Get Mystery Box with random crypto!

ዐውደ ጥበብ📖

የቴሌግራም ቻናል አርማ awdetibeb — ዐውደ ጥበብ📖
የቴሌግራም ቻናል አርማ awdetibeb — ዐውደ ጥበብ📖
የሰርጥ አድራሻ: @awdetibeb
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 756
የሰርጥ መግለጫ

ስዕል እና ግጥም 😍
እሁድ ብቻ

youtube channel =
https://www.youtube.com/channel/UCZECculwWjbdvPmLS3IWVCQ
subcribe በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-18 21:49:29 'አንድ ጌታ ፣ አንዲት ሐይማኖት ፣ አንዲት ጥምቀት ' ኤፌ ፬:፭

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም
አደረሳችሁ!!!!
558 viewsDesu Tegegn, edited  18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 22:13:14 እግዜር በምድር ላይ ፣ እስር ቤት ቢኖረው
ሁሉም ወንጀለኛ ፣ ሁሉም እስረኛ ነው

ደሱ ተገኝ
@awdetibeb
774 viewsDesu Tegegn, 19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 19:48:36 ሙክቱ ዶሮ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የበዓል ዋዜማ ላይ ከቀን ወደ ስምንት ሰዓት ገደማ አንዳንድ ነገር ለመግዛት እናቴ ጋር ገበያ ወጣን ። እና በመጀመሪያ የዶሮ ተራን ለማየት ወስነን ትንሽ  ገባ እንዳልን አንድ ፊቱ ደረቅ ያለ ወጣት የአንበሳ ደቦል የሚመስሉ ዶሮዎች ይዞ አየን። እኔም ጠጋ ብዬ አዘቅዝቄ ወደ አንዱ ዶሮ እያየሁ 'ስንት ነው አልኩት ? ' ። ሰውየው ወደ ዶሮው ትንሽ እያየ ቆየና ። 'ቆንጆ ዶሮ ነው ላት እራሱ ሊኖረው ይችላል የሚል ጥርጣሬ አለኝ ' አለኝ። አረ ዋጋውን ነው የጠየቅኩህ ስለው ። ሰምቻለሁ እንደ መግቢያ ይሆንህ ዘንድ ብዬ ነው ። ደግሞም ዋጋውን ከማወቅህ በፊት ስለ ዶሮው ትንሽ ነገር ብታውቅ ይጠቅምሃል እንደ ጠቅላላ እውቀት(general knowledge) ውሰደው ። ዶሮው ቆፍጠን ያለ ጀግና ዶሮ ነው የሰፈር ዶሮዎች ቀና ብለው አየዩትም 'አለኝ ። እና እንዴት ብለው ነው ሚያዩት ልለው ፈልጌ እድሉን አላገኘሁም ። ' እንደ ሌሎቹ ዶሮዎች ሶስቴ ብቻ አይደለም ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት የሚጮሀው ።' አለ። ይሄ ነገር መድፍ ነፍስ ዘርቶ ነው እንዴ የገጠመኝ?' አልኩ በሆዴ አሁንም እድሉን ስላልሰጠኝ ።
'የሚውልበትን የሚያውቅ ደፋር እና ብልህ ዶሮ ነው' ብሎ ሊቀጥል ሲል አቋረጥኩትና ። 'በል ዋጋውን ነገረኝ ' አልኩት። እሱም ' ያው ዋጋው መጨረሻ የሌለው ዘጠኝ መቶ ብር ነው ' አለኝ። በቁሜ ክው ነው ያልኩት። በዝግመተ ለውጥ ወደ በግ የሚቀየር ነው የመሰለኝ ።  