Get Mystery Box with random crypto!

የተከታይ ዕጣ (ደሱ ፍቅርኤል) ድር ሆና አገኘኃት ሸረሪት ሆንኩና አጠመድኩ ራቴን እሾህ ሆና መጣ | ጥበብ

የተከታይ ዕጣ
(ደሱ ፍቅርኤል)

ድር ሆና አገኘኃት
ሸረሪት ሆንኩና አጠመድኩ ራቴን
እሾህ ሆና መጣች
አጣሪ ሆንኩና አስከበርኩ ርስቴን
ቆሻሻ ነኝ አለች - ዝምብ ሆኜ ቀረብኳት
አበባ ነኝ ብትል - ንብ ነኝ ብዬ ሳምኳት
ይሄን ሆንኩኝ ስትል - ያን ሆኜ ሳሳዳት
በመላ ስትርቀኝ - በዘዴ ሳጠምዳት
ይኸው ብሎ ብሎ...
አውላላ ላይ ጣለኝ የመከተል ሱሴ
እሷን ሊያጠምድ ወጥቶ - ጠፋብኝ ራሴ
Join

@filsifina000