Get Mystery Box with random crypto!

ሙላ ነስሩዲን አንድ እጅግ አስቸጋሪ ፣ ተናካሽ አህያ እና ተራጋጭ አህያውን ለመሸጥ ገበያ ይዞት ወ | ጥበብ

ሙላ ነስሩዲን አንድ እጅግ አስቸጋሪ ፣ ተናካሽ አህያ እና ተራጋጭ አህያውን ለመሸጥ ገበያ ይዞት ወጣ። ወደሉ አህያ ማንንም ሊያሳቀርብ አልቻለም። የተጠጋውን ሁሉ ይናከሳል ይራገጣል።

" እውን ሙላ ይህን አስቸጋሪ አህያ እሸጣለሁ ፣ ሰው ይገዛኛል ብለህ ነው ግን ገበያ ይዘኸው የወጣኸው ?" አሉት አንድ ገበያው ውስጥ ያገኙት የሚያውቁት ሰው።

" ፈፅሞ ! ፈፅሞ ልሸጠው አይደለም ! ከምን አይነት አስቸጋሪ አህያ ጋር እየኖርኩ እንዳለሁ ዓለም እንዲያውቅልኝ ብዬ እንጂ ....”