2022-12-22 12:11:00
የጎንደር ከተማ መጅሊስ በአዲስ መልኩ ተዋቀረ
በአማራ ክልል መጅሊስ አመራሮች መሪነት የጎንደር ከተማ መጅሊሥ በአዲስ መልኩ እንዲዋቀር ተደርጓል::
በጎንደር ከተማ በጀሚዓል ከቢር መስጅዳ አዳራሽ "ኢስላማዊ አንድነት ለሀገራዊ አብሮነት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ የጎንደር ከተማ እስልምና ጉዳዬች ምክር ቤት የሙስሊሞችን አንድነት በሚያስጠብቅ መልኩ ተቋቁሟል::
አዲሱ አመራርም ከከፋፋይ አጀንዳዎች በመራቅ ብዙ የቤት ስራ ለሚጠብቀው የከተማው ህዝበ ሙስሊም የሚመጥን ስራዎችን እንዲሰሩ ይጠበቃል::
የአማራ ክልል መጅሊስ ከሪፎርሙ ቡኃላ በፍጥነት በስሩ ያሉ ዞኖችን እና የከተማ መጅሊሶችን በማዋቀር በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ተቀባይነትን እና ተወዳጅነትን ያተረፉ ለሙስሊሙ አንድነት የሚጨነቁ አሊሞችን እና አመራሮችን የመሪነቱን ሚና እንዲጫወቱ እያደረገ ይገኛል።
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
101 views09:11