Get Mystery Box with random crypto!

# የተወለድከው ነፃነት ራስህን ሆነህ ነው። ዳሩ ግን አስተዳደግህ ይህን ያስረሳሀል። ከአንድ ነገ | ጥበብ

# የተወለድከው ነፃነት ራስህን ሆነህ ነው። ዳሩ ግን አስተዳደግህ ይህን ያስረሳሀል።

ከአንድ ነገር ነፃ መሆን ትክክለኛ ነፃነት አይደለም። የፈለከውን ነገር የማድረግ ነፃነትም እኔ የምለው ዓይነት ነፃነት አይደለም። የእኔ ነፃነት ራዕይ ራስህን እንድትሆን ነው።

ነፃነትን ከአንድ ነገር የማግኘት ጥያቄ አይደለም። ይህ ነፃነት አይባልም ፣ ምክንያቱም የተሰጠህ ነፃነት ነው። ነፃነቱን ያገኘኸው በአንድ ነገር ምክንያት ነው። ጥገኝነት እንዲሰማህ የሚያደርግህ ነገር አሁንም በነፃነትህ ውስጥ ይገኛል። ለዚያ ነገር ግዴታ አለብህ። ያለዚህ ነገር ነፃነትህን አታገኘም።
የምትፈልገውን ነገር የማድረግ ነፃነትም ነፃነት አይባልም፣ ምክንያቱም አንድን ነገር "ለማድረግ "መፈለግ የሚመነጨው ከህሊናህ ነው። የህሊና ደግሞ ባሪያ ነህ።

ትክክለኛ ነፃነት የሚመጣው ምርጫ ከሌለው እውቀት ነው። ዳሩ ግን ምርጫ የሌለው እውቀት ሲኖር የምናገኘው ነፃነት በነገሮች ላይ ጥገኛ የሆነ አይደለም ፣አንድን ነገር በማድረግ ላይም ጥገኛ አይደለም። ምርጫ አልባ እውቀትን ተከትሎ የሚመጣው ነፃነት ራስን መሆን ብቻ ነው።
አንተ ደግሞ አንተን ሆነህ ተወልደሀል፣ስለዚህም ይህ ነፃነት በምንም ነገር ላይ ጥገኛ አይደለም። ማንም ሊሰጥህ ወይንም ሊወስድብህ አይችልም። ሰይፍ አንገትህን ሊቆርጠው ቢችልም ነፃነትህን ማለትም ማንነትህን ሊወስድብህ አይችልም።
በሌላ መልኩ ለመናገር ፣የአንተ መሠረት ፣መካከል ወይንም ስር የሚገኘው ከተፈጥሯዊ ፣ የህልውናዊነት ማንነትህ ውስጥ ነው። ከውጫዊው ዓለም ጋር የሚገኘው ነገር የለም።

ከነገሮች መቀላቀል ወይንም ነፃ መሆን በመጪው ዓለም ላይ ጥገኛ ነው። አንድን ነገር የማድረግ ነፃነትም ውጫዊውን ዓለም መሠረት ያደረገ ነው። ፍፁም ንፁህ የመሆን ከውጪው ዓለም ጋር ጥገኛ መሆን የለበትም።
# የተወለድከው ነፃነት ራስህን ሆነህ ነው። ዳሩ ግን አስተዳደግህ ይህን ያስረሳሀል።
ነፃነት ከሕይወት ስጦታዎች ሁሉ የላቀች ናት። በነፃነት የተነሳም በውስጤህ ብዙ አበቦች ይፈካሉ።

# የነፃነት አበባ ሲፈካ ፍቅር ውይም ርህራሔ ይሆናል። በሕይወት ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ሁሉ በንፁህ ተፈጥሯዊ ማንነትህ ውስጥ አብቦ ይጎመራል።

ስለዚህ ነፃነትን ከጥገኝነት ጋር ከመላቀቅ ጋር አቆራኘው። ከጥገኝነት መላቀቅ ከሰው ወይንም ከአንድ ነገር ጋር የተገናኘ ነው። ነፃነትን ማድረግ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ከማድረግ ጋር አታገናኘው። ምክንያቱም ይህ ህሊና እንጂ አንተ አይደለህም። አንድ ነገር ለማድረግ መፈለግ ወይም መሻትህ በፍላጎትህ ወይንም በመሻትህ ባርነት ቀንበር ይከትሀል። እኔ የማወራልህ ነፃነት፣ ነፃነትን ራሱን ነህ እያልኩ ነው። በፍጹም ፀጥታ ርጋታና ፍፁም ሀሴት።
ከጣመን እንቀጥላለን!!
# ኦሾ/OSHO