዶ
ህልሜ ሁሉ ባዶ
ፍቅሬ ሁሉ ባዶ
ሰው እንዴት ተስፋ ያርግ
በሾተላይ አገር ህልም ይዞ ተወልዶ?
ከስህተትም ስህተት ከመርገምም መርገም
በተስፋቢስ መሬት በተስፋ መፍገምገም!
ምን አይነት ህዝብ ነህ ተርመስማሽ ግትልትል
የወደቁልህን ለመብላት መጣደፍ እንደ መቃብር ትል!
እስከመቼ ድረስ ህልመኛ ይቀርጠፍ?
እስከመቼስ ድረስ
አንቺን የወደደ በአበባው ይቀጠፍ?
ልንገርሽ ሀገሬ እኔ እወድሻለሁ
መውደዴን እንዳልገልፅ ግን እፈራሻለሁ
አንቺን የወደዱ ሲዋረዱ አውቃለሁ
ሲሞቱ አይቻለሁ
እይው እስኪ ሀገሬ
ህልም አጨናጋፊው ደረት እየነፋ ህልመኛ ይሰጋል
ልፋ ቢለው እንጅ
በተስፋቢስ ሀገር ነገ በሌለበት ህልም ምን ያደርጋል?
132 views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 07:55:29 ደራሲ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
ፀሀፊው በታዘባቸው ነገሮች ላይ የሰላ ትችቱን ፅፎታል ።

join and share
@filsifina000
@filsifina000
1.3K viewsedited  04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 07:55:06 ደራሲ ህንዳዊው ራጅነሽ ወይም በሌላ ስሙ ኦሾ

የፍልስፍና መፅሀፍ ሲሆን ነገሮችን እኛ ከምናስበው ወጣ ባለ መንገድ ያብራራል። በተለይም ሀይማኖትን በተመለከተ በሰፊው ተፅፏል ።

join and share
@filsifina000
1.2K viewsedited  04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 20:05:55 #ዕድሌ_ነው...

ዕድሌ ነው...
በሚስት ልወሰን፣ እኔ ትዳር ሲያምረኝ፤
ሳታገባ 'ምትቆይ፣ አንድም ሴት አትገኝ
ዕድሌ ነው...
እኔ ዲግሪ ስይዝ፣ ዲግሪ ዋጋ ያጣል፤
ገንዘብ ያለው ሁሉ፣ ዶክትሬት ያመጣል
ዕድሌ ነው...
እኔ መድረክ ስይዝ፣ ይፈታል ጉባኤ፤
እኔ መጾም ሲያምረኝ፣ ይሆናል ትንሣኤ።
ዕድሌ ነው...
በቁርባን ለመኖር፣ ንሰሐ ስገባ፤
አቁራቢው ፖትልኮ፣ ቤተመንግሥት ገባ።
ዕድሌ ነው...
እኔ ኳስ ስገዛ፣ ሜዳው ይታረሳል፤
እኔ ቤት ሲኖረኝ፣ ሰፈሬ ይፈርሳል።
ዕድሌ ነው...
ለተሾመ ሁሉ፣ እንዳልኖርሁ ስለፋ፤
እኔ አለቃ ስሆን፣ የሚታዘዝ ጠፋ።
ዕድሌ ነውና...
ከዕለታት አንድ ቀን፣ መንገሤ ባይቀርም፤
እኔ ንጉሥ ስሆን፣ ሀገሪቱ አትኖርም።

* * * *
#ገጣሚ_መላኩ_አላምረው

@filsifina000
@filsifina000
@filsifina000
1.1K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 19:18:00
884 views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:01:39 # የተወለድከው ነፃነት ራስህን ሆነህ ነው። ዳሩ ግን አስተዳደግህ ይህን ያስረሳሀል።

ከአንድ ነገር ነፃ መሆን ትክክለኛ ነፃነት አይደለም። የፈለከውን ነገር የማድረግ ነፃነትም እኔ የምለው ዓይነት ነፃነት አይደለም። የእኔ ነፃነት ራዕይ ራስህን እንድትሆን ነው።

ነፃነትን ከአንድ ነገር የማግኘት ጥያቄ አይደለም። ይህ ነፃነት አይባልም ፣ ምክንያቱም የተሰጠህ ነፃነት ነው። ነፃነቱን ያገኘኸው በአንድ ነገር ምክንያት ነው። ጥገኝነት እንዲሰማህ የሚያደርግህ ነገር አሁንም በነፃነትህ ውስጥ ይገኛል። ለዚያ ነገር ግዴታ አለብህ። ያለዚህ ነገር ነፃነትህን አታገኘም።
የምትፈልገውን ነገር የማድረግ ነፃነትም ነፃነት አይባልም፣ ምክንያቱም አንድን ነገር "ለማድረግ "መፈለግ የሚመነጨው ከህሊናህ ነው። የህሊና ደግሞ ባሪያ ነህ።

