Get Mystery Box with random crypto!

አንግዲህ ይህ ሃሳብ ነው የኢትዮጵያ ችግር መፈቻ ቁልፍ ሆኖ በአለማያው ገላገይ፣ በዚህ መጽሐፍ ዘን | ጥበብ

አንግዲህ ይህ ሃሳብ ነው የኢትዮጵያ ችግር መፈቻ ቁልፍ ሆኖ በአለማያው ገላገይ፣ በዚህ መጽሐፍ ዘንድ የቀረበው። መጽሐፉ ሙሉውን አጥፍተን ከዜሮ እንጀምር አይነት አቀራረብ ያለው፣ አለምን በጠባብ መነጸር ያየ ነው። ስራን (ባርነትን) የድህነት መውጫ መንገዶ አድርጎ ገልጾ ግን ያለውን መንፈሳዊ እውቀት ይጥፋ ይለናል፣ የሚተካውን የእውቀት መንገድ ግን አላሳየንም። የችግሩን መንስኤዎች በሙሉው የሚያሳይም አይደለም። እናም መፍትሔ ጠቋሚ አይደለም። ጥሩ ጥያቄ፣ የመፍትሔው መንገድ ግን የጎደለና በሾርኔ አይቶ ወይም ሳያይ ያለፈ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ችግርን በቃላት ድርድራ አንፈታውም። ትክክለኛውን የሃሳብ መንገድ አላገኘውም እያልኩ ነው። ችግራችን የምንፈታው፣ በዚህ አይነት የመንስኤ-ውጤት ግንኙነትን በሚያጣርስ፣ ሁሉ ይጥፋ ከዜሮ እንጀምር በሚል ሃሳብ አይደለም። የችግራችን መንስኤዎች ብዙ መሆናቸውን መለየት፣ መፍትሔም ከዚህ አንፃር መፈለግን ይጠይቃል። እናም ስንጽፍ ብቻ ሳይሆን አስተያየት ስንረጥም ይህን ያገናዘበ መሆን አለበት። ከመጽሐፉም፣ ከውይይቱም ግን ይህን አላየሁም። ከዜሮ መጀመር መፍትሄ አይደለም። መፍትሄው ያለንን ጥሩ፣ ከመጥፎው መለየት። የጎደለውን ከአለም ዘንድ መፈለግና ለእኛ ችግር መፍቻ በሚሆን መንገድ መቅረጽ፣ ሁለቱን ለንቅጦና የእኛ አድርጎ መጠቀም ነው። ይጥፋ አብዮት ወይም ኒሂልስም ነው፣ ጥፋት። ከጥፋትም ልማት አይገኝም።

የተጠላው እንዳልተጠላ
አለማየሁ ገላጋይ