ለዚህማ መግቢያ ብቻ አይደለም ሀተታም ያስፈልገዋል ብዬ ዘወር ስል እናቴ የለችም በድንጋጤ ይመስለኛል ካጠገቤ ተሰውራለች ። በዘጠኝ መቶ ብር ሽንኩርት ከነጅራቱ ፣ ዘይት የባለ ሃይላንዱን እና በግ ከነማረጃው የሚገዛበትን ዘመን ላሳለፈ ሰው እውነትም መሰወር ሲያንስ ነው ብዬ ወደ ሻጩ ዘወር ስል ዶሮው በቆረጣ አየኝ ። እኔ ምልህ' ጀግናው የሰሜኑ ጦርነት ላይ ተሳትፏል እንዴ ቆረጣ ነው አስተያየቱ እራሱ' አልኩት። 'አዎ እሱ የመራው ግንባር ላይ ምንም ሽንፈት አልተስተናገደም ' አለኝ ። ጎበዝ ነጋዴ ነህ ስለምትሸጠው ነገር መረጃ ታሰባስባለህ ብዬ በል ቀንስ እና ሽጥልኝ አልኩት። 'ልጄ ተወው ' አለችኝ የተሰወረችው እናቴ ከየት እንደተከሰተች በማላውቀው ሁኔታ ካጠገቤ ቆማ። እኔም ነገሩን ተረድቼ ቆይ ትንሽ ልከራከር ይቀንሳል አልኳትና 'አትቀንስም? ' አልኩት በድጋሚ ሻጩን እየተማፀንኩ። 'በቃ ስምንት መቶ ሃምሳ ውሰድ ከዚያ በታች አይሆንም' አለኝ ። እናቴ ወገቤን ጉስም አድርጋ አረ ተወው የያዝኩት ብር አይበቃም ገና ሽንኩርት አልገዛሁም አለችኝ ። ግዛልኝ ከማለት የሚሻል አጠያየቅ ነው ። 'ግድ የለም እኔ ይዤአለሁ ' አልኳት ።
ሻጩ ከምክክራችን በጉጉት መልስ ሲጠብቅ የነበር ይመስላል ዘወር ስል 'እንዳያመልጥህ ውሰደው' አለኝ ።
እኔም ከዶሮው ይልቅ የዶሮው ታሪክ ስለደነቀኝ እሺ ይሁን አልኩት ። ከዚያ ክንፉን ለመያዝ ሲታገል 'ቆይ ቆይ ' ላግዝህ አልኩ እና ወፍራም ገመድ አምጥቼ ' አንገቱ ላይ አጥልቅልኝ እየጎተትኩ ነው የምወስደው 'አልኩት ። ለእናቴ ጅራፍ ገዝቼ ሰጠሗት ። ሻጩ ተገርሞ አየኝ እና 'በግ አረከው እንዴ ' አለኝ ። 'በዚህ ዋጋ ዶሮ ነው የገዛሁት ብዬ ብብቴ ውስጥ ብከተው ማን ያምንኛል 'አልኩት ። በዝግመተ ለውጥ ወደ በግ ቢቀየር እድሌን ልሞክር እንጅ  ብዬው ገንዘቡን ቆጥሬ ሰጠሁት እና  እናቴን " ጅራፉን እያኖጋሽ ቅረቢልኝ " አልኳት ። እኔ እየጎተትኩ እሷ እየቀረበች እንደምንም ቤት ደረስን ። እውነትም ጀግና ነው ዶሮው ክንፉን እራሱ ሚጠቀመው ላደጋ ጊዜ ብቻ ነው: ማለት እኔን ከምንም አልቆጠረኝም ወይም ወታደራዊ ስልት እያካሄደብኝ ይሆናል ። ብቻ አንድ ትልቅ ችካል ላይ ወስጄ አሰርኩት ። እናቴ ቤት ውስጥ አለ የተባለ ሳፋ (በውሃ ቢለካ አምስት ሊትር በትንሹ የሚችል ) እያዘጋጀች አየሗትና ። 'ምን እያረግሽ ነው ?' አልኳት ። 'እረደው እንጅ በጊዜ እንደሰራው ' አለችኝ ። እኔም ' ብቻዬን ነው ማርደው?' አልኳት ። 'አዎ ' አለችኝ ። ' እኮ የስምንት መቶ ሃምሳ ብር ሙክት ዶሮ ብቻዬን ላርደው??' ስላት። 'ወንድ አይደለህ እንዴ !!!' አለችኝ ። እሱን ተይው ብዬ በሆዴ ' ቆይ ጎረቤት ልጥራ ' አልኩና የሰው ሃይል አሰባሰብኩ ። ሁሉም ከመጡ በኋላ አንዱ አንድ ክንፉን ፣ አንዱ አንድ ክንፉን ፣ አንዱ አንድ  እግሩን ፣ አንዱ አንድ እግሩን  ፣ አንገቱን እና አፉን ቆልምሞ የሚይዝልኝ ሰው መደብኩ። እናቴ  አንዲት ብርቱካን መሰንጠቂያ የምታክል ቢላ ይዛ መጣች። በቃ ምን ልበላት ቆሌዬን ነው የገፈፈችው ። 'አሁን በዚህ  ላርደው ነው ወይስ ሙጀሌ ላወጣለት ነው?' አልኳት እና እንዳያመልጣችሁ ብዬ ሰዎቼን አስጠንቅቄ በግራንደር የተሳለ አርባ ገራፊ(ገጀራ) ከጋሻ ጋር ይዤ ስመለስ ሙክቱ ዶሮ ሊያመልጥ እየታገለ ፣ ሰዎቹ ላብ በላብ ሆነዋል ።  