ትክክለኛ ነፃነት የሚመጣው ምርጫ ከሌለው እውቀት ነው። ዳሩ ግን ምርጫ የሌለው እውቀት ሲኖር የምናገኘው ነፃነት በነገሮች ላይ ጥገኛ የሆነ አይደለም ፣አንድን ነገር በማድረግ ላይም ጥገኛ አይደለም። ምርጫ አልባ እውቀትን ተከትሎ የሚመጣው ነፃነት ራስን መሆን ብቻ ነው።
አንተ ደግሞ አንተን ሆነህ ተወልደሀል፣ስለዚህም ይህ ነፃነት በምንም ነገር ላይ ጥገኛ አይደለም። ማንም ሊሰጥህ ወይንም ሊወስድብህ አይችልም። ሰይፍ አንገትህን ሊቆርጠው ቢችልም ነፃነትህን ማለትም ማንነትህን ሊወስድብህ አይችልም።
በሌላ መልኩ ለመናገር ፣የአንተ መሠረት ፣መካከል ወይንም ስር የሚገኘው ከተፈጥሯዊ ፣ የህልውናዊነት ማንነትህ ውስጥ ነው። ከውጫዊው ዓለም ጋር የሚገኘው ነገር የለም።

ከነገሮች መቀላቀል ወይንም ነፃ መሆን በመጪው ዓለም ላይ ጥገኛ ነው። አንድን ነገር የማድረግ ነፃነትም ውጫዊውን ዓለም መሠረት ያደረገ ነው። ፍፁም ንፁህ የመሆን ከውጪው ዓለም ጋር ጥገኛ መሆን የለበትም።
# የተወለድከው ነፃነት ራስህን ሆነህ ነው። ዳሩ ግን አስተዳደግህ ይህን ያስረሳሀል።
ነፃነት ከሕይወት ስጦታዎች ሁሉ የላቀች ናት። በነፃነት የተነሳም በውስጤህ ብዙ አበቦች ይፈካሉ።

# የነፃነት አበባ ሲፈካ ፍቅር ውይም ርህራሔ ይሆናል። በሕይወት ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ሁሉ በንፁህ ተፈጥሯዊ ማንነትህ ውስጥ አብቦ ይጎመራል።

ስለዚህ ነፃነትን ከጥገኝነት ጋር ከመላቀቅ ጋር አቆራኘው። ከጥገኝነት መላቀቅ ከሰው ወይንም ከአንድ ነገር ጋር የተገናኘ ነው። ነፃነትን ማድረግ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ከማድረግ ጋር አታገናኘው። ምክንያቱም ይህ ህሊና እንጂ አንተ አይደለህም። አንድ ነገር ለማድረግ መፈለግ ወይም መሻትህ በፍላጎትህ ወይንም በመሻትህ ባርነት ቀንበር ይከትሀል። እኔ የማወራልህ ነፃነት፣ ነፃነትን ራሱን ነህ እያልኩ ነው። በፍጹም ፀጥታ ርጋታና ፍፁም ሀሴት።
ከጣመን እንቀጥላለን!!
# ኦሾ/OSHO
977 views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 18:36:29 ሳቅ ሲበዛ የሐዘንን ያህል እንምባ ያስፈስሳል፤መቀመጥ ሲበዛ የመስራትን ያህል ያደክማል፤ደግነት ሲበዛም እንዲሁ የክፋትን ያህል ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም።
.
.
.
ሁሉን ነገር በመጠን ከያዙት ግን እንኳንስ መልካሙ ክፋውም ይጠቅማል ።

