2022-06-05 08:23:13
የትዳር ዝግመት ለውጥ
ድንክ ልቦለድ
እንጋባ ሲል ጠየቃት አሳምነው …የለም… አለች አስማሩ ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል አለችው ተስማሙ ፡፡ ቤቷ እየመጣ እንደወትሮው ይጠይቃታል ፡ ቡና ታፈላለታለች ይጠጣሉ የሚቀመስ ካለ ታቀርብለታለች ይበላሉ አውግተው ይለያያሉ፡፡
የትዳር ነገር ዳግመኛ አልተነሳም : አሳምነው አንድ ቀን በጠራራው ፀሐይ መጣ፡፡ ቤት እንደገባ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ፡፡ ስለዘንድሮው ሙቀት ብዙ አውርተው ተለያዩ አሳምነው ሲወጣ ሹራቡን ረስቶት ወጣ፡፡ አስማሩ አሳምነው ረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለትና አስቀመጠቸው፤ ደግሞ ሲመጣ ደርቦ ነበርና የሚያልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ አላስፈለገውም ጃኬቱን አውልቆ ሄደ አስማሩ እሱንም አጥባ አኖረችው፡፡
ሌላ ቀን ሱሪውን ደርቦ መጣ በርዶት ነበር እሷን ሲያያት ወበቀው አወለቀው አስማሩ አጥባ አኖረችው ፡፡ በሌላ ቀን ደግሞ ደርቦት የመጣውን ካፖርት ጥሎ ሄደ አጥባ አኖረችው፡፡
አንድ ቀን በጠራራ ፀሃይ ብርድ ልብሱን ተከናንቦ መጣ አስማሩ ምነው አለችው፡ በጠራራ ፀሐይ ብርድ ሆዴ ገባ አላት ምች ይሆናል አለችው፡፡ የምች መድሃኒት ተቆርጦለት ተሻለው፡፡
ሲሻለው ብርድ ልብሱ አላስፈለገውም ጥሎ ሄደ፡፡ አስማሩ ብርድ ልብሱን አጥባ አኖረችው፡፡ ትንሽ ቆይቶ ፍራሹን ተሸክሞ መጣ ምነው አለችው አስማሩ ላሳስደው መሄድ ነው አይቼሽ ልለፍ ብዬ መጣሁ አላት አመነችው ጨዋታው ደራ ፍራሹን እረስቶት ሄዶ ኖሮ እኩለ ለሊት ላይ ቢመጣ አስማሩ ቦታ ስላጣች ፍራሹን ፍራሽ ላይ ደርባው ደረሰ ያኔ ተነሽ ከማለት “ጠጋ” በይ ማለት ቀሎ ተገኘ ጠጋ አለች፡፡
ከቆየ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ያገኘሁት ነው፡፡
https://t.me/filsifina000
https://t.me/filsifina000
https://t.me/filsifina000
707 views05:23