Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.85K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2020-12-02 16:05:02 የተሳሳተ መረጃ ማስተካከያ
==============
ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢፌዲሪ ፈዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሀገር ክህደት ወንጀል የፈፀሙ በርካታ የከሀዲው ጁንታ ህዋሀት ቡድን አባላት የሆኑ ጀኔራል መኮንኖች ፣ ከፍተኛና የመስመር መኮንኖች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣቱንና እነዚህን ህገወጦች በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል መጀመሩን ለህዝብ ይፋ ማደረጉ ይታወቃል።
ኮሚሽኑ የክትትል ስራውን አጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም በኢትዮ FM የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገልፀዋል በሚል 38 የህዋሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል ስል ያስተላለፈው መረጃ ሐሰትና በም/ኮሚሽነር ጀነራሉ ያልተላለፈ መሆኑን እየጠቆምን ተያዙ በሚል ሃላፊው የገለፁት መከላከያ ውስጥ የግንኙነት መስመር ያቋረጡና ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዱን (ወዲ ነጮን) ጨምሮ 38 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው መሆኑን እየጠቆምን ከጁንታው ቡድን አባላት ከአሁን በፊት ከተገለጹት በስተቀር እስከአሁን ተጨማሪ አዲስ የተያዙ አለመኖራቸው ታውቆ ሌሎች ሚዲያዎች ይህንን የተዛባ መረጃ ለህብረተሰቡ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን ።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን

@fastmereja
13.3K viewsedited  13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-02 11:09:29 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቦንብ ፍንዳታው ምንም የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ገለፀ፡፡
***
ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ጎርጎርዮስ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ የቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ተጥሎ የተገኘ ቦምብ ከአካባቢው ሰዎች በደረሰው ጥቆማ የፈንጅ አምካኝ ባለሙያዎች ወደ ቦታው በማቅናት ለማምከን ባደረገው ሙከራ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሊፈነዳ ችሏል፤
በዚህም አንድ ግለሰብ የቦንቡ ፍንጣሪ በቅርብ ርቀት ከሚሰራበት ጋራዥ ቅጥር ግቢ በስራ ላይ ሳለ በፍንጣሪው ቀላል ጉዳት የደረሰበት ሲሆን ተጎጂው የህክምና ርዳታ በማግኘት ወደ ቤቱ መመለሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እየገለፀ ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ባላቸው ግለሰቦችና አጠቃላይ የምርመራውን ውጤት እንደደረሰን የምናሳውቅ ሲሆን በተመሳሳይ በዚሁ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጉርድ ሾላ ቅዱስ ያሬድ ሆስፒታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለፖሊስ በደረሰ መረጃ መሰረት ባለሙያዎች ቦታው ድረስ በመገኘት ቦንቡን የማምከን ስራ ሰርተዋል፡፡
በነብስ ውጪ ግቢ ጣር ላይ የሚገኘው የጁንታው ተላላኪዎች በከተማችን አዲስ አበባ በንፁሃን ላይ ከባድ ጉዳት ለማድረስ የሚደርጉትን መንፈራገጥ ለማምከን የሚቻለው ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር የሚኖረውን የመረጃ ልውውጥ በማጠናከርና አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ መሆኑን ኮሚሽኑ ማስገንዘብ ይወዳል፡፡

አዲስ አበባ ፖሊስ
-------------
@fastmereja
12.7K views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-01 20:01:31 ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ

ከተፈላጊ የህወሓት ጁንታ አባላት አንዷ የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ።

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የህውሓት ከፍተኛ አመራርና በመንግስት ከፍተኛ ሃላፊነት የነበራቸው እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት አገልግለዋል። ፋና

@fastmereja
21.2K viewsedited  17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-30 20:41:02 የአሮጌው ብር የመገበያያ ጊዜ ከነገ ጀምሮ ያበቃል

የአሮጌው ብር ኖት የመገበያያ ጊዜ ከነገ ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ያበቃል።

የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል።

ባንኩ ከዚህ ቀደም ህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ከነገ ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት አይቻልም።

ከመስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አሮጌ የብር ኖቶች በአዲስ የብር ኖቶች እየተቀየሩ መሆኑ ይታወቃል።