#ከበደ_ሚካኤል

Join and share
@filsifina000
@filsifina000
@filsifina000
990 views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 06:59:44 አንግዲህ ይህ ሃሳብ ነው የኢትዮጵያ ችግር መፈቻ ቁልፍ ሆኖ በአለማያው ገላገይ፣ በዚህ መጽሐፍ ዘንድ የቀረበው። መጽሐፉ ሙሉውን አጥፍተን ከዜሮ እንጀምር አይነት አቀራረብ ያለው፣ አለምን በጠባብ መነጸር ያየ ነው። ስራን (ባርነትን) የድህነት መውጫ መንገዶ አድርጎ ገልጾ ግን ያለውን መንፈሳዊ እውቀት ይጥፋ ይለናል፣ የሚተካውን የእውቀት መንገድ ግን አላሳየንም። የችግሩን መንስኤዎች በሙሉው የሚያሳይም አይደለም። እናም መፍትሔ ጠቋሚ አይደለም። ጥሩ ጥያቄ፣ የመፍትሔው መንገድ ግን የጎደለና በሾርኔ አይቶ ወይም ሳያይ ያለፈ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ችግርን በቃላት ድርድራ አንፈታውም። ትክክለኛውን የሃሳብ መንገድ አላገኘውም እያልኩ ነው። ችግራችን የምንፈታው፣ በዚህ አይነት የመንስኤ-ውጤት ግንኙነትን በሚያጣርስ፣ ሁሉ ይጥፋ ከዜሮ እንጀምር በሚል ሃሳብ አይደለም። የችግራችን መንስኤዎች ብዙ መሆናቸውን መለየት፣ መፍትሔም ከዚህ አንፃር መፈለግን ይጠይቃል። እናም ስንጽፍ ብቻ ሳይሆን አስተያየት ስንረጥም ይህን ያገናዘበ መሆን አለበት። ከመጽሐፉም፣ ከውይይቱም ግን ይህን አላየሁም። ከዜሮ መጀመር መፍትሄ አይደለም። መፍትሄው ያለንን ጥሩ፣ ከመጥፎው መለየት። የጎደለውን ከአለም ዘንድ መፈለግና ለእኛ ችግር መፍቻ በሚሆን መንገድ መቅረጽ፣ ሁለቱን ለንቅጦና የእኛ አድርጎ መጠቀም ነው። ይጥፋ አብዮት ወይም ኒሂልስም ነው፣ ጥፋት። ከጥፋትም ልማት አይገኝም።

የተጠላው እንዳልተጠላ
አለማየሁ ገላጋይ
927 viewsedited  03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 06:59:44 ኒሂሊዝም (Nihilism) የተባለው ፍልስፍና መሰረቱ፣ ጥቅሙስ ምንድን ነው?
---
ኒሂሊዝም የሚባለው ፍልስፍና በአውሮፓ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳ ርዕዮትነው። ኒሂሊዝም እንደሚገለፅበት አውድ እና ዲሲፕሊን የተለያዩ መልኮች ቢኖሩትም ማጠንጠኛው “ክህደት” ሲሆን ሃይማኖት፣ ዕምነት፣ ባህል፣ እውቀት፣ ሕግ፣ ሥነ ምግባር ወዘተ በጠቅላላው በኒሂሊዝም ይካዳሉ። ኒሂሊዝም መሠረቱ ጥርጥር (skepticism) ነው። ጥርጥር ዓላማው ውሸትን ለይቶ እውነት ጋር መድረስ ነው። ጥርጥር ግን በወለደችው ኒሂሊዝም የተሰኘ ልጅ ዓላማዋንም ትርጉሟንም አጥታ እየሞተች ነው። ጥርጣሬ ጫፍ ሲይዝ እና ጨለምተኛነት የሚባል ቅመም ተጨምሮበት ሲበስል ኒሂሊዝምን ይወልዳል። ኒሂሊዝም ሁሉንም ነገር ያለምህረት መካድ ነው። በኔ በኩል ጥቅም አለው ብዬ አላስብም። የአብዘርድ አቀንቃኙ ካሙ እንኩዋን፣ እውነት ነው ህይወት ትርጉም የላትም፣ ግን ትርጉም የላትም ብለን ልንተዋት አይገባም፣ ትርጉም ልንፈጥርላት ግድ ነው ይለናል።

የሰው ልጅ በማህበራዊ ኑሮ ዉስጥ ህልውናውን የሚያስጠብቅባቸው፣ ባህሉን የሚያስከብርባቸውና ለትውልድ የሚያስተላልፍባቸው፣ ዕውቀቱን የሚያሰፍርባቸው፣ ስሜቱን የሚገልጽባቸውና ሥነ-ምግባሩን የሚተረጉምባቸው እሴቶች አሉት፡፡ እነዚህ እሴቶች የሰው ልጅ የፈጠራቸው እና ለእነዚህ ዕሴቶች ተገዥ ሆኖ የሚኖርባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል አንድ ማህበረሰብ እንደ ማኅበር ራሱን የሚገልጥበትና ህላዌውን የሚያዘልቅበት ባህል አለው፡፡ ባህል ለተፈጥሮአዊ ጉዳዮች የሚሰጥ “ምላሽ” (expression) ነው፡፡ እምነት፣ ሃይማኖት፣ እውቀት፣ ሞራል፣ ልማድ፣ ህግ/መተዳደሪያ ደንብ፣ ኪነ-ጥበብ፣ ምርትና ማምረቻ መሳሪያ፣ አልባሳት፣ ወዘተ. . . የባህል ዘርፎች ናቸው፡፡ በየትኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ባህል አለ። ማህበረሰብ ለባሕል ያለው አመለካከት የተለያዬ ቢሆንም ለዕሴቶቹ እውቅናን መስጠት ብቻ ሳይሆን አስፈላጊነታቸውንም ያምናል፡፡ ነገር ግን ኒሂሊዝም እነዚህን ሰዋዊ እሴቶች ይክዳል፤ አላስፈላጊነታቸውንም ይሰብካል፡፡ መሰረት የሌላቸውና አንዳችም ጥቅም የማይሰጡ መሆናቸውን በመግለጽ በሰው ልጅ ህላዌ ውስጥ ያላቸውን ህልውና ይክዳል።