እንዴ!!! እሄንማ ቶሎ ልጥረበው አልኩ እና ያለ የሌለ አቅሜን አጠራቅሜ ገጀራውን አንገቱ ላይ ባሳርፈው ገጀራው ተጣመመ ። ልደግመው ስል እግሩን አንስቶ ሆዴ ላይ አሳረፈው ። እኔን ለብቻ ፣ ገጀራዬን ለብቻ ፣ ጋሻዬን ለብቻ ፣ ሰዎቼን ለብቻ ለብቻ ገነጣጠለን።  ለትንሽ ደቂቃ እራሴን ስቼ ስነሳ ሙክቱ ዶሮ አንድ ኩንታል ጥሬ እናቴን አዞ አስበትኖ ጥሬ እየለቀመ ነው  ።  እውነትም ኮማንዶ ነው  ክንፉን ላደጋ ጊዜ ብቻ የሚጠቀም!!! ። እኔም እናቴን 'የሚያርድ ባለታንክ እና ታንከኛ ሰው ጥሪ ' አልኳት እና በእግራ እግሩ ሳይደግመኝ ቀስ ብዬ ተንፏቅቄ አመለጥኩ ።  ማታ ስመለስ እናቴ በርሚል ማን እንዳበደራት አላውቅም ፣ ሙክቱንም ማን እንዳረደው አላውቅም መቀመጫ ቀጣጥላ ቆማ በግምት ሶስት ሜትር ቁመት ያለው ማማሳያ(የወጥ እንጨት) ወገቡን በትከሻዋ ተሸክማ ወጡን እያማሰለች ነበር።
(ሽንኩርቱን በምን ሰዓት ገዝታው ይሆን!!)
~~~~~~~~~~~~~~~~~
ደሱ ተገኝ...

እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!

@awdetibeb
725 viewsDesu Tegegn, edited  16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-20 16:49:59 #የአህያነት_ባህሪህን_ካልተውክ_ጅቦች_አንተን_መፈለግ_አያቆሙም
አንዱ ጠንቋይ ጋ ይሄድና "ጌታዬ ማታ ማታ ወደ ስፈሬ ስገባ ጅብ አስቸገረኝ እባኮትን እሚታሰር ምናም ይስጡኝ" ይላል ጠንቋይም "እሺ እንግዲ
ጅቡን በቋንቋው አናጋግሬ መደሀኒቱን እስጠሀለው ምሳችንን ስጥና ሂድ ከሳምንት ቡሀላ ተመለስ" ይለዋል ሰውየውም በሳምንቱ ይመለስና " ጅቦቹን አነጋገሩልኝ"ብሎ ይጠይቃል ጠንቋዩም "አዎ" አናግሬያቸው ነበር ይለዋል። ሰውየውም " እና ለምንድነው እምናስቸግረው አሉ" ሲል "ከአህያ ጋር እየተመሳሰለብን ነው" ብለዋል አለው። ጠንቋዩም ቀጠል አድርጎ " ወዳጄ ጅቦችን ከመክሰስክ በፊት የአህያ ባህሪን ተው ብሎ መክሮ ሸኘው። ታዲያ ዛሬ ስለራሳችን ባህሪ በደንብ አውቀን ነው ሌሎችን ለመውቀስ ምንሯሯጠው? መልሱ ለናንተው ትቻለው።
ከእያዩ ፈንገስ!!!

@awdetibeb
770 viewsDesu Tegegn, 13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-11 18:24:43

690 viewsDesu Tegegn, 15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-10 13:39:08 subscribe በማረግ ይቀላቀሉ !!!
አስተማሪ የሆኑ የቲክቶክ ቪዲዮችን ከላካችሁ እኔ publish አረግላችሁለሁ




624 viewsDesu Tegegn, edited  10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 14:07:24 አንዳንድ ሰዎች እጅግ ድሆች ናቸዉ፤ ገንዘብ ብቻ ነዉ ያላቸዉ። — ቦብ ማርሌይ
700 viewsDesu Tegegn, 11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 11:26:32 ፅናት እና ናፍቆት
~~~~~~~~~~~~~
ትላንት ...