የብር ኖት ቅያሬው በሶስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መወሰኑም አይዘነጋም።
-------------
@fastmereja
10.9K views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-30 15:32:01 ዛሬ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን በፓርላማ የተሞገሱ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እና የጀግናዉ መከላከያ ሰራዊታችን አመራሮች
1. ድል ቁርሱ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ
2. ትንታጉ ሌ/ጀነራል አበባዉ ታደሰ
3. ነበልባሉ ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ
4. ሀገር ወዳዱ ሌ/ጀነራል ዮሃንስ ገብረመስቀል
5. የወገን አቅም ገንቢዉ ሌ/ጀነራል ሀሰን ኢብራሂም
6. ግስላዉ ሌ/ጀነራል ጌታቸዉ ጉዲና
7. አነፍናፊዉ ሌ/ጀነራል አስራት ዲናሮ
8. የጦርነት ሊቁ ሜ/ጀነራል አለምሸት ደግፌ
9. ሰዉ ሀይል አመጋጋቢ ሜ/ጀነራል ሀጫሉ ሸለማ
10. አይበገሬዉ ሜ/ጀነራል ዘዉዱ በላይ
11. ሳተናዉ ሜ/ጀነራል በላይ ሥዩም
12. ልበ ቆራጡ ሜ/ጀነራል መሰለ መሰረት
13. ሎጂስቲክስ አሳላጩ ሜጀር ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል
14. ንስሩ ሜ/ጀነራል ሹማ አብደታ
15. አርዕድ አንቀጥቅጡ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ
16. ነጎድጓዱ ሜ/ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ
17. ንስሩ ሜ/ጀነራል ብርሃኑ በቀለ
18. ካርታን እንደ ምድር አንባቢዉ ብ/ጀነራል ተስፋዬ አያሌዉ
19. ጀግናዉ ብ/ጀነራል ግርማ ከበበዉ
20. ቆራጡ ብ/ጀነራል ናስር አባዲጋ

@FastMereja
10.1K views12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-30 12:02:20 በመከላከያ ውስጥ የነበረውን የትግራይ ተወላጆች የበላይነት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተዘርዝሮ ተነግሯል

መከላከያ ውስጥ የሙሉ ጀነራል ማዕረግ 60 በመቶ በትግራይ ተወላጆች የተያዘ ነበር፤ የሌሎች ብሄሮች ድርሻ 40 በመቶ ብቻ ነበር፤

ሌተናል ጄነራል የትግራይ ተወላጆች 50 በመቶ ድርሻ ነበራቸው፤

ሜጀር ጀነራል የትግራይ ተወላጆች 45 በመቶ ድርሻ ነበራቸው፤ በብርጋዴር ጀነራል ማዕረግ የትግራይ ተወላጆች 40 በመቶ ድርሻ ነበራቸው፤

በኮሎኔል ደረጃ 58 በመቶ የትግራይ ተወላጆች ድርሻ ነበራቸው፤

በሌተናል ኮሎኔል ደረጃ 66 በመቶ በትግራይ ተወላጆች የተያዘ ነበር፤

በሻለቃ ማዕረግ 53 በመቶ በትግራይ ተወላጆች የተያዘ ነበር፤

እዞች ውስጥ አዛዥ መቶ በመቶ በትግራይ ተወላጆች የተያዘ ነው፤

ምክትል አዛዥ መቶ በመቶ በትግራይ ተወላጆች የተያዘ ነበር፤ በሁሉም የሰሜን እዝ ላይ አዛዥ እና ምክትል አዛዥ ሎጂስቲክ እና አስተዳደር በትግራይ ተወላጆች የተያዘ ነው፤

ክፍለ ጦሮች ውስጥ የኢትዮጵያ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦሮች መቶ

በመቶ አዛዦቹ በትግራይ ተወላጆች የተያዙ ናቸው፤

እግረኛ ክፍለ ጦሮች 80 በመቶ በትግራይ ተወላጆች የተያዘ ነው፤

በመከላከያ ዋና መምሪያ ውስጥ 80 በመቶ በትግራይ ተወላጅ የተያዘ ነበር፤

ሜካናይዝድ ብርጌዶች 85 በመቶ እግረኛ ብርጌድ 80 በመቶ በትግራይ ተወላጆች የተያዘ ነበር፤

በመከላከያ ስልጠና ተቋማት ውስጥ 85 በመቶ በትግራይ ልጆች ነው የሚመራ ነበር፤

EPA
-------------
@fastmereja
9.6K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-28 20:32:46 የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ጀግናው ሠራዊታችን መቀሌን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አረጋገጡ ።
9.9K views17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-27 11:23:16 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ኅዳር 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ኅዳር 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ።ቢሮው ተማሪዎች በተገለጹት ቀናት ወደ መፈተኛ ጣቢያዎች በመገኘት ፈተና እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

[AMN]
-------------
@fastmereja
21.0K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-26 09:24:59
የመጨረሻው የዘመቻው ምዕራፍ ተጀምሯል።
22.3K views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-25 20:04:44 በየሄደበት ሁሉ በሁለቱም እጆቹ ላይ ሁለት ሰዓቶችን ያጠልቃል፤ አንደኛው የሀገሩን የአርጀንቲናን የሰዓት አቆጣጠር ይከተላል፤ ሁለተኛው ሰዓት ደግሞ የሚሄድበትን ሀገር ሰዓት ይቆጥራል

ዛሬ ግን የአርጀንቲናውም የአለሙም ሰዓት ቆሟል። ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና የእግር ኳሱ ንጉስ ከዚህች አለም በሞት ተለይቷል

የጊዜ መቁጠሪያው የ24 ሰዓት ርዝመት፣ የሰዓቱ የ60 ሰከንድ መዘውር ማራዶናን በ60 አመቱ በቃህ ብሎት ቆጠራውን አቁሟል። በእግሩም በእጁም እግር ኳስን እንደፈለገው ያሾረው ባለ ዘውድ ንጉስ ትዝታውን ትቶ አልፏል... ነፍስ ይማር!!!
Via: ታምሩ አለሙ
-------------
@fastmereja
11.5K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