ኒሂሊዝም ሕይወት ትርጉም የለሽ እንደሆነ በማመን፣ ሁሉንም ሃይማኖታዊ እና ሥነ ምግባራዊ መርሆች አለመቀበል ነው፣ ልቅ የሆነ ነፃነት ይኑርም፣ ሁሉንም ከዜሮ እንጀምረው ይላል። የሰውን ተፈጥሯዊ ምንነት ካለማወቅ የሚመነጭ የጥፋት መንገድም ይመስላል። ሰው በcognitive evolution ያገኘውና ከሌሎች እንሰሳት የለየው ነገር ቢኖር የሌለን ነገር በ association በአዕምሮው መፍጠር መቻሉ ነው። ነገር ግን ኒሂሊስቶች በዚህ መንገድ የተፈጠረው ይጥፋና በሌላ ተጨባጭ እውነት ይተካ ይላሉ። በመጀመሪያ ይህን የማይጨበጥ እውነት እንዴት ለማጥፋት ይቻለናል? ከተቻለስ፣ ሰው እራሱ መልሱ እንደማይፈጥረው ምን እርግጠኛ አደረገን?

አንግዲህ ይህ ሃሳብ ነው የኢትዮጵያ ችግር መፈቻ ቁልፍ ሆኖ በአለማያው ገላገይ፣ በዚህ መጽሐፍ ዘንድ የቀረበው። መጽሐፉ ሙሉውን አጥፍተን ከዜሮ እንጀምር አይነት አቀራረብ ያለው፣ አለምን በጠባብ መነጸር ያየ ነው። ስራን (ባርነትን) የድህነት መውጫ መንገዶ አድርጎ ገልጾ ግን ያለውን መንፈሳዊ እውቀት ይጥፋ ይለናል፣ የሚተካውን የእውቀት መንገድ ግን አላሳየንም። የችግሩን መንስኤዎች በሙሉው የሚያሳይም አይደለም። እናም መፍትሔ ጠቋሚ አይደለም። ጥሩ ጥያቄ፣ የመፍትሔው መንገድ ግን የጎደለና በሾርኔ አይቶ ወይም ሳያይ ያለፈ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ችግርን በቃላት ድርድራ አንፈታውም። ትክክለኛውን የሃሳብ መንገድ አላገኘውም እያልኩ ነው። ችግራችን የምንፈታው፣ በዚህ አይነት የመንስኤ-ውጤት ግንኙነትን በሚያጣርስ፣ ሁሉ ይጥፋ ከዜሮ እንጀምር በሚል ሃሳብ አይደለም። የችግራችን መንስኤዎች ብዙ መሆናቸውን መለየት፣ መፍትሔም ከዚህ አንፃር መፈለግን ይጠይቃል። እናም ስንጽፍ ብቻ ሳይሆን አስተያየት ስንረጥም ይህን ያገናዘበ መሆን አለበት። ከመጽሐፉም፣ ከውይይቱም ግን ይህን አላየሁም። ከዜሮ መጀመር መፍትሄ አይደለም። መፍትሄው ያለንን ጥሩ፣ ከመጥፎው መለየት። የጎደለውን ከአለም ዘንድ መፈለግና ለእኛ ችግር መፍቻ በሚሆን መንገድ መቅረጽ፣ ሁለቱን ለንቅጦና የእኛ አድርጎ መጠቀም ነው። ይጥፋ አብዮት ወይም ኒሂልስም ነው፣ ጥፋት። ከጥፋትም ልማት አይገኝም።

አለማየሁ ገላጋይ
የተጠላው እንዳልተጠላ

ኒሂሊዝም (Nihilism) የተባለው ፍልስፍና መሰረቱ፣ ጥቅሙስ ምንድን ነው?

831 views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