ወዜ ደብዛው ጠፍቶ ፣
እንደ ወለደች ላም ፣ አንጀቴ ተጣብቆ
ናፍቆት ህልሙን ድሮኝ ፣
አላስችልህ ቢለኝ ፣ መኖር ተራርቆ
ጀንበር ስትዘቀዝቅ ፣
በቀዝቃዛው አየር ፣ ብመኝሽ ከጎኔ
እያመመኝ መጣሁ ፣
ካንቺ አይብስም ብዬ ፣ ህመም ወሀዘኔ
ይሄን ሰማች መሰል ፣
ያን እለት ልታበራ ፣ ጨረቃ አልወጣችም
በድቅድቅ ጨለማ ፣
ከተማው ተውጧል ፣ ጎዳናው አይመችም
አይጣል ነው መቸም!!!
ወዴት ነሽ ውዴ ሆይ ፣
በየት በኩል ልምጣ ፣ እያልኩ እንዳላሻሁ
የመንገድ መብራቶች ፣
ለጨረቃ አ'በሩ ፣ ሳላይሽ አመሸሁ

አላቆምኩም ነበር...

እንቅፋት ካልበዛ ፣ ፍቅር አይጣፍጥም
ዘጠኝ እድል መሀል ፣  ባንዱ ተስፋ አልቆርጥም
ወደ ፊት ነው መውደቅ ፣
በሚል ቃል ባንኜ  ፣ ወኔ ተጋብቶብኝ
ሀሩሩ ንዳዱ ፣
ልክ እንደ ዶፍ ዝናብ ፣ እየወረደብኝ
ተስፋዬን አንግቤ ፣
እየተንደረደርኩ ፣ ህልሜን ተሸክሜ
ነጋ ባልኩት እለት፣
በቀን እኩሌታ ፣ ቀትሩን ተቋቁሜ
መጣሁኝ ደግሜ !!!
አያምጣው አይደለ ፣
ያንዳንዴ አገጣጠም ፣ ወዶ ፈቅዶ ማፈር
ቀረሽ ነግቶም መሸ  ፣
አንድ ያንቺን ቀጠሮ ፣ እርሜን ብደፋፈር

ዛሬ ...

ሲሮጡ የታጠቁት ፣ ሲሮጡ ይፈ'ታል
በሦስት ካልፀና ፣ ነገር ይሸብታል 
ቢቆነጠር እንጅ ፣ ተሟጦ ማይጠፋ
ባህርን ይመስላል ፣ ያፍቃሪ ሰው ተስፋ 
ብዬ መንገድ ጀመርኩ ፣
ትላንቴን ሚያስረሳ ፣ ቄጠማ ነስንሼ
የተናደው ልቤን ፣
ክቤው እንደገና  ፣ ገንብቼ መልሼ

ዳሩ ምን ያደርጋል...

ቀሚስሽ እንደ ክንፍ ፣
ባየር ላይ ሲንሳፈፍ ፣ እያየሁ ስትሮጪ
እድል ቀናችኝ ስል ፣
ናፍቆቴን ል'ወጣ ፣ ጓጉቼ ስትመጪ

አንቺን ናፋቂ ዓይኔ ፣
ካይንሽ ሊገጣጠም ፣
ተጣድፎ እስክትደርሺ ፣ ከሩቅ ሲመለከት
ልክ ስትቀርቢ ፣
ንፋስ እንኳን ባቅሙ ፣
ምቀኝነት ለምዶ ፣ አቧራ አስገባበት !!!
~~~~~~~~~~~~~~~~
ደሱ ተገኝ

(Modified=የተሻሻለ)
@awdetibeb
870 viewsDesu Tegegn, 08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 11:24:51 "የምትማረው ሰው ኹሉ እውቅና በሰጠው መንገድ ተጉዘህ ቦታና መተዳደርያ ለማግኘት ነው። የምታነበው ግን በሕይወት አንተ ብቻ እውቅና የሠጠኸው ደረጃ ላይ ለመድረስ ነው።"

ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ

@awdetibeb
620 viewsDesu Tegegn, 08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-17 14:57:15 Watch "ትኩረትን ያጣ ነገር ትልቁ ትንሽ ነው !! የሃሳብ ሃይል በከድር አሰፋ ክፍል አንድ" on YouTube


917 viewsDesu Tegegn, 11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