Get Mystery Box with random crypto!

ምን አይነት ህዝብ ነህ? (ደሱ ፍቅርኤል) ከጥንት አይቻለሁ የወደዱህ ሁሉ ወድቀዋል ከፊትህ ፍቅር | ጥበብ

ምን አይነት ህዝብ ነህ?
(ደሱ ፍቅርኤል)

ከጥንት አይቻለሁ የወደዱህ ሁሉ ወድቀዋል ከፊትህ
ፍቅርህን ለሚሉ ሞት ነው ሽልማትህ
ምን አይነት ህዝብ ነህ?
እኔ እወድሃለሁ
መውደዴን እንዳልገልፅ - ግን እፈራሃለሁ
ሲያከብሩህ አታከብር ሲወዱህ አትወድም
ጠላሁህ ለሚሉህ ለሚበድሉህ ነው የምታገለድም
ጨለማ ሲውጥህ
የትም ሲዘርርህ ህይዎት እንደ ፈንግል
ቅድስት ሀገር እያልክ ራስህን ሸንግል
የህልመኛ ሾተላይ
የእውር-ድንብስ ተጓዥ የባዶነት መንጋ
ፀሀይ እያጠፋህ
ጨረቃ እየጋረድክ እንዴት ብሎ ይንጋ?
ኢትዮጵያ ሀገሬ
ቅድስት ናት ብሎ ማነው ያዘናጋሽ?
እርጉም ነሽ እወቂው
ሞት ለመለመን ነው አክናድ የዘረጋሽ!
ባዶ
ባዶ
ባዶ
ህልሜ ሁሉ ባዶ
ፍቅሬ ሁሉ ባዶ
ሰው እንዴት ተስፋ ያርግ
በሾተላይ አገር ህልም ይዞ ተወልዶ?
ከስህተትም ስህተት ከመርገምም መርገም
በተስፋቢስ መሬት በተስፋ መፍገምገም!
ምን አይነት ህዝብ ነህ ተርመስማሽ ግትልትል
የወደቁልህን ለመብላት መጣደፍ እንደ መቃብር ትል!
እስከመቼ ድረስ ህልመኛ ይቀርጠፍ?
እስከመቼስ ድረስ
አንቺን የወደደ በአበባው ይቀጠፍ?
ልንገርሽ ሀገሬ እኔ እወድሻለሁ
መውደዴን እንዳልገልፅ ግን እፈራሻለሁ
አንቺን የወደዱ ሲዋረዱ አውቃለሁ
ሲሞቱ አይቻለሁ
እይው እስኪ ሀገሬ
ህልም አጨናጋፊው ደረት እየነፋ ህልመኛ ይሰጋል
ልፋ ቢለው እንጅ
በተስፋቢስ ሀገር ነገ በሌለበት ህልም ምን ያደርጋል?